Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የኛዎቹ vs. ሸኹ


የኛዎቹ vs. ሸኹ
__________
ሸይኽ ረቢዕ (አላህ ያቆያቸው) በአንድ ወቅት ለዳዕዋ ወደ ሱዳን ይሄዳሉ ፤ በቆይታቸውም በአንድ መንደር ውስጥ የሚገኙ መሳጂዶችን ይጎበኛሉ ፤ አብረዋቸው ይሄን ዳዕዋ ከሚያደርጉ የሱዳን ወጣቶች መካከል በመንደሩ የሚገኙ መሳጂዶችችን ሁሉ እንዳዳረሱና አንድ መስጂድ ብቻ እንደቀራቸው ሸኹ ይሰማሉ ፤ ሰምተውም ' ለምን ?' ብለው ይጠይቃሉ ፤ የተሰጣቸውም ምላሽ ' መስጂዱ የቲጃኒዮች (1) በመሆኑና በጣም ተዓሱብነት (ጭፍን ተከታይነት) እንደሚያጠቃቸው በመሆኑም ዳዕዋ እንዲያደርጉ እንደማይፈቅዱላቸው' ይነገራቸዋል ፤ ሸኹ ግን ቀድሞውኑ እግራቸውን ያነሱት ለተውሂድ ጥሪ ነበርና ወደ መስጂዱ ይዘዋቸው እንዲሄዱ ይጠይቃሉ ፤ ሰዎቹ ግን ' ይቅርቦት የተውሂድ ጥሪ ለመስማት ፍቃደኛ አይደሉም' አሏቸው ሸኹም 'እንሂድና ከፈቀዱልን ዳዕዋ እናደርጋለን ካልሆነም እንመለሳለን እኛ በጉልበት ዳዕዋ ልናደርግ አልመጣንም ይላሉ'።

ሰዎቹም ሸኹን ይዘው ወደ መስጂዱ ይጓዛሉ ፤ መስጂድ የደረሱትም በሰላት ወቅት ነበርና ሰላት ሰግደው እንዳጠናቀቁ ሸኹ ወደ ኢማሙ ቀረብ በማለት ዳዕዋ ለማድረግ እንደሚፈልጉና እንዲፈቅዱላቸው ይጠይቃሉ ኢማሙም ፈቃደኝነቱን ይገልፃል ።
ሸኹም ከመቀመጫቸው በመነሳት ንግግራቸውን ይጀምራሉ የአላህን ብቸኛ ተመላኪነትና ሰዎችቹ ያሉበትን ግልፅ ስህተት መረጃ እያጣቀሱ ዳዕዋ አደረጉ ፤ በመሃልም አንድን የእናታችን አዒሻን አሰር (ንግግር) በማጣቀስ ይናገራሉ ፤ አሰሩም ' እናታችን አዒሻ ቡኻሪ እና ሙስሊም እንደዘገቡት:- " አንድ ሰው መጥቶ 3 ነገሮችን ቢነግራቹ አላህ ላይ ትልቅ ቅጥፈትን ቀጥፏል 1ኛው ረሱል ሰለላሁዓለይሂወሰለም አላህን በአይናቸው አይተውታል ያለ 2ኛው ነቢዩ ሰለላሁዓለይሂወሰለም የወደፊቱን ያውቃሉ ያለና 3ኛው ነቢዩ ሰለላሁዓለይሂወሰለም ዲኑን ሙሉበሙሉ ለሰዎች አላደረሱም ያለ ናቸው" ብለው ሳይጨርሱ ኢማሙ ፍንጥር ብሎ ብድግ ይልና.. ' ይሄማ አይሆንም ወላሂ ! ረሱል አላህን ግንባራቸው ላይ ባለው አይን አይተውታል ' ብሎ ያቋርጣቸዋል ሸኹም ' አላህ በመልካም ይመንዳክ ነገር ግን እናታችን አዒሻ ከማንም በላይ ስለረሱል ሰለላሁዓለይሂወሰለም ታውቃለች ፤ ረሱልም ሰለላሁዓለይሂወሰለም አላህን በአይናቸው ቢያዩት ኖሮ ለርሷ በነገሯት ነበር' አሉት
ሰውየው ግን መናገሩን አላቆመም ሸኹም 'ንግግሬ እስክጨርስ ጠብቀኝና ከጨረስኩኝ በኋላ ጥያቄክን ትጠይቀኛለክ ፤ የማውቀው ከሆነ እመልስልካለው የማላውቀው እንደሆነም አላህ ያውቃል እልካለው' አሉት ።
ንግግራቸውንም ቀጠሉ ዳዕዋውን ከሚያደምጡት መካከል አንዱ ' ይህ 'ዙል' (በሱዳንኛ ይህ ሰው ለማለት ነው) የሚናገረው ዕውነት ነው' ይላል ። እሳቸው ዳዕዋቸውን በማድረግ ላይ ሳሉ የሰላት ወቅት ደረሰና አዛን እና ዒቃም ተባለ ፤ ሰው ለመስገድ ተነሳ ፤ ከዚያም ሰው ሸኽ ረቢዕ እንዲያሰግዱ ወደ ፊት ገፏቸው ሸኹ ግን አሻፈረኝ ቢሉም ሰው እንዲያሰግዱ ወደፊት መገፍተሩን አላቆመም ፤ እሳቸውም ግብዣውን ተቀብለው አሰገዱ ፤ ሰላቱን አጠናቀው መስጂዱን ለቀው ሲወጡ ሸኹ... ' ኢማሙን አላየኋቸውም የት ሄዱ?' ብለው ይጠይቃሉ ሰዎቹም ' አባረርናቸው !' ብለው መለሱላቸው ።
________
እኛ ጋር ያሉትማ….. ቲጃኒዎች መስጂድ ሄደው አንገት ለአንገት ተቃቅፈው ፎቶ ይነሳሉ ፤ ቪዲዮ ተቀርፀው በቻናል ይለቃሉ
' በርቱ! እናንተ እና እኛ መካከል ልዩነት የለም አሕለል ሱና ናቹ!' ብለው ከች ይላሉ
ወይ ደሞ እንደሻንጣ ተሸካሚዎቹ (ባለሂክማዎች) አርደውና ሩዝ ቀቅለው አብረው በልተው ይመለሳሉ
ብቻ ሆድ ይፍጀው ፤ ለማንኛውም ወንድሞቼ እህቶቼ በሽርክ እና ቢድዓ ላይ ያለ ወንድማቹም ይሁን እህታቹ እናታቹም ትሁን አባታቹ ወደ ተውሂድ ከመጥራት ወደኋላ አትበሉ
________
1) ቲጃኒዎች አደገኛ የሱፊያ ጦሪቃ ተከታዮች ሲሆኑ በብዛት የሚገኙት በምዕራብ አፍሪካና እኛም ሃገር ወደ ሰሜም አካባቢ ነው። ከብዙ ዓመታት በፊት አሕመድ ቲጃኒ በሚባል ግለሰብ በ1815 የተፈለሰፈ አንጃ ሲሆን ፤ ብዙ ቢድዓ ኹራፋት እና ኩፍሪያት ያዘሉ ቃላቶች ይናገራሉ ይተገብራሉም
ለአብነት ያክል
- ወሊዮች ፣ ሷሊሆች ፣ መልዒካዎችን ከጭንቅ እንዲያወጧቸው ይለምናሉ
- መውሊድን በድምቀት የሚያከብሩ ሲሆን በክብረበዓሉም ላይ ረሱል ከአራቱ ኸሊፋዎች ጋር መጥተው ይዘይሩናል ይላሉ ለዚህም ሲሉ የሚዘክሩበት ቦታ ላይ ባዶ ቦታ በመተው ነጭ ጨርቅ ያስቀምጣሉ ። ለነርሱ ብለው :: (ይሄን የኢኽዋኑ መስራችም ሃሰነል በናም የሚለው ነው)
- ወሊዮች መዕሱም (ወንጀል) ስህተት የማይፈፅሙ ናቸው ብለው ያምናሉ (በአሕለል ሱና አቋም መሰረት ከስህተት የራቁት አንቢያዎች ብቻ መሆናቸው ልብ ይበል)
የአንጃው መስራች የሆነው አሕመድ ቲጃኒ እንዲህ ይላል ...
- የውመል ቂያማ ሸፋዕ (ምልጃ) የሚገኘው በርሱና በተከታዮቹ ብቻ ሲሆን ፤ እርሱንም የዘየረ (በተለይ በአርብና ሰኞ) ምልጃውን ያገኛል ካፊርም ሰው ቢሆን
- የነሱ ሰላተል-ፋቲህና ጀውሃራቱል-ከማል የሚባለውን የፈጠራ አዝካር ማለት ስድስትሺህ (6000) ጊዜ ቁርዓንን ከማክተም ይበልጣል ይላሉ

ወዘተ......
______
አላህ ከጥመት ይጠብቀን
ሃቁን ተናግረን ሰውን ወደ ተውሂድ የምንጠራ ያድርገን !!