Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አልከሶ ለመሄድ ከተሰናዳክ አሊያም ቤተሰቦችክን ገንዘብ ሰጥተክ ወደዚህ ቦታ ለመሸኘት ከተነሳክ ለማንኛውም ቦታው ላይ አላህ ያወገዛቸው ምን ምን ነገራቶች እንደሚከናወኑ ፍንጭ ልስጥክ አድምጠኝ!!


Abubeker Siraj

አልከሶ ለመሄድ ከተሰናዳክ አሊያም ቤተሰቦችክን ገንዘብ ሰጥተክ ወደዚህ ቦታ ለመሸኘት ከተነሳክ ለማንኛውም ቦታው ላይ አላህ ያወገዛቸው ምን ምን ነገራቶች እንደሚከናወኑ ፍንጭ ልስጥክ አድምጠኝ!!
• #ከአልከሶ_መስጊድ_ምሰሶ_ስር_ይፈልቅ_የነበረን_ውሃ_ዘምዘም_ነው_ብሎ_በማመን_በረካና_ፈውስ_መፈለግ
ግጭት ቁ.1 ዘምዘም ውሃ የሚገኘው በመካ ከተማ በተከበረው አላህ ቤት አቅራቢያ እንጂ ስልጤ ክልል አይደለም ፤ በረካም የሚፈለገው ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም
(( ኑሕ ሆይ ከኛ በሆነ ሰላም ባንተ ላይና አንተም ጋር ባሉት ሕዝቦች (ትውልድ) ላይ በሆኑ በረከቶችም የተጎናጸፍክ ሆነህ ውረድ)) ሁድ #48
#በአልከሶ_መስጊድ_ግቢ_ውስጥ_የሚገኝ_ቀብር_ዘንድ_ሄዶ_እገዛና_እርዳታ_መጠየቅዕርዳታ የሚጠየቀው ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምዘወትር በቀን በትንሹ አስራሰባት ጊዜ ፋቲሃ ላይ የምንለው ለዚህ መልስ ነው(( አንተን ብቻ እንገዛለን አንተን ብቻ ዕርዳታ እነጠይቃለን)) ፋቲሐህ #5
• #አፈሩንም_ቆንጥሮ_ወደቤት_በመውሰድ_ለቤተሰብ_በማስቃም_በረካን_መፈለግ በረካ የሚሰጠው አላህ እንጂ የቀብር አፈር አይደለም(( (ኢሳም አለ) በየትም ስፍራ ብኾን ብሩክ አድርጎኛል)) መርየም #ሰላሳአንድ
• #ጊስቲ_ተብለው_የሚጠሩ_አሮጊት_ዘንድ_ቀርቦ_እየዘየሩ_ሃጃቸውን_የቸገራቸውን_ነገር_በማቅረብ_እገዛ_መጠየቅ ጉዳይን የሚያስፈፅመው ችግር እንዲያስወግድልን ዕርዳታ የሚጠየቀው አላህ ብቻ ነው((ወይም ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል መከራንም የሚያስወግድ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋችሁ፤ (ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሠጹም። )) አል፡ነምል ስድሳ ሁለት
#በአሁኑ_ወቅት_የሚገኙት_የአልከሶ_ወራሽ_ዘንድ_ሃጃቸው_ለማስፈጸም_ብር_ጨብጦ_ወረፋ_ይዞ_በመግባት_በእንብርክክ_ወደሳቸው_ቀርቦ_ልክ_ስጁድ_ያህል_በማጎንበስ_እጃቸውን_ለአፍታ_ስሞ_መውጣትስለት የሚገባውም ዕርዳታ የሚጠየቀውም ሱጁድ የሚገበደድለትም አላህ ብቻ ነው«ስግደቴ፣ መገዛቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡ አንዓም#162
• #በማንኛውም_አጋጣሚና_ወቅት_በአልከሶ_ቀብር_ሲታለፍ_አጥሩን_ልክ_እንደ_ኩፋሮች_ሶስት_ጊዜ_መሳም (( ረሱል ሰላላሁአለይሂወሰለም « ከከሃዲዎች ጋር የተመሳሰለ ከነርሱ ነው» ))
• #ዝናብ_በሚጠፋበት_ወቅት_የየአካባቢው_ሰዎች_በጋራ_ሰንጋ_እየነዱ_ወደ_አልከሶ_በመሄድ_የዝናብ_ተማጽኖ_የሚያቀርቡ_ሲሆን_በምላሹም_በቃሂዱ_ነገ_ይዘንባል_በሚል_ምላሽ_ቃል_ተገብቶላቸው_የሚመለሱ_መሆኑ..ዝናብ የሚለመነው አንድ አላህ ብቻ ነው ዕርድም የሚገባው እርሱ ብቻ ነው(( ስለዚህ ለጌታህ ስገድ፤ (እርድ) ሠዋም (ለርሱ ብቻ) )) ከውሠር #2
• #አልከሶ_መውሊድ_እንዲሁም_ከአልከሶ_መውሊድ_ወቅት_እና_ቦታ_ውጪ_አስደንጋጭ_የሆነ_ጩኸት_አደጋና_ሁከት_በሚያጋጥምበት_ቅጽበት_ፈይዲ_አልከሶ_ጌቶች_ሰይዲ_ በይዲ_የሚሉ_የአድኑኝ_ተማጽኖ_ጥሪዎችን_ማሰማት_መማጸንድረስልኝ የምንለው አላህን ብቻ ነው((ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፤ ቢሰሙም ኖሮ ለናንተ አይመልሱላችሁም)) ፈጢር #14
• #በጌቶች_እና_የመሳሰሉ_ስሞች_መማል (( ረሱል ሰላላሁአለይሂወሰለም «ከአላህ ውጪ ባለ ፍጡር የማለ በርግጥ አጋርቷል»))
#ልጅ_ሃብት_ጤንነት_እና_የመሳሰሉ_ነገሮችን_በመፈለግ_እንስሳ_ገንዘብ_እህል_ቡና_ቅቤ_የመሳሰሉ_ነገሮችን_ለማስገባት_መሳልና_ስለትን_መሙላት (( የዒምራን ባለቤት (ሐና) «ጌታዬ ሆይ፦ እኔ በሆዴ ውስጥ ያለውን (ፅንስ ከሥራ) ነጻ የተደረገ ሲኾን ለአንተ ተሳልኩ፡፡ ከእኔም ተቀበል አንተ ሰሚው ዐዋቂው ነህና»ጊዜ (አስታውስ) )) ዒምራን #35_____________#ዕወቅ_ወንድሜአላህ ቤተሰቦችክን በጀነት እንዲያኖራቸው ከፈለግክ ከዚህ ስፍራ መሄድን እንዲቆጠቡ አሁኑኑ አድርግ (አልረፈደም)ይሄን መረጃ አልከሶ ቦታው ድረስ በመሄድ ዱዓቶችንና ከዚህ (ከ አልከሶ) በተሰብ ወደ ሱና የተመለሱ ሰዎችን ጠይቆ መረጃ ያቀበለኝን ወንድሜ ኡመር ኢብኑ ኡመር አላህ እጥፍ ድርብ ምንዳ ይሸልምልኝ ::____________ አላህ ቤተሰቦቻችንን ወደ ተውሂድ ይምራልን ፤ ባለማወቅ የሚያደርጉትንም ሂዳያ ይስጣቸው ፤ ለሽርክና ቢድዓ ጥብቅና የሚቆሙትን አላህ ሂዳያ ይስጣቸው