Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እኔስፈራሁ እንጃ ግጥም

~~~እኔስፈራሁ እንጃ~~~
ወላሂ ፈራሁ እኔስ እንጃ!
እንባ ሳይወርድ ከዐይናችን
ተቅዋ ሳይገባ ከልባችን
ተንኮል ሳይተው አዕምሮአችን
ከበደል ሳያርፍ እጃችን
እንዲህ በዝቶ ወንጀላችን
በየቀኑ ጨምሮ ጥፋታችን
ተማርን ብለን አሊም ንቀን
በሱና ተከታዮች ተሳልቀን
ለወር ብቻ መስጊድ ሞልተን
ለፊጥር ብቻ ዘካ ከፍለን
እንዲህ ከርመን ተዘናግተን
ለአኼራ መች ሰርተን
ልፋት ድካማችን ሳይበዛ
እንደርስ ይሆን እንደዋዛ
የአላህ ጀነት መች ረክሶ
ውድ እኮ ነው መች ቀንሶ
ሲቸግረን ስሙን ጠርተን
ሲያልፍልን በሱ አምፀን
ሲጠናብን ቃሉን ሰምተን
ሲረግብልን ከዲን ወጥተን
እንደርስ ይሆን ለጀነቱ
ከአላህ ራህመት ከውድ ቤቱ
እነሆን ይሆን ከዚያች እንጃ
ወላሂ ፈራሁ እኔስ እየመጂቡ
ያመጂቡ አሳምረው ሁኔታችን
ሰላም አርገው ሕይወታችን
ከቀብር ቅጣት ነጃ በለን
ያኢላሒ ወንጀላችንን አፉ በለን
ከከሰሩ ሰዎች አትመድበን