Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የኢኽዋን ምሽጎችን ማንኮታኮት (ተከታታይ፣ ክፍል-1)


የኢኽዋን ምሽጎችን ማንኮታኮት
(ተከታታይ፣ ክፍል-1)
ኢኽዋኖች በርካታ የተክፊር አመለካከቶችን ባደባባይ መልቀቁን ተያይዘውታል፡፡ በርግጥ ዘመናዊው የተክፊር አመለካከት መነሻው ኢኽዋን እንደሆነ የሚያውቅ ይሄ ብዙም አይደንቀውም፡፡ ፅሁፌ ኢንሻአላህ ቀጣይ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ንኡስ-ርእስ ስር የምዳስሰው ሁለት ነገሮችን ነው፡፡
1/ እውን አጥፊ የሆኑ ሙስሊም መሪዎች ላይ ማመፅና ያደባባይ ትችት መሰንዘር የተከለከለው የመሪዎቹ ጥፋት እራሳቸው ላይ ሲገደብ ብቻ ነውን?
2/ የመሪዎችን ጥፋት በመቃወምና ምክር በመለገስ ላይ የአህሉሱና አቋምስ የቱ ነው? በምስጢር ወይስ ባደባባይ?
ወደ ነጥቦቹ
1. በሙስሊም መሪዎች ላይ ማመፅን፣ መሪዎችን ማንቋሸሽና መተቸትን የሚከለክሉ በርካታ ሶሒሕ ማስረጃዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ይሄ የአህሉ ሱና ዑለማዎች ዘንድ ውዝግብ የሌለበት ግልፅና የማያሻማ ርእሰ-ጉዳይ ነው፡፡ የኸዋሪጅ አመለካከት የተፀናወታቸው አካላት ግን የሐዲሦቹን መልእክቶች የግድ ሊጠመዝዙ እየተውተረተሩ ነው፡፡ እነኚህ በሰይድ ቁጥብ አመለካከት የተጠመቁ ሰዎች የሐዲሦቹ መልእክት “ባለስልጣናቱ በግላቸው ከዲን ጋር የሚጣረሱ እንደ መጠጥ፣ ዝሙትና የመሳሰሉ ወንጀሎችን ቢሰሩ በእነሱ የግል ጉዳይ አትግቡ ለማለት እንጂ ከሸሪዐ አንፃር ስለሚኖራቸው ክፍተቶቻቸው፣ ወይም ህዝብ ላይ ግፍ ሲፈፅሙ ዝም እንድንል አይደለም” በማለት የራሳቸውን ትንተና እየሰጡ ነው፡፡ ይሄ አቋም ውድቅ እንደሆነ ከሚከተሉት ሐዲሦች በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡
1.1. ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ከኔ በኋላ ‪#‎በመመሪያየ_የማይመሩ‬‪#‎በሱናየም_የማይጓዙ‬ መሪዎች ይመጣሉ፡፡ በነሱም ላይ ‪#‎ልቦቻቸው_የሸይጧን‬ ‪#‎አካላቸው_ደግሞ_የሰው‬ የሆኑ ሰዎች ይነሱባቸዋል” አሉ፡፡ ሁዘይፋ ረዲየላሁ ዐንሁ “እንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ከደረስኩኝ ምን ላድርግ?” ሲላቸው “አሚሩን#ትሰማለህ፣ ለሱም ‪#‎ትታዘዛለህ‬- ‪#‎ጀርባህ_ቢመታም‬ ‪#‎ገንዘብህ_ቢነጥቅም‬ እንኳን” አሉት፡፡ (ሙስሊም የዘገቡት) አስተውሉ!!
• መሪዎቹን እንዴት እንደገለፁዋቸው ተመልከቱ፡ #በመመሪያየ_የማይመሩ፣ #በሱናየም_የማይጓዙ “ጀርባህን ቢመታም ገንዘብህ ቢነጥቅም” እነዚህ ሀረጎች የመሪዎቹ ጥፋት ከራሳቸው የሚያልፍ እንደሆነ ልቡ በስሜት ላልታወረ ሁሉ ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ፡፡
• ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነዚህ ከሸሪአዊ መመሪያ ባፈነገጡ መሪዎች ላይ “አምፁ” ሳይሆን “ስሙ ታዘዙ” ነው ያሉት፡፡
• በነዚህ ከሸሪዐ መመሪያ በራቁ መሪዎች ላይ የሚነሱትን “ልቦቻቸው የሸይጧን አካላቸው ደግሞ የሰው የሆኑ ሰዎች” ሲሉ ነው የገለፁዋቸው፡፡ ግን እነማን ናቸው ስልጣን እያነፈነፉ ሁሌ በመሪዎች ላይ በምላስም በተግባርም የሚነሱት? “ብልጥ አሽትቱኝ እንጂ አጥግቡኝ አይልም፡፡”
1.2. ሌላ ማስረጃ፡- ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “…ከኔ በኋላ ‪#‎አድሎን‬ ታያላችሁ፡፡ ያኔ ‪#‎ታገሱ‬- ሐውድ ላይ እስከምታገኙኝ ድረስ!” (ቡኻሪና ሙስሊም)
• ልብ በሉ በሐዲሡ ውስጥ የተመለከተው የመሪዎቹ ጥፋት እንደ አስካሪ መጠጥ መጠጣት አይነት በራሳቸው ላይ የተገደበ ጥፋት ሳይሆን ወደ ህዝብ ተሻጋሪ የሆነ ‪#‎አድልዎ‬ ነው፡፡
• በሐዲሡ የተሰጠው መፍተሄ ተቃውሞ ማስነሳት ሳይሆን መታገስ ነው፡፡ ኢኽዋኖች የዚህን ሐዲሥ መልእክት ቢቀበሉ ጎልተው የሚታዩበት ሌላ ምን አጀንዳ ይኖራቸው ነበር?
• እስከመቼ ነው የመሪዎችን ጭቆና የምንታገሰው ከተባለ ሐዲሡ ላይ ግልፅ መልስ አለ፡፡ ባይሆን የነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትእዛዝ ለማክበር ከስሜት ነፃ መሆን ይጠይቃል፡፡
• እንዳውም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ፡- “የመሪዎችን በደል መታገስ ከአህሉሱና ወልጀማዐ መሰረቶች አንዱ መሰረት ነው” ይላሉ፡፡ (አልመጀሙዕ፡ 28/179) ስሜት ያሰከራቸው ልማደኞች ኢብኑ ተይሚያንም “ቅጥረኛ ነው” እንዳይሉት ደግሞ! ልብ በሉ! ወደው አይደለም ዑለማዎች ኢኽዋን ከአህሉሱና አይደለም የሚሉት፡፡
1.3. ሌላ ማስረጃ፡- ዒርባድ ኢብኑ ሳሪያ ረዲየላሁ ዐንሁ ባስተላለፈው ሐዲሥ በአንድ ወቅት ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ልቦች በፍርሃት የራዱበት፣ አይኖች እንባ ያረገፉበት ምክርን መከሩን፡፡ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ልክ የተሰናባች ምክር ትመስላለች፣ እናም ምከረን” አልን፡፡ እሳቸውም “አላህን በመፍራትና ባሪያ እንኳን#ቢሾምባችሁ ‪#‎በመስማትና_በመታዘዝ‬ ‪#‎አደራ‬ እላችኋለሁ፡፡ ከናንተ የሚቆይ በርካታ ውዝግቦችን ያያል፡፡ ያኔ አደራችሁን የኔን ሱና እና ቀጥተኛና ቅን የሆኑ ምትኮቼን ሱና አደራችሁን፡፡ በመንጋጋዎቻችሁ ነክሳችሁ ያዙ፡፡ አዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ፡፡ ምክኒያቱም ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነውና፡፡” (ሰሒሑትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 37)
በዚህ ሰሐቦችን ባስለቀሰው ምክር ውስጥ የሚገኙ ቁም ነገሮችን አስተውሉ፡-
• ሙስሊም የሆነን መሪ ‪#‎በጉልበት_ቢነግስ‬ እንኳን መታዘዝ ግዴታ ነው፡፡ ሐዲሡን አስተውሉ!
• በሐዲሡ እንደተገለፀው ውዝግቦችን እያየን ነው፡፡ መፍተሄው ደግሞ ወደ ሱና መጠለል ነው፡፡ ሱና ደግሞ መሪዎች ላይ “ግልፅ የሆነ ክህደት እስካላያችሁ” በመልካም ስሙ ታዘዙ ነው የሚለው፡፡ የአህሉሱና አቋም ምን እንደሆነ ከላይ የኢብኑ ተይሚያን ንግግር አሳልፊያለሁ፡፡ ከዚህ የተለየ አመለካከት ያላቸው ኸዋሪጆች ናቸው፡፡ የኸዋሪጅ አመለካከት ደግሞ በሐዲሡ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠባቸው መጤ ነገሮች አንዱ ነው፡፡
1.4. ሌላው መሪዎች ከራሳቸው ያለፈ ጥፋት እንኳን ቢኖርባቸው መታዘዝ እንዳለብን ከሚያመላክቱ ሐዲሦች አንዱ፡- ሶሐቦች “ሐቃቸውን የሚጠይቁን ‪#‎ሐቃችንን‬ ግን ‪#‎የሚከለክሉን‬ መሪዎች ካገኙን ምን እናርግ?” ብለው ነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲጠይቁ “‪#‎ስሙ‬ ‪#‎ታዘዙ‬!! በነሱ ላይ የተጣለባቸው ሀላፊነት አለ፡፡ በናንተም ላይ የተጣለባችሁ ሀላፊነት አለ” በማለት ነው የመለሱላቸው፡፡ (ሙስሊም የዘገቡት) ልብ በሉ!!
• በሐዲሡ ላይ የተገለፁት መሪዎች ጥፋታቸው በራሳቸው ላይ የተገደበ ሳይሆኑ በዘመኑ ቋንቋ አንባገነን የሆኑ ጨቋኞች ናቸው፡፡ መልእክቱን አስተውሉት፡፡ “ #ሐቃችንን ግን #የሚከለክሉን” ነው የሚለው፡፡
• ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተሰጠው መፍተሄ ግን “ስሙ ታዘዙ!!” የሚል እንጂ አምፁ አይደለም፡፡
• ይሄ ከስልጣን ኋላ ለሚያለከልኩ ኢኽዋኖች ላይዋጥ ይችላል፡፡ በግድ ሊያሰልሙት በሚዳክሩለት ዴሞክራሲ ለተለከፉ ሰዎች ባይዋጥም አይገርምም፡፡ “ጥፋትም ብታዩ መመካከር እንጂ ባደባባይ መተቸት ወይም ማመፅ አይቻልም” ሲባሉ ያቺ የሚሞቱላት ስልጣን እንደሰማይ ልትርቅ ነው፡፡ አዎ እውነታቸውን ነው ኩርሲዋ ትርቃለች፡፡ ስለዚህ ለነሱ የስልጣን ጥማት ሲባል የሐዲሡ መልእክት ይጠመዘዛል፡፡ እዚህ ጋ ለምን ስልጣን ፈላጊ ትላቸዋለህ ሊባል ይችላል፡፡ በቀጣይ ክፍሎች እመለስበታለሁ ኢንሻአላህ፡፡
• ኢኽዋኖች “ዐሊሞችን እናክብር” እያሉ ለሙብተዲዖች እንደሚሟገቱ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ስሜታቸውን የማይጋሩ ዐሊሞቹን የአንባገነን ቅጥረኛ አድርገው ሲፈርጁ ምንም አይሰቀጥጣቸውም፡፡ የት አል ዐሊም ማክበሩ? ስለ ዑለማእ ክብር የምታስተጋቡ ሁሉ! ለመሆኑ ይሄ መፈክራችሁ የሱና ዑለማዎችን አይመለከትምን? ለሙብተዲዖች ጥብቅና የሚቆሙ የናንተ የሰፈር ሸይኾች ሲነኩ አገር ታቃጥላላችሁ ዐለም አቀፍ ዑለማዎች በወጠጤዎች ሲወረፉ ግን በረዶ ናችሁ - ምናልባት አጫፋሪ ካልሆናችሁ፡፡ ይሄ ባንድ እራስ ሁለት ምላስ መሆን ያዛልቃል?
• “የእከሌ መንግስት ዱዐቶችን ያስራል፣ ደዕዋ ይከለክላል” ሲሉ እውነት ለደዕዋ ተቆርቁረው እንዳይመስልህ፡፡ እዚሁ ሀገራችን ውስጥ እራሱ ስንት ኢስላማዊ ትምህርቶችንና ደዕዋዎችን አስከልክለዋል?! ስንት መድረሳዎችን አዘግተዋል?! ስንት ዱዐቶችን አሳስረዋል?! ይሄ ፊትናቸው ዛሬ እንኳን በዚህ ቀውጢ ሰአት አልቆመም፡፡
2. ሌላኛው በዚህ ፅሁፌ ውስጥ ላነሳው የፈለግኩት መሪዎችን ባደባባይ በግልፅ መተቸትን የሚመለከት ነው፡፡ ኢኽዋኖች የጧት ማታ ዚክራቸው መሪን ማንቋሸሽ ነው፡፡ “ትምህርታቸውን”፣ ጋዜጦቻቸውን፣ መፅሀፎቻቸውን፣ የርስ በርስ ወሬያቸውን እንዳለ የሚያደምቁት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሀሳብ የማይጋሯቸውን ሙስሊም መሪዎች በማብጠልጠል ነው፡፡ “ሸሪዐው በዚህ መልኩ ባደባባይ መተቸትን አይፈቅድም” ብትሉ ቅጥረኛ ያደርጓችኋል፡፡ “ከጂሃድ ሁሉ በላጩ ከጨቋኝ መሪ ‪#‎ፊት‬ ሐቅን መናገር ነው” የሚለውን ሐዲስ ፊትና ለመፍጠር በየመድረኩ፣ ወይም ከማህበራዊ ድረገፅ ስር አድፍጠው ለሚነዙት መርዝ ማስረጃ ያደርጉታል፡፡ እነሱ ያሉት ከማዶ ሐዲሡ ያለው ሌላ ማዶ፡፡ ጥንትም የሙብተዲዖች መታወቂያ ይሄው ነው፡፡ የሚፈልጉትን ሐዲሥ በሚያሰኛቸው መልኩ መተርጎም፡፡ የሚነቅፏቸውን ማስረጃዎች ወደ ኋላ ያሽቀነጥራሉ፡፡ እርግጥ ነው ፊትና እንደማይፈጠር ከታየው እና ለብቻ መልእክቱን ለማድረስ እድሉ ከሌለው ያየውን ጥፋት ከመሪው ፊት መምከር ወይም መናገር ትልቅ ስራ ነው፡፡ ይሄ ግን አንድም የከፋ ፊትና የማይፈጠር ከሆነ ሁለትም ሌላ አማራጭ ከሌለ ነው፡፡ በኢስላም “ሙንከርን ከሱ በከፋ ሙንከር ማስወገድ አይቻልም” የሚለው የታወቀ መርህ ነው፡፡ እንዳውም ለመሪዎች የሚሰጥ ምክር መሰረቱ በግልፅ ሳይወጣ ለብቻ ነው መሆን ያለበት፡፡ ይህን ከሚያመላክቱ ማስረጃዎች ውስጥ ጥቂቶቹን እንይ
2.1. ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- “ ‪#‎መሪን_በሆነ_ጉዳይ_ሊመክር_የፈለገ‬#በግልፅ_አያውጣው፡፡ ‪#‎ይልቅንም_እጁን_ይዞ‬ ‪#‎ገለል_አርጎ_ይንገረው‬፡፡ ከተቀበለው መልካም፡፡ ‪#‎ካልተቀበለው‬ ግን ‪#‎ያለበትን‬ ‪#‎አውርዷል‬፡፡” (ዚላሉልጀናህ፡ 507)
2.2. ኡሳማ ኢብኑ ዘይድን “ለምን ዑሥማንን ገብተህ አታናግረውም” አሉት፡፡ እሱም እንዲህ አለ፡- “ ‪#‎ሳናግረው‬ ‪#‎ካላሰማኋችሁ‬ እንደማላናግረው ነው የምታስቡት? ወላሂ በጉዳዩ ላይ የመጀመሪያ ከፋች ሆኜ የሆነን ነገር ሳልከፍት #ብቻችንን_ሆነን_አናግሬዋለሁ፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም)
2.3. ዐብዱላህ ኢብኑ ዐኪም አልጁሀኒ “ከዑሥማን በኋላ በየትኛውም ኸሊፋ ደም ላይ አልተባበርም” ሲል “የመዕበድ አባት ሆይ! በሱ (በዑሥማን) ደም ላይ ተባብረሃልን?” አሉት፡፡ “እኔ #የሱን_መጥፎ_ነገሮች #መናገሬን #በደሙ_ላይ_እንደመተባበር_ነው_የምቆጥረው” አለ፡፡ (ጠበቃት ኢብኑ ሰዕድ፡ 6/115)
2.4. ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር “መሪውን በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል እችላለሁ?” ብየ ኢብኑ ዐባስን ጠየቅኩት ይላል፡፡ እሱም “እንዳይገልህ ከፈራህ ተው” አለኝ፡፡ ስደግምለት እሱም ደገመልኝ፡፡ ከዚያም ስደግም ተመሳሳይ ነገር አለኝ፡፡ ከዚያም “ #የግድ #የምታደርገው_ከሆነ #ባንተና_በሱ_መሃል_ይለቅ” አለኝ፡፡(በይሀቂ ዘግበውታል)
2.5. ኢብኑ ዓሚር የተባለ ገዢ የሳሳ ልብስ ለብሶ ሚንበር ላይ ኹጥባ ያደርጋል፡፡ አቡ ቢላል የተባለ ሰው “አሚራችንን እዩ የጋጠ-ወጦችን ልብስ ነው የለበሰው!” አለ፡፡ ሰሐቢዩ አቡ በክራህ ረዲየላሁ ዐንሁ “ #ዝም_በል! የአላህ መልእክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡-“ #ምድር_ላይ_ያለን #የአላህን_ሹም_ያዋረደ #አላህ_ያዋርደዋል!” (ሶሒሕ ቲርሚዚ፡ 2224) አስተውሉ! ይሄ አስተዋይ ለሆነ ሰው ከባድ መብረቅ ነው!
2.6. ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በምድር ላይ የአላህን ሱልጣን ያዋረደ አላህ ያዋርደዋል፡፡” (አሶሒሐህ፡ 2296) ከዚህ ሐዲሥ ስር ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡ “ስለንጉስ #ክፉ_ማውራት #ሀሜት_ከሆነ ወይም ደግሞ #ህዝብ_እንዲያውቅ_አድርጎ_መምከር፣ #በግልፅ_ማውጣት አላህ ፈፃሚውን #ሊያዋርደው_ቃል_የገባበት #ማዋረድ_ከሆነ፤ ሊያገኟቸው ለሚችሉ ዑለማዎች የገለፅነውን ነገር (ምክሩን በምስጢር ማድረጉን) ከግምት ማስገባት ግዴታ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡”
2.7. ሰዒድ ኢብኑ ጁምሃን የተባለው ታቢዒይ ዐብዱላህ ኢብኑ አቢ አውፋን አገኘሁትና “መሪው ሰዎችን እየበደለ ነው፣ የተለያዩ ነገሮችን ይፈፅምባቸዋል” አልኩት፡፡ እጄን ይዞ #ጠንከር_አርጎ_ቆነጠጠኝና ከዚያም አንዲህ አለኝ፡ “ኢብኑ ጀምሃን ሆይ! #ወዮልህ! አደራህን ከብዙሃኑ ጋር ሁን አደራህን ከብዙሃኑ ጋር ሁን፡፡ መሪው የሚሰማህ ከሆነ ከቤቱ ሄደህ የምታውቀውን ንገረው፡፡ ከተቀበለህ መልካም፡፡ ካልሆነ ግን ቶወው፣ አንተ ከሱ የተሻለ የምታውቅ አይደለህም፡፡” (አልባኒ ሐሰን ብለውታል)
2.8. ሸውካኒ ረሒመሁላህ፡- “በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ የመሪው ስህተት የታየው ሰው ሊመክረው ይገባል፡፡ #ማጥላላቱን_በግልፅ_ባደባባይ_ሊያወጣ_ግን_አይገባም፡፡ ይልቅ #በሐዲሥ_እንደመጣው #እጁን_ይዞ_ገለል_ብሎ ምክሩን ይለግሳል እንጂ #የአላህን_ሹም_አያዋርድም፡፡ (አስሰይል፡ 58) ኢኽዋኖች ሆይ! በሉ እንደለመዳችሁ ሸውካኒንም “ቅጥረኛ” በሏቸው፡፡
2.9. ሸይኽ አስሰዕዲ ረሒመሁላህ፡- “ሰዎች #የመሪዎችን_ክፉ_ነገር_ሊደብቁ_ይገባቸዋል፡፡ #እነሱን_በመሳደብ_ውስጥ #ሊገቡ_አይገባም፡፡ ይልቁንም አላህ ቅናቻን እንዲያድላቸው #ዱዐ_ሊያደርጉላቸው #ይገባል፡፡ ንጎሶችንና አሚሮችን #መሳደብ_ትልቅ_ሸር_አለው፣ ጠቅላይና ልዩ የሆነ ጉዳትም አለው፡፡ …” (ኑሩልበሳኢር ወልአልባብ፡ 66)
2.10. ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ፡- “ወደ ልዩነት፣ ውዝግብ እንዲሁም መሪዎችንና ዑለማኦችን ወደመሳደብ የሚጠሩ ካሴቶችን ማሰራጨት ያለጥርጥር ይሄ እጅግ ከከፉ ጥፋቶች ውስጥ ነው፡፡ (መጅሙዑልፈታዋ ወልመቃላት፡ 8/410) ይሄ የኢብኑ ባዝ ንግግር የነዚህን በኸዋሪጅ አመለካከት የተጠቁ ሰዎችን ጥፋት ለሚያሰራጩ አስተዋሽ ደወል ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- መሪዎችን ችግር ቢኖርባቸውም መስማትና መታዘዝ የአህሉሱና አቋም ነው ሲባል በጥፋት ሲያዙ ጥፋቱን እንፈፅማለን ማለት አይደለም፡፡ ኢኽዋኖች እንደ ቅጥረኛ የሚስሏቸው ዑለማዎችም አንዳቸውም በጥፋት መታዘዝ አለብን አላሉም፡፡ ነገር ግን ጧት ማታ ለአመፅ መቀስቀሳቸውን ስላጋለጧቸው ነው በማያምኑት ነገር የሚወነጅሏቸው፡፡ ባጭሩ መሪዎች በጥፋት ቢያዙ ያዘዙትን ጥፋት አንፈፅምም፣ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚኖረን ታዛዥነት ግን ባለበት ይቀጥላል፡፡ ጥፋት ስላየን ብቻ ጭራሽ አለመስማትና አልፎ ባደባባይ ማንቋሽሽ ከላይ በመጠኑ ከተዘረዘሩት ግልፅ ማስረጃዎች ማፈንገጥ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሐዲሥ እንውሰድ፡ ዑባዳህ ኢብኑስሳሚት ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፡- “ሲከብድም ሲቀልም፣ ሲደላም ሲከፋም፣ #አድልዎ_ሲፈፀምብንም #ልንሰማና_ልንታዘዝ፣ እንዲሁም ስልጣንን ከባለቤቱ ላንሞግት፣ የትም ብንሆን ሐቅን ልንናገር፣ በአላህ ላይ የወቃሽን ወቀሳ ላንፈራ ለአላህ መልእክተኛ ቃልኪዳን ገብተናል፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም) አስተውሉ፡- አድሎ እየፈፀሙም ለነሱ የሚኖረው ታዛዥነት ግን አይነሳም፡፡ ይሄ የማስረጃ ቋንቋ ለሚገባው ግልፅ ነው፡፡ ሸይኹልአልባኒን አላህ ይማራቸውና “ሐቅ ፈላጊን አንድ ማስረጃ ይበቃዋል፡፡ ስሜት ተከታይን ግን አንድ ሺ ማስረጃም አይበቃውም” ይላሉ፡፡
- ሙስሊም መሪዎችን ስለመታዘዝ ስናወራ ያልተፃፈ የሚያነቡት ኢኽዋኖች “አቅሙ ቢኖርህም ካፊር መሪዎችንም መታዘዝ ዋጂብ ነው፣ ቢረግጥህም፣ ዲንህን ሊያጠፋ ቢያሴርም ስማ ታዘዝ ብለዋል” እያሉ የሚቀጥፉ ብዙ አሉ፡፡ ለነዚህ ቃላት ማባከን አያስፈልግም፤ አላህ ልቦና ይስጣቸው፡፡ ለነገሩ እነሱ ሰፈር ውሸት ብርቅ አይደለም፡፡
*************ይቀጥላል ኢንሻአላህ*************

የኢኽዋን ምሽጎችን ማንኮታኮት (ተከታታይ፣ ክፍል-2) 
የኢኽዋን ምሽጎችን ማንኮታኮት (ተከታታይ፣ ክፍል-3) ሰይድ ቁጥብ ለማያውቀው