Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የኢኽዋን ምሽጎችን ማንኮታኮት (ተከታታይ፣ ክፍል-2)

የኢኽዋን ምሽጎችን ማንኮታኮት
(ተከታታይ፣ ክፍል-2)
ለነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሱና ተገቢውን ክብር የማይሰጡ ኢኽዋንዮች ሰሒሕ ሐዲሦችን ወደ ኋላ በማሽቀንጠር የኸዋሪጅን መንገድ እንደ አዲስ ማስተዋወቅ ይዘዋል፡፡ ከነዚህ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ውስጥ ጥፉ አካሄዳቸውን የሚነቅፍን ሁሉ የሚያከፍሩና ዑለማዎችን የሚያብጠለጥሉ፣ ያለምንም ጥንቃቄ በጅምላ የሚያከፍሩም አሉ፡፡ በመሪዎች ላይ መቀስቀስና ማመፁንማ እንደ ንቃት ነው የሚቆጥሩት፡፡ ከነሱ አልፈው በርካታ አላዋቂ የሆነውን ሙስሊም በዚህ ቆሻሻ የኸዋሪጅ አመለካከት እየበከሉት ነው፡፡ ትላንት “መሪዎችን በቃላት መተቸት ችግር የለውም” ሲሉ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ ከፍ ብለው “በመሳሪያም መዋጋት ይቻላል” እያሉ ነው፡፡ ነብዩ ዐለይሂሰላም ግን እነዚህ ዘመናዊ ኸዋሪጆች እንደዲን የያዙትን ነገር አስመልክተው ለሱናቸው ዋጋ ለሚሰጥ ግልፅና የማያሻሙ በርካታ መልእክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ የተወሰኑትን በክፍል አንድ ስላሳለፍን የፈለገ በዚህ ሊንክ ገብቶ ማየት ይችላል፡፡ https://www.facebook.com/photo.php?fbid=724982540906553&set=a.294190613985750.68152.100001844423938&type=1&theater
‪#‎ኢኽዋናዊ_ማምታቻዎችና_መልሶቻቸው‬
የሙብተዲዖች አንዱ መገለጫ ማሰረጃዎችን መልእክታቸውን እየጠመዘዙ በሚፈልጉት መልኩ ማቅረብ እና ደካማ ትውፊቶችን ሳያጣሩ መጠቀም ነው፡፡ ዘመናዊ ኸዋሪጆችም በመሪዎች ላይ ለማመፅና ይህን አመለካከታቸውን የሚቃወሟቸውን ባስቀያሚ ቃላት ለመወረፍ ግፋ ሲልም ለማክፈር ወደ ኋላ እንደማይሉ በተጨባጭ እያየን ነው፡፡ ለዚህ ብልሹ አካሄዳቸው የሚጠቀሟቸውን ጥቂት “ማስረጃዎችን” እንመልከት
1. “ከጅሃድ ሁሉ በላጩ ጨቋኝ መሪ ፊት ሀቅን መናገር ነው፡፡”
ይሄ ሐዲሥ ኸዋሪጆቹ እንደሚያራግቡት በመሪ ላይ ሰይፍ መምዘዝን አያመላክትም፡፡ ምክኒያቱም
1.1. ሐዲሡ “ ‪#‎ከጨቋኝ‬” ነው የሚለው፡፡ እነሱ ግን ፍትሃዊ የሆነው የነብዩ ዐለይሂሰላም ኸሊፋም አያረካቸውም፡፡ ኸዋሪጆች የነብዩን ዐለይሂሰላም ምርጥ ኸሊፋዎች ዑሥማንና ዐልይን የገደሉ ናቸው፡፡ ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን ረዲየላሁ ዐንሁ በጀነት የተመሰከረለት፣ ቀድመው ኢስላምን ከተቀበሉት በመሆኑ ብዙ ግፍ ያስተናገደ፣ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሁለት ልጆቻቸውን የዳሩለት፣ ከአራቱ ምርጥ ኸሊፋዎች አንዱ ነው፡፡ በዘመናችን የዚህ የኸዋሪጅ አደገኛ በሽታ ዋና ሞተር የሆነው ሰይድ ቁጥብ በዑሥማን ላይ የተነሱ ሙናፊቆችን “ለኢስላም ሩሕ የቀረቡ ናቸው” ብሎ ነው ያሞካሻቸው፡፡ የኡስማን ረዲየላሁ ዐንሁ የኺላፋ ዘመን በሶስቱ ኸሊፋዎች ዘመን ውስጥ የገባ ክፍተት እንጂ የእውነት የነገሰው እሱ ሳይሆን መርዋን ነው፤ ዑስማን በስልጣኑ ተከልሎ የሙስሊሙን ገንዘብ ያላግባብ የተጠቀመ፣ ለዘመዶቹ እያዳላ የነብዩን ወዳጆች ያራቀ፣ ኸሊፋ ሊሆን በማይገባው እድሜ ስልጣን ይዞ የመርዋን መጫወቻ የሆነ፣ አገዛዙ ከኢስላም ሩህ የራቀ ነበር ይላል፡፡(አልዐዳለቱልኢጅቲማዒያህ፡ 160-186) እንግዲህ ተመልከቱ፡፡ ታላቁን ኸሊፋ ዑሥማንን እና ዘመነ-ኺላፋውን በዚህ መልኩ የሚገልፅ እንዲሁም ለንዲህ አይነት ጠሞ አጥማሚ በጭፍን የሚሟገት ሰው ምን አይነት መሪ ነው የሚያረካው?
1.2. ሐዲሡ ከመሪው “ ‪#‎ፊት‬” ነው የሚለው፡፡ እንጂ በሌለበት አይደለም፡፡ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡ “በስፋት የተንሰራፉ ጥፋቶችን መቃወም ተፈላጊ ነገር ነው፡፡ ምንም ችግር የለበትም፡፡ ነገር ግን በመሪ ላይ መቃወምን በተመለከተ ለምሳሌ አንድ ሰው መስጂድ ውስጥ ተነስቶ “መንግስት በደለ፣ እንዲህ ሰራ” እያለ የሚተቻቸው ሰዎች ‪#‎በሌሉበት‬ በመሪዎች ላይ በዚህ መልኩ ባደባባይ ቢናገር - (ይሄ ነገር አይፈቀድም፡፡) አሚሩ ወይም ገዢው ከፊት ለፊትህ ሆኖ መናገርና በሌለበት መናገር ‪#‎ልዩነት‬ አለው፡፡ ምክኒያቱም ከሰለፎች የመጡት በመሪዎች ላይ የተደረጉት ተቃውሞዎች በሙሉ ከአሚሩ ወይም ከገዢው ፊት የተፈፀሙ ናቸውና፡፡” (ሊቃኣቱልባቢልመፍቱሕ፡ 62/14)
1.3. ሐዲሡ ባደባባይ በመቀስቀስ መሪና ህዝብን ሆድና ጀርባ ለማድረግ የሚውልም አይደለም፡፡ እንዲያ ከሆነማ “ ‪#‎መሪን_በሆነ_ጉዳይ_ሊመክር_የፈለገ‬ ‪#‎በግልፅ_አያውጣው‬፡፡ ‪#‎ይልቁንም_እጁን_ይዞ‬ ‪#‎ገለል_አርጎ_ይንገረው‬” የሚለውን የነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አስተምሮ ምን ልናደርገው ነው?
1.4. ከዚያ በተረፈ ሐዲሡ የሚለው “ሀቅን ‪#‎መናገር‬” እንጂ ሰይፍ መምዘዝ አይደለም፡፡ ይስተዋል! “ከጅሃድ ሁሉ በላጩ ጨቋኝ መሪ ፊት ሀቅን መናገር ነው” ያሉት ነብይ ናቸው እኮ “ግልፅ ክህደት ካላያችሁ እንዳትወጡ” ያሉት፡፡ ይህን ሐዲሥ የተናገሩት ነብይ ናቸው እኮ “ጀርባህ ቢመታም ገንዘብህ ቢነጠቅም ታገስ”፣ “አድሎ ቢፈፀምባችሁም ታገሱ” ያሉት፡፡ የምን እየመረጡ መውሰድ ነው? ነብዩማ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አይደለም ጦር መስበቅ ቀርቶ ከዚያም በቀለለ “ ‪#‎መሪዎቻችሁን_አትሳደቡ‬‪#‎አታታሏቸውም‬‪#‎አትጥሏቸውም‬፡፡ አላህንም ፍሩ ‪#‎ታገሱም‬፡፡ (የአላህ) ውሳኔው ቅርብ ነው” ነው ያሉት፡፡ (አስሱናህ ሊብኑ አቢ ዓሲም)
1.5. ደግሞም ሐዲሡ የሚለው “ ‪#‎ሀቅን‬ መናገር” ነው፡፡ ኢኽዋኖች ግን በውሸት የተካኑ ቆርጦ ቀጥሎች ናቸው፡፡ “ ‪#‎ሰልፋችንን_ሊደግፍ_ጂብሪል_ወረደ‬!” “ ‪#‎አላህን_አየነው‬” የሚሉ ሀፍረተ-ቢሶች በሚነዟቸው ውንጀላዎች ላይ የሚታመኑ አይደሉም፡፡
2. ሌላው ዘመናዊ ኸዋሪጆች በመሪ ላይ ማመፅ ሸሪዐዊ መሰረት እንዳለው ለማስመሰል ከሚያቀርቧቸው “ማስረጃዎች” “ወደፊት ሪዝቆቻችሁን የሚቆጣጠሩ መሪዎች ይሾሙባችኋል። ሲናገሯችሁ ይዋሻሉ። ሲሰሩም ስራውን ያበላሻሉ። አፀያፊ ተግባራቸውንም ጥሩ ነው እስካላላችኋቸው ድረስ አይደሰቱባችሁም። ውሸታቸውንም እስካላመናችሁ ድረስ አይደሰቱባችሁም። ድንበርን ባለፉ ጊዜ ወደው እስከተቀበሉ ድረስ ሀቅን ስጧቸው። በዚህ ሁኔታ የሚገደል ሰውም ሸሂድ ነው” የሚለው “ሐዲሥ” ነው፡፡
መልስ፡- ነገር ግን “ሐዲሡ” ዶዒፍ ነው፣ ደካማ፡፡ የታላቁን ሙሐዲሥ ሸይኹልአልባኒን ረሒመሁላህ ብይን “ሶሒሕ ወዶዒፍ አልጃሚዑስሶጊር፡ 3255 እና 6999 ላይ ይመልከቱ፡፡
3. ሌላኛው ማምታቻቸው “ዑመር /ረዲየላሁ ዐንሁ/ ኸሊፋ ሆኖ ሲመረጥ ሚንበር ላይ ወጥቶ “መልካም የምሰራ ከሆነ አግዙኝ፣ መጥፎ ከሰራሁ ደግሞ አስተካክሉኝ” ሲሉ አንድ ሰው ተነሳና “አንተ ላይ ጥመት ካየንብህ በሰይፋችን ነው ምናቃናው” አለ። ከዚያም ዑመር “ከሙሀመድ ኡመት ውስጥ ዑመርን በሰይፍ የሚያቃና ሰው ላኖረ አላህ ምስጋና ይገባው” አለ” የሚለው ቂሷ ነው፡፡
3.1. በመጀመሪያ ቂሳው ደካማ ነው፡፡ ደካማ “ማስረጃዎችን” መነሻ እያደረጉ ሰሒሕ ሐዲሦችን ዋጋ ለማሳጣት መጣር የስሜት ተከታዮች መታወቂያ ነው፡፡ ኢኽዋኖችም እያደረጉ ያሉት ይሄንኑ ነው፡፡ ለሚያራግቡት ባጢል ደካማ ትውፊቶችን ማስተዋወቅ፡፡ ይሄ ቂሳ ሶሒሕ እንዳልሆነ፣ ሰሒሑ ይሄ ሳይሆን ሌላ እንደሆነና መልእክቱም እነሱ እንደሚያራግቡት እንዳልሆነ በዚህ ሊንክ ገብተው ይመልከቱ፡፡ http://www.sahab.net/forums/?showtopic=118565
3.2. እንዳውም ከዑመር የተገኘው ሶሒሕ ማስረጃ ከዚህ በተቃራኒ ነው፡፡ ሱወይድ ኢብኑ ገፈላህ ረሒመሁላህ ዑመር ኢብኑልኸጣብ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብሎኛል ይላል፡ “የኡመያህ አባት ሆይ! ከኔ በኋላ ከቆየህ የሐበሻ ባሪያ ቢሆን እንኳን መሪውን ታዘዝ፡፡ ቢመታህም ታዘዝ፡፡ በሆነ ጉዳይ ቢያዝህም ታገስ፡፡ ሐቅህን ቢከለክልህም ታገስ፡፡ ቢበድልህም ታገስ፡፡ ዲንህን በሚያጓድል ነገር ቢያዝህ ግን “ህይወቴ ከዲኔ በታች ነው” በለው (ቢገድልህም በጥፋት እንዳትታዘዘው)፣ (ከጥፋቱ ውጭ ባሉ ነገሮች ላይ ግን) “ሰሚ ነኝ” ታዛዥ ነኝ” በለው፡፡ (አስሱነኑልኩብራ፡ 16628)
4. በመሪዎች ላይ የተነሱትን የነሑሰይንነና ኢብኑዙበይርን ድርጊት ማጣቀሻ መጠቀምም አያዋጣም፡፡ ምክኒያቱም፡
4.1. ጌታችን አላህ (እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ታዘዙ፡፡ መልእክተኛውንና ከናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ በማንኛውም ጉዳይ ብትከራከሩ፣ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ከሆናችሁ፣ (የተከራከራችሁበትን ጉዳይ) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው) ይላል፡፡ (አንኒሳእ፡ 59) መልካም! ስለዚህ እንደ አማኝ የምንወዛገብበትን ይህን ጉዳይ ወደ አላህና ወደ መልእክተኛው እንመልሰው፡፡ ወደ አላህ ስንመልስ አሁን ባሳለፍነው አንቀፅ ውስጥ (የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ) ይላል፡፡ ወደ መልእክተኛው ስንመለስ መሪዎቹ ቢበድሉም፣ ከኩፍር በታች ባለ ቢያምፁም፣ ገንዘብህን ቢበሉብህም፣ ጀርባህን ቢመቱህም፣ ከወንጀል ውጭ ባለ ነገሮች “ስማ፣ ታዘዝ”፣ “በነሱ ላይ አታምፅ” ነው የሚሉት ሐዲሦቻቸው፡፡ ምንም እንኳን አንዱ ቢበቃም ሐዲሦቹ አንድ ሁለት፣ ወይም አምስት ስድስት አይደሉም፡፡ በአስር የሚቆጠሩ እንጂ፡፡ የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲሥ ከቀረበ በኋላ ደግሞ የማንም የተለየ ሀሳብ ዋጋ አይኖረውም፡፡ ከነብዩ ሱና ጋር ከተጋጨ ሌላው ቀርቶ የነአቡበክርና የነዑመርም ትውፊት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ኢብኑ ዐባስ “ከሰማይ ድንጋይ ልትዘንብባችሁ ይቀርባል! እኔ 'የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ' እላለሁ እናንተ ግን 'አቡበክር እንዲህ ብሎ' 'ዑመር እንዲህ ብሎ' ትላላችሁ" በማለት ሐዲሥ እየተጠቀሰ ሌላው ቀርቶ እነ አቡበክርን እንኳን ማጣቀሱ አደጋ እንዳለው አስፈሪ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡ የመልእክተኛውን ትእዛዝ የማያከብር አደጋ ይከተለዋል፡፡ (እነዚያ የመልእክተኛውን ትእዛዝ የሚጥሱ ሰዎች ፈተና ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳታገኛቸው ይጠንቀቁ)፡፡ (አነኑር፡ 63) ታዋቂው የቁርኣን ተንታኝ አልኢማም ኢብኑ ከሢር ረሒመሁላህ ይቺን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፡ “የማንም ንግግሮችና ተግባሮች የሚመዘኑት በሳቸው (በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ንግግሮችና ተግባሮች ነው፡፡ ከሳቸው ጋር የተስማማ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ከሳቸው የሚለይ ግን በተናጋሪው ወይም በሰሪው ላይ ተመላሽ ይሆናል፡፡ ማንም ይሁን ማንም!!” ቀድሞ ነገር ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ውጭ ፍፁም (መዕሱም) የሆነ አለ እንዴ? የሳቸውን ንግግር ጥሎ ውዝግብ የበዛባቸውን ፍፁም ያልሆኑ ሰዎችን አሻሚ ተግባራት ማንሳት የጤና ነው? ነው ወይስ ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ውጭ ወሕይ የሚደርሰው አለ? ሱብሓነላህ!!
4.2. እነኚህ ከሑሰይንና ኢብኑዝዙበይር የተገኙት ክስተቶች ‪#‎ግፋ_ቢል‬ “ሙተሻቢህ” ነው የሚሆኑት፡፡ መሪዎች ቢበድሉም በነሱ ላይ እንዳትነሱ የሚሉት በርካታ ሐዲሶች ግልፅ መልእክት ነው ያዘሉት፡፡ ሙሕከም ናቸው ማለት ነው፡፡ ሙሕከም የሆኑ ማስረጃዎችን ጥለው ሙተሻቢህ ላይ የሚንጠለጠሉት ደግሞ የጥመት፣ የስሜትና የብጥብጥ ሰዎች ናቸው፡፡ ኣሊ ዒምራን፡ 7 ይመልከቱ፡፡ “ከቁርኣኑ (ሙሕከሙን ጥለው) የሚመሳሰለውን (ሙተሻቢሁን) የሚከተሉትን ካያችሁ እነሱ ናቸው አላህ (ልቦቻቸው ላይ ጥመት ያለባቸው ሲል በቁርኣኑ) ያነሳቸው፡፡ ተጠንቀቋቸው!!” ይላሉ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም) መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከኢስላም እስካልወጡ ድረስ በመሪዎች ላይ ማመፅን በበርካታ ሐዲሶች ከልክለዋል፡፡ እንደመፍተሄ ያስቀመጡት ሶብር እንጂ ሰይፍ አይደለም፡፡ ጥቂት ሐዲሶቻቸውን እንመልከት፡፡
=1= “ከመሪዎቻችሁ ምርጦቹ እነዚያ የምትወዷቸውና የሚወዷችሁ፣ ዱዐ የሚያደርጉላችሁና ዱዐ የምታደርጉላቸው ናቸው፡፡ መጥፎ መሪዎቻችሁ እነዚያ የምትጠሏቸውና የሚጠሏችሁ፣ የምትረግሟቸውና የሚረግሟችሁ ናቸው” አሉ፡፡ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ‪#‎በሰይፍ_እንፋለማቸው‬?” ሲሉ “ ‪#‎በጭራሽ‬! በናንተ ዘንድ ሶላት እንዲሰገድ እስካደረጉ ድረስ፡፡ በናንተ ዘንድ ሶላት እንዲሰገድ እስካደረጉ ድረስ፡፡ ‪#‎አዋጅ‬! በሱ ላይ ሹም የተሾመበት ሰው በሆነ ነገር አላህን ሲያምፅ ካየው የሚፈፅመውን በአላህ ላይ ማመፅ ይጥላ፡፡ ‪#‎ከታዛዥነት_ግን_እንዳያፈነግጥ‬፡፡” (ሙስሊም፡ 1855) ማስረጃ ለሚያከብር ሰው ይሄ ሐዲሥ ብቻ በቂው ነበር፡፡
=2= “ከአሚሩ የሆነ የሚጠላው ነገር ያየ ሰው ይታገስ፡፡ ከጀማዐ ስንዝር ታክል አፈንግጦ የሞተ ሞቱ የጃሂሊያ ሞት ነው፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም)
=3= ሶሐቦች “ሐቃቸውን የሚጠይቁን ‪#‎ሐቃችንን‬ ግን ‪#‎የሚከለክሉን‬ መሪዎች ካገኙን ምን እናርግ?” ብለው ነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲጠይቁ “‪#‎ስሙ‬ ‪#‎ታዘዙ‬!! በነሱ ላይ የተጣለባቸው ሀላፊነት አለ፡፡ በናንተም ላይ የተጣለባችሁ ሀላፊነት አለ” በማለት መለሱ፡፡ (ሙስሊም የዘገቡት)
=4= “ከኔ በኋላ ‪#‎በመመሪያየ_የማይመሩ‬‪#‎በሱናየም_የማይጓዙ‬ መሪዎች ይመጣሉ፡፡ በነሱም ላይ ‪#‎ልቦቻቸው_የሸይጧን‬ ‪#‎አካላቸው_ደግሞ_የሰው‬ የሆኑ ሰዎች ይነሱባቸዋል” አሉ፡፡ ሁዘይፋ ረዲየላሁ ዐንሁ “እንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ከደረስኩኝ ምን ላድርግ?” ሲላቸው “አሚሩን #ትሰማለህ፣ ለሱም #ትታዘዛለህ- #ጀርባህ_ቢመታም #ገንዘብህ_ቢነጠቅም እንኳን” አሉት፡፡ (ሙስሊም የዘገቡት)
=5= “ዑባዳህ ኢብኑስሳሚት ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፡- “ሲከብድም ሲቀልም፣ ሲደላም ሲከፋም፣ #አድልዎ_ሲፈፀምብንም #ልንሰማና_ልንታዘዝ፣ እንዲሁም ስልጣንን ከባለቤቱ ላንሞግት፣ የትም ብንሆን ሐቅን ልንናገር፣ በአላህ ላይ የወቃሽን ወቀሳ ላንፈራ ለአላህ መልእክተኛ ቃልኪዳን ገብተናል፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም)
ያስተውሉ! መሪዎች ላይ ጥፋቶቻቸው ተሻጋሪ ሆኑም አልሆኑም ኩፍር (ክህደት) እስካልደረሱ ድረስ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ማንም በነሱ ላይ በሰይፍ እንዲነሳ አልፈቀዱም፡፡ ሐዲሣቸውን በጥሞና ተመልከቱ፡- “ከአላህ አስተማማኝ ማስረጃ ያላችሁ ግልፅ የሆነ ክህደት ካላያችሁ(ባቸው) በስተቀር!!” ነው ያሉት፡፡ የሁለት ሀገር ሰላም የፈለገ የነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲሥ ያክብር፡፡ ኢማሙ አሕመድ እንደሚሉት “የአላህ መልእክተኛን ሐዲሥ የመለሰ ከጥፋት አፋፍ ላይ ነው፡፡”
4.3. ከዚያ ባለፈ ሑሰይን ረዲየላሁ ዐንሁ የወጣበት ምክኒያት የአባቱ መናገሻ ከተማ በነበረችው ኩፋ የዐልይ ረዲየላሁ ዐንሁ “ደጋፊዎች ነን” የሚሉ ሰዎች በወንድሙ ልጅ አማካኝነት በይዐ ከገቡለትና ተከታታይ ደብዳቤዎች ከፃፉለት በኋላ ነው፡፡ ከደረሱት ደብዳቤዎች ውስጥ “እኛ መሪ የለንም፡፡ ምናልባት አላህ ባንተ አማካኝነት በሐቅ ላይ ከሰበሰበን ና” የሚል ነበር፡፡ እንግዲህ የሑሰይን ኢጅቲሃድ መነሻ ይሄ ነው፡፡ ኢብኑዙበይርም ቢሆን እንደ አንዳንድ ዑለማዎች ምናልባትም ደም አፍሳሹን ሐጃጅን ካፊር ነው ብሎ አምኖ ሊሆን ይችላል የተነሳው፡፡ የኢማሙ አንነወውይን ማብራሪያ (ሸርሑ ሰሒሕ ሙስሊም፡ 12/229) ይመልከቱ፡፡
4.4. የሑሰይንንም የኢብኑዝዙበይርንም፣ የኢብኑልአሽዐሥንም መውጣት ታላላቅ ሶሐቦችም ታቢዖችም ተቃውመውታል፡፡ ኢብኑ ዑመር ሶስት ሌሊት ተጉዞ ነው ሑሰይንን እንዲመለስ እያለቀሰ የለመነው፡፡ ኢብኑ ዐባስም እንዲሁ ሊመልስ ብዙ ጥሯል፡፡ ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምር ኢብኑልዓስም እንዲሁ “ሑሠይን ቀደሩን አፋጠነ፡፡ ወላሂ አግኝቸው ቢሆን ካላሸነፈኝ በቀር እንዲወጣ አልተወውም ነበር” ብሏል፡፡ (አልቢዳያ ወንኒሃያ፡ 8/160) አቡ ሰዒድ አልኹድሪ ረዲየላሁ ዐንሁም “ሑሰይን አሸንፎኝ ነው የወጣው፡፡ 'በነፍስህ ላይ አላህን ፍራ! ከቤትህ ተቀመጥ፡፡ በኢማምህ ላይ አትውጣ' ብየው ነበር” ይላል፡፡(አልቢዳያ ወንኒሃያ፡ 8/163) ወንድሙ ሙሐመድ ኢብኑልሐነፍያህ እራሱ ተቃውሞታል፡፡ ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህም እንዲሁ “ሑሰይንን ረዲየላሁ ዐንሁ አላህን ፍራ! ሰውን እርስ በርሱ አታጫርስ… ብየ አናግሬው ነበር፡፡ ግና አልተቀበለኝም” ይላል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ፡፡ ታላቁ ታቢዒይ ሰዒድ ኢብኑልመሰይብ ረሒመሁላህ “ሁሰይን ወደ ዒራቅ ባይወጣ ኖሮ ለሱ የተሻለ ነበር” ይላል፡፡ ኢብኑ ተይሚያም ረሒመሁላህ “ሑሰይን ረዲየላሁ ዐንሁ ብዙ ደብዳቤዎች ሲፅፉለት ወደ ዒራቅ ሰዎች ሊወጣ ያሰበ ጊዜ እንደ ኢብኑ ዑመር፣ ኢብኑ ዐባስ፣ አቡበክር ኢብኑልሓሪሥ ኢብኑ ሂሻም ያሉ ታላቅ የእውቀት ሰዎች እንዳይወጣ ጠቁመውት ነበር፡፡ … በሱ መውጣት ውስጥ የዲንም ይሁን የዱንያ ምንም ፋይዳ አልነበረም፡፡ … በመውጣቱና በመገደሉ ሳቢያ በሀገሩ ቢቀመጥ ከሚደርሰው የከፋ ነገር ተከስቷል፡፡ ኸይር እንዲገኝ፣ ሸር እንዲወገድ ያሰበው ነገር ምንም አልተገኘም፡፡ እንዳውም በመውጣቱና በመገደሉ ምክኒያት ሸሩ ጨመረ፤ ኸይሩ ቀለለ፡፡ እናም መውጣቱ የከባድ ጥፋት መንሰኤ ነው የሆነው፡፡ የሑሰይን መገደል ያለጥርጥር ከባድ ፈተናን ነው ያስከተለው፤ ልክ የዑሥማን መገደል ፈተናዎችን እንዳስከተለው” ይላሉ፡፡ (ሚንሃጅ፡ 4/531) ኢብኑ ከሢርም አዋቂዎችና የሚወዱት እንዳይወጣ አስጠንቅቀውት እንደነበር ገልፀዋል፡፡
የመዲና ሰዎች ለየዚድ ኢብኑ አቢሱፍያን ያላቸውን ቃል ባፈረሱ ጊዜ ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ቤተሰቡንና ልጆቹን ሰብስቦ እንዲህ አለ፡- “እኔ የአላህ መልእክተኛን (በቂያማ ቀን ለእያንዳንዱ ቃል አፍራሽ ባንዲራ ይተከልለታል” ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ እኛ ለዚህ ሰውየ (ለየዚድ) በአላህና በመልክተኛው ቃልኪዳን ቃል ገብተናል፡፡ እኔ አንድ ሰው በአላህና በመልክተኛው ቃልኪዳን ቃል ከተጋቡ በኋላ ለሱ ጦር ከመስበቅ የከፋ ቃል አፍራሽነት አላውቅም፡፡ እኔ በዚህ ነገር (ኺላፋ) ቃል ከገባ በኋላ ቃሉን የሚያፈርስ አላውቅም፣ የእኔና የእሱ መቆራረጫ ቢሆን እንጂ!!” (ቡኻሪ፡ 7111) ኢብኑ ከሢር ረሒመሁላህ ይህን ክስተት ሲያነሱ “አብዱላህ ኢብኑ ዑመር ኢብኑልኸጣብ እና በርካታ የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም #ቤተሰቦችም #ቃላቸውን_ካላፈረሱት_ውስጥ ነበሩ” ይላሉ፡፡ (አልቢዳያ ወንኒሃያ፡ 8/235) ጁንዱብ ኢብኑ ዐብዲላህ አልበጀሊ ረዲየላሁ ዐንሁም እንዲሁ ዐብዱላህ ኢብኑዙበይርን ሊመልስ ሞክሯል፡፡ በኢብኑ ዙበይር ፊትና ጊዜ ሁለት ሰዎች ዐብዱላህ ኢብኑ ዐመር ዘንድ መጡና “ሰዎች የምናየውን ውዝግብ እየፈፀሙ እያበላሹ ነው፡፡ አንተ ደግሞ የዑመር ልጅ እና የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰሐባ ነህ፡፡ እንዳትወጣ የሚከለክልህ ምንድን ነው?” አሉት፡፡ እሱም “የሚከለክለኝ አላህ የወንድሜን ደም ክልክል ስላደረገብኝ ነው” አላቸው፡፡ እነሱም “አላህ (ፊትና እስከማይኖር ድረስ ተዋጓቸው) አላለም እንዴ?” አሉት፡፡ እሱም “ፊትና እስከማይኖር ድረስ ተዋግተናል፡፡ ዲንም ለአላህ ሆኗል፡፡ #እናንተ_ግን_ፊትና_እስከሚኖር እና #ዲን_ከአላህ_ሌላ-ላለ_እስከሚሆን ድረስ ልትዋጉ ትፈልጋላችሁ!!” (ቡኻሪ፡ 4513) እንግዲህ ተመልከቱ! ግልፅ ሐዲሶችን ገሸሽ አድርገው ከጥንት ጀምሮ እንዲህ አይነት ሀሳብ የተሰነዘረባቸው ክስተቶች ላይ ነው የሚመረኮዙት፡፡
4.5. “የሑሰይንና የኢብኑ ዙበይርን ረዲየላሁ ዐንሁማ መነሳት ሰለፎች “ፊትና” ሲሉ ነው የጠሩት፡፡ ፊትናን ደሊል ማድረግ ደግሞ አይቻልም፡፡ እንዳውም በሚወጡት ላይ ማስረጃ ነው የሚሆነው፡፡ ታዲያ እንዴት ሆኖ ነው ፊትናዎች ማስረጃ የሚሆኑት?” ቀድሞ ነገር ከሑሰይን፣ ኢብኑ ዙበይር፣ ኢብኑልአሽዐሥና ከሌሎችም ክስተቶች የተገኘው ኸይር ነው ሸር? ያለጥርጥር ኸይር አልተገኘም፡፡ ታዲያ ምንን ማስረጃ እያደረጉ ነው ሰዎቹ?
የሑሰይንም ይሁን የኢብኑ ዙበይር ረዲየላሁ ዐንሁማ መውጣት ማስረጃ እንደማይሆን የታላላቅ ዑለማዎችን (ሸይኹልአልባኒ፣ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ሸይኽ ፈውዛን፣ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ ረስላን፣ ሸይኽ ዓዲል መንሱር፣ ሸይኽ ኻሊድ ዐብዱረሕማን፣ ሸይኽ አሕመድ አስሱበይዒ፣ ሸይኽ ጀማል አቡልፉረይሃን) መልስ በዚህ ገብተው ይከታተሉ https://www.facebook.com/ebanah/posts/710227582365532
በነገራችን ላይ ሑሰይን ረዲየላሁ ዐንሁ ወደ ሀገሩ ለመመለስ፣ ወይም ወደ ሙስሊሞች ምሽግ ለመሄድ ወይም ወደ የዚድ እንዲሄድ ፈቃድ ጠይቆ ነበር፡፡ ገዳዮቹ እምቢ ብለው ነው የገደሉት፡፡ ስለዚህ ሑሰይን በወጣበት አቋሙ ላይ አልነበረም፡፡ ኢብኑ ዙበይርም ለየዚድ መጀመሪያ ላይ ቃል ባይገባም ኋላ ላይ ገብቷል፡፡ ፊትናው ቢዘልቅም የስልጣን ይገባኛል ጉዳይ ግን የዚድ እስከሚሞት ድረስ አላነሳም፡፡ የተነሳው ኋላ ላይ ነው፡፡ በርካታ የሙስሊም ሀገራት በቁጥጥሩ ስለነበሩ አንዳንድ ዑለማዎች ዘንድ እንደኸሊፋም ተቆጥሯል፡፡
ኢኽዋናዊ ማምታቻዎች በጥቅሉ ወይ ላቅመ-መረጃ ያልደረሱ ደካሞች ናቸው፣ ወይ ያላግባብ እየለጠጧቸው እንጂ እነሱ ከሚያስተጋቡት አቋም ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው ወይ ደግሞ ግልፅ ከሆኑ በርካታ የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠንካራ ማስረጃዎች ጋር የማይነፃፀሩ ግላዊ ኢጅቲሃዳት ናቸው፡፡ እንዳውም እንደ ኢብኑ ተይሚያህ፣ ነወውይ እና ኢብኑ ሐጀር ያሉ በርካታ ታላላቅ ዑለማዎች በመሪዎች ላይ መውጣት ኋላ ላይ የዑለማእ ኢጅማእ ያገኘ ጉዳይ ሆኗል ይላሉ፡፡ ኢጅማዑን እንኳን ብንቶወው ከላይ የተጠቀሱት ሐዲሶች ከበቂ በላይ ናቸው፡፡
ቀድሞ ነገር ዛሬ ሽንጣቸውን ገትረው ለአመፅ የሚሟገቱትና የሚቀሰቅሱት ኢኽዋኖች ከሚቃወሟቸው መሪዎች መሻላቸው በራሱ አጠያያቂ ነው፡፡ ምክኒያቱም የሚቀናቀኗቸውን መሪዎች የሚተቹት በሸሪዐ አያስተዳደሩም ከሆነ
1. ኢኽዋኖች እራሳቸው ተረጋግተው ለአመታት በነገሱባቸው ሀገራትም በሸሪዐ አላስተዳደሩም
2. እንዳውም ሙርሲ “የሸሪዐ ህግ ቀድሞም በግብፅ ምድር አለ” ይላችኋል፡፡ እንግዲያው ምን ፍለጋ ነው የሚያምፁት?
3. አላማቸው ሸሪዐን ተግባራዊ ለማድረግ እንዳልሆነ በሊቢያ፣ በቱኒዚያና በግብፅ የተናገሩትን ከራሳቸው ስሙ http://www.safeshare.tv/w/FokaJQENG
4. ሙርሲ ከክርስቲያኖች ጋር የዐቒዳ ልዩነት የለንም፡፡ ይክፈቱና ይስሙት፡፡ http://www.safeshare.tv/w/OBAQYUadqF
5. ሴቶችን ሸሪዐዊ ልብስ እንዲለብሱ ማድረግ ባዶ ንግግር ነው! ሴቷ የሚስማማትን መልበስ መብቷ ነው፡፡ ሙርሲን ይስሙት http://www.safeshare.tv/w/nGkqNwayUo
6. እነዚህንና ሌሎች እጥፍ ድርብ ጥመቶችን በኢስላም ስም የሚፈፅሙ ኢኽዋኖች ከሚተቿቸው መሪዎች መሻላቸው እራሱ አጠያያቂ ነው፡፡ ምክኒያቱም የሚያምፁባቸው መሪዎች ጥፋታቸውን በአብዛሃኛው ኢኽዋኖች እንደሚያደርጉት በሸሪዐ ስም አይፈፅሙም፡፡ ኢኽዋኖቹስ? ለዚህም ነው ሸይኹልአልባኒ ረሒመሁላህ “የኢኽዋኖች አደጋ ከአይሁዶች አደጋ የከፋ ሊሆን ይችላል” ያሉት፡፡
በመጨረሻ እንዲታወቅ የምንፈልገው በመሪዎች ላይ ማመፅን መቃወማችን ጥፋታቸውን ለመሸፈንም ለነሱ ለመከላከልም አይደለም፡፡
1. ይልቅ የምንከላከለው ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሱና ነው፡፡ የነብዩን ሱና ማስተጋባት “የመንግስት ቅጥረኛ” ካስባለ ትችቱ ወዴት እንደሚዞር አስቡት፡፡
2. ሌላው ስለዚህ ርእስ የምናወራበት ምክኒያት ከዑለማዎቻችን ለመከላከል ነው፡፡ ከሰሒሕ ሐዲሦች ይልቅ “የትም ፍጪው” ላይ መሰረቱን የጣለው ቡድናዊ አመለካከታቸውን ስላጋለጡ ብቻ ዑለማዎቻችንን ለመግለፅ በሚሰቀጥጡ ቆሻሻ ቃላት ሲወጓቸው እያየን ነው፡፡ ከሙብተዲዖች አልፎም ከከሃዲዎች ጋር ህብረት እየፈጠሩ ሳለ ታላላቅ የሱና ዑለማዎችን ያለስማቸው ስም እየሰጡ ህዝቡ ከዑለማ ርቆ የነሱ ጭፍን ተከታይ እንዲሆን ሲተጉ እያየን ነው፡፡
3. ሌላው ስለዚህ ርእስ የምናወራበት ምክኒያት ኢኽዋኖች በኢስላም ስም አደገኛውን የኸዋሪጅን አመለካከት ህዝብ ላይ እያሰረፁ ስለሆነ ነው፡፡ ይስተዋል ኸዋሪጅ ማለት መሳሪያ ይዞ ለአመፅ የተነሳው ብቻ አይደለም፡፡ በራሳቸው የማይሳተፉትም በመሪ ላይ መውጣትን እየቀባቡ እንደ ጥሩ የሚያቀርቡም ኸዋሪጆች ናቸው፡፡ እንዳውም እንዲህ አይነቶቹን ኸዋሪጆች ከሰለፍ አኢማዎች አንዱ የሆኑት ዐብዱላህ ኢብኑ ሙሐመድ አድደዒፍ የመጨረሻ ቆሻሻዎቹ የኸዋሪጅ ክፍሎች እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡ ወገኔ ሆይ ያለህበትን ቦታ ረጋ ብለህ ተመልከት፡፡ ሳይታወቅህ የኸዋሪጅ አቀንቃኝ እንዳትሆን!!
**************ኢንሻአላህ ክፍል- 3 ይቀጥላል************


 የኢኽዋን ምሽጎችን ማንኮታኮት (ተከታታይ፣ ክፍል-1) 
የኢኽዋን ምሽጎችን ማንኮታኮት (ተከታታይ፣ ክፍል-3) ሰይድ ቁጥብ ለማያውቀው