Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አንተ ወጣት ሆይ ቀብር ውስጥ ጌታህ ማነው እንጂ ተብለክ የምትጠየቀው ፖለቲካ አይደለም


       Abubeker Siraj  
ታላቁ ኢትዮጵያዊው ዓሊም አል- አላማ ሸኽ ዱክቶር ሙሃመድ አል አማን አል ጃሚ ረሂመሁላህ
« አንተ ወጣት ሆይ ቀብር ውስጥ ጌታህ ማነው እንጂ ተብለክ የምትጠየቀው ፖለቲካ አይደለም !! »
ታላቁ ኢትዮጵያዊው ዓሊም አል- አላማ ሸኽ ዱክቶር ሙሃመድ አል አማን አል ጃሚ ረሂመሁላህ
“ .. በሚያሳዝን ሁኔታ በአሁን ሰዓት አንዳንድ ተማሪዎች (ወጣቶች) የፖለቲካን ትርጉም እንኳን ሳያውቁት እራሳቸውን በፖለቲካ ቢዚ አድርገዋል
እራሳቸውን ቢዚ አድርገዋል ።
ዕውቀትን መፈለግ ያሻው ሰው
ሙሉ በሙሉ ፊቱን ከፖለቲካ ውጥረት (እንቅስቃሴ) ማራቅ ይኖርበታል ።
ቀለል ያሉ ኪታቦችን በመሸምደድ (በቃል በመያዝ) መጀመር ይኖርበታል
ከዑሱሉ ሰላሳ ይጀምር እናም እንዲህ ለሚሉት ለፖለቲካ አንቀሳቃሾች ትኩረት መስጠት አይገባውም
ዕወቅ የ አላህ ዕዝነት አንተ ላይ ይሁን እስከመቼ?
እስከምትሞት ይህን ቃል በላቸው
የሞትክ ጊዜ ቀብር ውስጥ ስታላግጥ ስለነበረበት ነገር ትተየቃለክ
- ጌታክ ማነው?
- ዕምነትክ (ዲንክ ምንድነው)?
- ነቢይክ ማነው?
በሕይወት እያለክ በዚህ አፊዘካል ፤ ስትሞትም ስታላግጥ ስለነበረበት ነገር ትተየቃለክ
መጀመሪያ የምትተየቀው (ቀብር ውስጥ) የዑሱሉ ሰላሳን ትርጉም ነው
ለዚህ የጥፋት (ፖለቲካዊ) እንቅስቃሴ ትኩረት አት ስጥ
ተውሂድን ያዘለውን ይህን አነስተኛ ኪታብ ሸምድ ድ ፤ የተውሂድን ቃላቶች ደንቦቹን ፣ ክንውኖቹን (ዕወቅ)
ነዋቂደል ኢስላም (እስልምናን የሚያፈርሱ)
አል ቀዋዒደል አርበዓ (አራቱ መርሆች)
እነዚህን ልክ እንደ ፋቲሃ ሸምድድ
ከዚያም እንዲያብራሩልክና እንድትረዳው ወደ ዕውቀት ፈላጊዎች (ዓዋቂዎች) ሂድ
ዕርግጠኛ ነኝ ዑሱሉ ሰላሳን የተረዳ አንድ ተማሪ ወደ አረብ ያልሆኑ አገራት ቢላክ (በሰዎች ዕይታ) ኢብኑ ተይሚያህ ይሆናል ፤
በዑሱሉ ሰላሳ ይህ ነው ከዚህ ቀደም የተከሰተው
ይህን (ዑሱሉ ሰላሳ) ሸምድ ደክ ብትረዳውና በ አፍሪካያዊዎችና በ ኤሲያዊያን መካከል ቆመክ ብታስተምር ፤ አንተ እዛ ቦታ ላይ ኢብኑ ተይሚያ ነክ
ነገር ግን ለ አላህ ምስጋና ይገባው አሁን ልጆቻቸው ም እየሸመደዱት ነው ፤ ነገር ግን የሚያብራራላቸው ሰው ይፈልጋሉ
ወደጥፋት አይምሩክ (ፖለቲከኞች)
እነዚህ (በዕውነት) የማይመክሩክ (ፖለቲከኞች) ወደ ጥፋት እንዲመሩክ ቦታ አትስጣቸው
እንዚህን መፅሃፎች ሸምድ ድ
- ኪታቡ ተውሂድ
- አል - በይቁኒያ
- አል- አርበዒን አነወዊያ
እነዚህ ኩቱቦች ናቸው ፤
አንተ እራስክን (በፖለቲካ) ቢዚ ታደርጋለክ ፤ ነገር ግን የሕንድ ልጆች ፣ የፓኪስታን ፣ የ አፍሪካ እነዚህን መፅሃፍት እየሸመደዱ ነው ።
የአፍሪካ ልጆች ዕሱሉ ሰላሳ ፣ ከሽፉ ሹቡሃት ፣ ኪታቡ ተውሂድ ፣ አርበዒን አነወዊያን በዚህ ሁለት ጆሮዬ ሰምቻለው
የመማሪያ ክፍላቸው ገብቼ ቆሜ እነዚህን መፅሃፍት ልክ እንደፋቲሃ ሲሸመድ ዱ አዳምጨያቸዋለው
ይህም የሆነው የፖለቲካ አራማጆች እዛ ቦታ ስላልደረሱ ነው ፤ (ልጆቹ) ፊጥራ (የተፈጥሮ ይዘታቸው) ላይ ናቸው ።
አላህ ሱብሃነሁወተዓላን ብዙ ወጣቶች ካጠቃውን (የፖለቲካ እንቅስቃሴ) እነዚህን ልጆች እንዲጠብቃቸው እለምነዋለው
ስለዚህም እነዚህን መፅሃፍቶች ሸምድ ዱ
ከዚያም ዑለማዎችና አንዳንድ ተማሪዎች ጋር ሂዱ (እንዲያብራሩላቹ)
ከዚያም በደንብ ወደ ተብራሩትና ከፍ ወዳሉት መፅሃፍት ትሽጋገራላቹ
ከትናንሽ ጉዳያዊ መፅሃፍቶች ጀምሩ ከዚያም ከፍ ወዳሉት መፅሃፍቶች ተሸጋገሩ ፤ ይህ ንግ ግር ልክ ከሆነ
እንዲህ ነው የአንድ ዕውቀት ፈላጊ አካሄድ
አካባቢው ላይ ስላሉት (የፖለቲካ) እንቅስቃሴዎች ትኩረት አይስጥ
አንዱ ለግሉ እንዲህ ሊል ይችል ይሆናል ፤
ይህ ማለት ከዓለም ተገልለን እንድንኖር ነው እንዴ የምትፈልጉት ? ስለተጨባጭ መረጃ ምንም ዕውቀት ላይኖረን ነውን?
ለተጨባጭ መረጃ ፤ (የፖለቲካ ያልሆነን) ራዲዮን አድምጥ ፣ አንዳንዴም ጋዜጣን አንብብ
ተጨባጭ መረጃዎች አንተ ወደ ቤትክ በእግርክ ስትጓዝም ይደርስካል ፤ ወይንም በመኪና እየሄድክ ይደርስካል
በዚህ ላይ እራስክን አታጨናንቅ ፤ (ዲንክን) ተማር ፣ ዕውቀት ላይ አተኩር ።
https://www.youtube.com/watch?v=sRWtEWFZ0L0