Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

(ተጀሡስ) እከሌ ምን ሠራ???

(ተጀሡስ) እከሌ ምን ሠራ???
አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካቱ
☞ ተጀሡስ (የሠዎችን ግራ ጎን መከታተል) በእስልምና እጅጉኑ የተወገዘ እና የተከለከለ ነገር መሆኑን ደግፈው የሚመጡ የሀዲስ እና የቁርአን መረጃዎች አሉ
አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እንዲህ ሲል ይከለክለናል
( ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺍﺟْﺘَﻨِﺒُﻮﺍ ﻛَﺜِﻴﺮًﺍ ﻣِّﻦَ ﺍﻟﻈَّﻦِّ ﺇِﻥَّ ﺑَﻌْﺾَ ﺍﻟﻈَّﻦِّ ﺇِﺛْﻢٌ ﻭَﻟَﺎ ﺗَﺠَﺴَّﺴُﻮﺍ ﻭَﻟَﺎ ﻳَﻐْﺘَﺐ ﺑَّﻌْﻀُﻜُﻢ ﺑَﻌْﻀًﺎ ﺃَﻳُﺤِﺐُّ ﺃَﺣَﺪُﻛُﻢْ ﺃَﻥ ﻳَﺄْﻛُﻞَ ﻟَﺤْﻢَ ﺃَﺧِﻴﻪِ ﻣَﻴْﺘًﺎ ﻓَﻜَﺮِﻫْﺘُﻤُﻮﻩُ ﻭَﺍﺗَّﻘُﻮﺍ ﺍﻟﻠﻪَ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠﻪَ ﺗَﻮَّﺍﺏٌ ﺭَّﺣِﻴﻢٌ ) [ﺍﻟﺤﺠﺮﺍﺕ 12: ] .
እናንተ ያመናችሁ ሆይ ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ ከጥርጣሪ ከፊሉ ሀጢአት ነውና አውራ አትከታተሉ ፣አ ንደኛችሁ አንደኛችንአይማ ።አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ሲሆን መብላት ይወዳልን? (መብላቱን ጠላችሁትን) ሀሜቱንም ጥሉት)
የአላህ መልእክተኛም ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ብለዋል
ﻭﻓﻲ «ﺍﻟﺼﺤﻴﺤﻴﻦ » : ﺃﻥَّ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻗﺎﻝ : (( ﻭﻻ ﺗﺠﺴَّﺴﻮﺍ، ﺗﺤﺴﺴﻮﺍ ..))
((የሠዎችን አውራ ለሠዎች ለመንገርም ቢሆን ፣ለራሣችሁ ለማወቅ ብላችሁ አትከታተሉ))
☞እንደሚታወቀው የሠው ልጅ ሢፈጠርም ተሣሣች ተደርጎ ነው የተፈጠረው በተለያዩ አጋጣሚዎች ከሡ የማይጠበቁ ተግባራትን ሊፈፅም ይችላል የዚኔ ከእኛ የሚጠበቀው ሠውዬውን እግር በእግር እየተከታተሉ በወንጀሉ ለማማት እና ለማጋለጥ መቸኮል አይደለም ወንጀሉን ሢሠራ እንኳን ለማየት አጋጣሚው ቢፈጠርልን ላለማየት መሞከር ይኖርብናል
☞ነገር ግን የአንድን ወንጀለኛ ወንጀሉን እየተከታተልን እከሌ እንዲህ ነው ፣ እከሌ እንዲህ አደረገ የምንል ከሆነ ((እኛም ሠዎች ነንና አይብ (ነውር) አይጠፋንም)) አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ የኛንም ነውር ይፋ ያደርግብናል በአሔራም ከበድ ያለ ቅጣትን አዘጋጅቶልናል
: ﺃﻥ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻗﺎﻝ : « ﻳﺎ ﻣﻌﺸﺮ ﻣﻦ ﺁﻣﻦ ﺑﻠﺴﺎﻧﻪ، ﻭﻟﻢ ﻳﺪﺧﻞ ﺍﻹﻳﻤﺎﻥُ ﻗﻠﺒَﻪ، ﻻ ﺗﻐﺘﺎﺑﻮﺍ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ، ﻭﻻ ﺗﺘﺒﻌﻮﺍ ﻋﻮﺭﺍﺗﻬﻢ؛ ﻓﺈﻥَّ ﻣَﻦ ﺗﺘﺒَّﻊ ﻋﻮﺭﺍﺗﻬﻢ ﺗﺘﺒَّﻊ ﺍﻟﻠﻪُ ﻋﻮﺭﺗﻪ، ﻭﻣﻦ ﺗﺘﺒﻊ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻮﺭﺗﻪ ﻳﻔﻀﺤﻪ ﻓﻲ ﺑﻴﺘﻪ » .
((በምላሣችሁ ያመናቹ ሆይ! እምነት በልባቹ ያልገባች ሠዎች ሆይ! ሙስሊሞችን አትሙ ነውራቸውንም አትከታተሉ ፣ የነሡን አውራ የተከታተለ ሠው የሡን አውራ አላህ ይከታተለዋል አላህ አውራውን ከተከታተለው እቤቱ የሠራውን ያጋልጠዋል))
ከቀደምት ሠለፎች መካከልም በዚህ ዙር ብዙ ተብሏል የተወሠነውን
ﻗﺎﻝ ﻋﺒﺪ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﻦ ﻣﺴﻌﻮﺩ - ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ : « ﺇﻧّﺎ ﻗﺪ ﻧﻬﻴﻨﺎ ﻋﻦ ﺍﻟﺘَّﺠﺴُّﺲ، ﻭﻟﻜﻦ ﺇﻥ ﻳﻈﻬﺮ ﻟﻨﺎ ﺷﻲﺀ ﻧﺄﺧﺬ ﺑﻪ » .
አብደላህ ኢብኑ መስኡድ አላህ ስራውን ይውደድለትና « የሠዎችን አውራ ከመከታተል ተከልክለናል ፣ ሣንፈልግ ካወቅን ግን ለራሣችን እንይዘዋለን»
-2 ﻋﻦ ﺍﺑﻦ ﻋﺒّﺎﺱ - ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﻤﺎ- ﻓﻲ ﻗﻮﻟﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ : ( ﻭَﻻ ﺗَﺠَﺴَّﺴُﻮﺍ ) [ ﺍﻟﺤﺠﺮﺍﺕ 12: ]
ﻗﺎﻝ : ﻧﻬﻰ ﺍﻟﻠﻪُ ﺍﻟﻤﺆﻣﻦَ ﺃﻥ ﻳﺘّﺒﻊ ﻋﻮﺭﺍﺕ ﺃﺧﻴﻪ ﺍﻟﻤﺆﻣﻦ .
አብደላህ ኢብን አባስ አላህ ስራውን ይውደድለትና ( ﻭَﻻ ﺗَﺠَﺴَّﺴُﻮﺍ)) ) ይህችን የአላህ ንግግር አስመልክቶ « አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ምእመናንን ነሌች ምእመናን አውራ መከታተሎን ከለከለ))
☞☞ የሠዎችን አውራ መከታተል ከሚያስከትላቸው ችግሮች ውስጥ ይጥላል
★ የእምነት ድካማነት ምልክት ነው
★ አመፀኛ ያደርጋል
★ ለጥፋት ይዳረጋል
★ የራሡ አይብ ይጋለጥበታል
★ የአላህ የመልዕክተኛው እና ለሙእሚንች ቁጣ ይዳርጋል
♜ ማስጠንቀቂያ !!!
☞☞ አንተ ማን ሆነህ ነው ስለ ወንድምህ የምትከታተለው ፣ አንተ መላይካ ነህ ወንጀል የማሠራ? አንተ በቤትህ ለብቻህ የሠራህውን ወንጀል አላህ ደብቆልህ እንጂ አንተ ወንጀል አትሠራም ማለት ነው?? ተጠንቀቅ የራስህን ማንነት ደብቀህ ስለ ሠው ማንነቶ ስታወራ አላህ ያንተን ማንነት እንዳያፍረጠርጠው ተጠንቀቅ
♜ ማሣሠቢያ!!!
☞ እዚህ ርእስ ላይ ሣልጠቅሠው የማላልፈው ነገር በዲን ጉዳይ ስለተሣሣቱ ሙብተዲኦች በምናስጠተቅቅበት ወቅት በግላቸው የሚሠሩት ወንጀል እየተከታተለን በግሉ ስለሠራው ወንጀል ማውራት የለብንም !!እከሌ የሚባል ሙብተዲእ ሴት ጨበጠ እንዲህ ሆነ እንዲህ ወጣ እንዲህ ወረደ ማለት ተገቢ አይደለም!!! ማሶጠንቀቅ ያለብን ዲን ላይ ስለጨመራት ነገር ብቻ ነው!!!
☞ ይህ ማለት ደግሞ በዲን ላይ ሢቀጣጥፍ አይቡ ነውና ይፋ አይውጣበት ለማለት የሚያስደፍር አይደለም
ወንድሞች ሁላችንም እራሳችንን እንገምግምበት ይህ ችግር የተወሠኑ ሠዎችን አይደለም ያጠቃው ብዙዎቻችንን ነው በርካታዎቻችን ወደ እራሣችን ከማየት በላይ የሠው ጀርባ ማጥናት እና የሠው ግራ ጎንን መፈለግ ይቀናናል ወደ እራሣችን እንመለስ!! ሁል ግዜ የራሣችንን አህዋል እንፈትሽ! እራሣችንንም እንመርምር! እራሳችንን እንተሣሠብ!!!
አላህ በሠማነው ተጠቃሚ ያድርገን!!!

Post a Comment

0 Comments