Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የብዙሀን መንገድ ሁሌም ትክክል ወይንስ.....?

 

Abubeker Siraj
           =====የብዙሀን መንገድ ሁሌም ትክክል ወይንስ.....? ?======

በጃሂልያ ዘመን (ረሱል ሰለላሁአለይሂወሰለም ከመላካቸው በፊት) ሕዝብ የበዛበትን መንገድ ልክ እንደ ትክክለኛ መንገድ አድርገው የሚያስቡ ነበሩ። ጥቂቱን (አናሳውን) ደግሞ እንደተሳሳተ አድርገው ነበር የሚወስዱት። ስለዚህ በነርሱ እይታ ሕዝብ ብዛት የሀቅ መንገድ ነገር ግን የሰው ቁጥር ማነስን ልክ እንደ ጠማማ መንገድ ነበር። ይሄ ነበር ለነርሱ የሀቅ እና የተሳሳተ መንገድ መመዘኛ (የሰው ብዛት)።
ነገር ግን ይሄ የተሳሳተ አመለካከት ነው።
አላህ በቁርዓኑ እንዲህ ይላል

وَإِن تُطِعْ أَكْثَرَ مَن فِي الْأَرْضِ يُضِلُّوكَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا الظَّنَّ وَإِنْ هُمْ إِلَّا يَخْرُصُونَ [٦:١١٦]
በምድርም ካሉት ሰዎች አብዛኞቹን ብትከተል ከአላህ መንገድ ያሳስቱሃል፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡ አል አንዓም 116

أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ [٧:١٨٧]
ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፤ በላቸው። አል አዕራፍ 187

" ስለዚህ መመዘኛው የሰው መብዛት ወይም ማነስ ሳይሆን መመዘኛው ሀቅ ነው። እናም ማንም ሀቅ ላይ ያለ ሰው ትክክለኛው መንገድ ላይ ነው። ምንም እንኳን ብቻውን ቢሆንም። እርሱ ነው ቅኑን ጎዳና ተከትሎ ለስኬት የሚበቃው። ነገር ግን ምንም እንኳን የሰው ቁጥር ቢበዛም ሀቁን መንገድ ካልተከተሉ ከነርሱ መንገድ መራቁ ግዴታ ነው። እንዳይሳሳትም መጠንቀቅ አለበት። ማየት ያለብን ሀቁን ነው። አንዱ አሊም ብለዋል:- "ሀቅ በሰው አይመዘንም ነገር ግን ሰው በሀቅ ይመዘናል" በመሆኑም ማንም ሀቅ ላይ ያለ ስው ሊከተለው የሚገባው የያዘውን ሀቅ ብቻ እና ብቻ ነው።"

አላህ ስለቀደምት ህዝቦች በቁርዓኑ ላይ ሲያነሳ እንዲህ በማለት ሁሌም አናሳው በሀቅ መንገድ ላይ እንዳለ ይነግረናል

አላህ ስለቀደምት ዝቦች በቁርዓኑ ላይ ሲያነሳ እንዲህ በማለት ሁሌም አናሳው በሀቅ መንገድ ላይ እንዳለ ይነግረናል

وَمَا آمَنَ مَعَهُ إِلَّا قَلِيلٌ [١١:٤٠]
ከርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም። ሁድ 40

በሀዲስ እንደተገለጸው ረሱል ሰለላሁአለይሂወሰለም አየሁኝ አሉ:- " ነቢይ ሆኖ በጣም ትንሽ ህዝብ የሚከተለው ፤ ነቢይ ሆኖ አንድ እና ሁለት ሰው የሚከተለው ፤ ነቢይ ሆኖ ምንም ሰው የማይከተለው። " (ሰሂህ ቡኻሪ)

"ሰዎች የበዙበት መንገድ ሁሌም እንደ ሀቅ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባውም። ሊታይና ሊወሰድ የሚገባው የዕውነት ወይም የውሸት መንገድ መሆኑ ብቻ ነው። ስለዚህ ሀቁ ምንም ሆነ ምንም ሰው ሊከተለው ይገባል ምንም እንኳን አናሳውም ወይንም ማንም ህዝብ ባይከተለውም። ስለዚህ ሀቁ መንገድ ነው መከተል ያለብን ይሄ ነው መዳኛው መንገድ።"
ረሱል ሰለላሁአለይሂወሰለም ብለዋል:-
"ኢስላም እንግዳ ሆኖ ይመጣል እንግዳ ሆኖ ይመለሳል።"
"ይሄ የሚሆነው ፈሳድ በበዛበት ወቅት ነው። ወሸትና ባጢል ይንሰራፋል:: ጥቂት ሰዎች (እንግዶች) ሲቀሩ ሁሉም ከትክክለኛው መንገድ ይስታል፤ እናም እነዛ ሀቅ ላይ ያሉት ጥቂት ሰዎች እንደ እንግዳ ይታያሉ።"
አልፉደይል ኢብን ኢያድ ረሂመሁላህ ብለዋል
"ያለህበት መንገድ ትክክለኛ ከሆነ አብረውህ ባሉት ጥቂት ሰዎች ቁጥር አትጨነቅ። ሁሌም ቢሆን የጥመትን መንገድ ተጠንቀቅ። በውሽት የተመሰረተ የሕዝብ ባዛት እንዳትታለል ተጠንቀቅ።"
======ሸይኽ ሳልህ አል ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ) =======