Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የኡማው አንድነት

የኡማው አንድነት አንድነት
አንብበው ሲጨርሱ share አድርገው ያዳርሱ
☞ አንድነት በኢስላም ከፍተኛ ቦታ የሚሠጠው ነገር ነው
☞አምስቱ የኢስላም መሠረቶች በአጠቃላይ ካስተዋልናቸው ወደ ዚሁ አንድነት እና መሠባሠብ ይጠራሉ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላም እሡጋር የሚያደርሠን ገመድ ላይ እንድን ሠባሠብ እና ያችኑ ገመድ በአንድነት እንድንይዝ እንዲሁም ይህችን ገመድ እንዳንለቅና እንዳንበታተን እንዲህ ሢል ያዘናል
«የአላህን(የማመን) ገመድ ሁላችሁም ያዙ አትለያዩም»
‪#‎ግን‬
‪#‎ምን_አይነት_አንድነት_እና_ህብረት‬??? =>አዎንልበሉ! ወንድሞቼ ሁሉም ለአንድነት እና ህብረት ይዘምራል አሥፈላጊነቱንም ይሠብካል ይደሠኩራል የጥንቶቹ ቁረይሾችም /ሙሽሪኮች/ ሣይቀሩ ሙሀመድ (ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም) አንድነታችንን በተነው አባትን ከልጅ ባልን ከሚሥት ጏደኛን ከጏደኛ በድግምት ለያየብን ብለው ነበር እነዚያም የአላህን ሢፋት/ ባህሪ/ከአላህ ላይ በመግፈፍ አላህና መልዕክተኛውን ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም በማሥተባበል የሚታወቁትም /ጀህሚያዎች/ እና /ሙዕተዚላዎች/ አህመድ ኡብኑሀንበልን ከፋፋይ በታታኝ ብለዋቸው ነበር ኢብኑ ተይሚያ: መሀመድ ኢብኑ አብድል ወሀብም በየዘመኑና በየትውልዱ ተውሒድን እና ሡናን ይፋ ያወጡ ኡለማዎች ተመሣሣይ እጣ ደርሧቸው ነበር ትከፋፍላለህ ትበታትናለህ ስለ ልዩነት እንጂ ሥለ ሌላ አታውቅም ልሠማ ባይ የመደቤን አሙቁልኝ..... ወዘተ በመሆኑም አንድነት እና ህብረት ሊተገበር የሚችለው አላህን ሡብሀነሁ ወተአላን በብቸኝነት በማምለክ ወደ እሡም አምልኮት ብቻ በመጣራት የኢሥላማዊውን ጥሪ ዳእዋን በዚህ /በተውሒድ/ በመጀመር የነብዩን ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ሡናን ህያው በማድረግ የትኛውንም ነብያዊ ፈለግን ሣያንቁ በመከተል በተጎዳኙም ማንኛውም በዲኑ ላይ አዲሥ መጤ አስተሣሠብን /ቢድአ/ የሆኑ ነገሮችን በመዋጋት የቢደአ አራማጆጅ በሆኑ በየትኛዎቹም ግለሠቦች ሆኑ ቡድኖች እንዲሁም ቢደአ የሆኑ ነገሮች የተሠገሠጉባቸውን ና /የተከማቹባቸውን/ መፀሀፍቶቻቸውን እና ትምህርቶችን በማሥጠንቀቅ እና በመዋጋት የቁርአን እና ሀዲሥን ግንዛቤ በቀደምት ሠለፎች በማድረግ ብቻና ብቻ ነው አንድነታችንን ልንጠብቅ የምንችለው:
☞ ለኡማው አንድነት ወሣኝ ከሆኑ ነጥቦች መካከል
1,ትክክለኛና እወነተኛ የሆነን እምነተ /አቂዳን/ ማሥተናገድ ይህም በሁሉም የእምነት ዘርፍ ሙሥሊሞች የቁርአንእና ሀዲሥን በሠለፎች ግንዛቤ የተገነባ እምነት ያላቸው እንደሆን ፍፁም የሆነ አንድነት እና ህብረት ሊኖራቸው ይችላል በተቃራኒው በስመ ሙሥሊም ብቻ ጨርሦ ተቃራኒና የተለያየ የእምነት አካሔድ / መንሀጅ/ ይዘው ለምሣሌ በአምልኮት ላይ አንዱ አላህን በብቸኝነት አያመለከ ሌላው ሁሴንን እየተገዛ ወይንም አልይን ሥሙንም አብድልሁሤን አብድልአሊ አብዱዘህራ እያለ አምልኮትን ከአላህ ውጪ እየሠጠ መቃብሮችን ወልዮችን እየተገዛ ና እያመለከ እንዲሁም የአላህ ሥሞችን እና የባህርያት መገለጫዎችን በተመለከተ አንዱ አላህን ከፍጡራን እያመሣሠለ ሌላው ጭራሽ ባህሪዎቹን እየገፈፈ እንዲህ ያለ ፍፁም ሊዋሀድ የማይችል አመለካከት እና እምነትን እያሥተናገደ ሙሥሊም ከሚለው ሥያሜ ሌላ ከቶውንም አላውቅም ብሎ መደነጋገር እና ማደነጋገር ምን ይሉታል ደርሦም ባጢል አይነካ ሥለ ቢደአ አይወራ ሙብተዲኦችም አይጠሩ ይመሥላል:: የሠው ሥም አታንሡ በሚል ሽፋን ዳዕዋን እና ዳኢን ለማፈን እነሡ ግን ያለብርሀን የወንድም ሥጋ እየቦጨቁ ለምን አላህ ሙሥሊም ብሎ ሠይሞን ሌላ ተቀፅላሥም ለራሣችን እንሠጣለን በሚል ሽፋን የማንነትን መለያን ለማፈን ብሎም አጥፊዎች ከአልሚዎች እንዳይለዩ ለማድረግ የሚደረግ የተሣሣተ አሥተሣሠብ ለጊዜው የኡማውን አንድነት የሠበሠበ መሥሎ ዳግም አንድ እንዳይሆን የሚበታትን የውሸት አንድነት ነው የሚሆነው ሥለዚህ ወንድሞቼ የአፈ ጮሌዎችን ማታለያ ወደጎን ትተን የቀደምት ሙሥሊሞችን አንድ ወዳደረገው ተውሒድ እና ሡና መጥተን አንድ እንሁን!!!
2,የነብዩን ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ሡናን ህያው ማድረግና ማክበር እንዲሁም የህይወታችን መመርያ ማድረግ እንዳለብን አላህ እንዲህ አለ ((አላህን እና መጨረሻውን ለሚከጅል ለሆነሠው አላህንም በብዙ ለሚያወሣ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ)) {አል አህዛብ} ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ አሉ ((እነሆ ከእኔ ማለፍ ቡሀላ በህይወት የሚቆይ ሠው ብዙ ልዩነነቶችን ያያል ማየቱ አይቀርም በሡናይ አጥብቆ መያዝ አደራ እላቹሀለው ከእኔም ቡሀላ የሚመጡትን ቅንም ፈለግ ጨምሮ)) አቡዳውድ በዚህ ነብያዊ ንግግር ውሥጥ በግልፅ እንደተቀመጠው ልዩነት የማይቀር መሆኑን ከመገለፁ ባሻገር መፍትሔውም በይፋ ተቀምጧል
① ,ሡናን አጥብቆ መያዝ
② ,የሁለፋዎችንም መንገድ መከተል ይህም የሚገለፀው በአቂዳ በኢባዳ በሢያሣ በሌሎችም የህወት ዘርፍ ሁሉ... ዲነል ኢሥላም ሁለት መሠረታዊ የሆኑ አጠቃላይ መርሆች አሉት
¥አንዱ አላህን እንጂ ሌላን አለማምለክ ሲሆን
¥ሁለተኛው ይህንኑ አምልኮ ራሡ አላህበደነገገው /በነብዩ ሡና/ እንጂ አለመፈፀም
3,ለኡማው አንድነት ወሣኝ ከሆኑ ነጥቦች ሁሉንም የቢድአ አይነቾች እንዲሁም የቢድአ አራማጆችን /ሙብተዲእ/ በተጨማሪ ለቢድአና በሙብተዲኦች ዋስትና ጠበቃ የሚሆኑትን ማውገዝ እና ማግለል /ከመምከር እንዲሁም ከመግለፅ በኃላ /ምክንያቱም ቢድዓ በባህሪው ከሸሪያ ውጪ ያለ ተግባር በመሆኑ ልዩነትንና ግጭትን አምጪ ነው ((በዲኑ ላይ አዲስ መጤ የሆኑ ነገሮች ሁሉ ቢደዓ ናቸው ቢደዓ ሁሉ ጥመት ናቸው ጥመትም ሁሉ ለእሳት ይዳርጋል)) ነብዩ ሰለላሁ አለይሒ ወሠለም አቡዳውድ /ቲርሚዝዩ/ ነሳኢ የዘገቡት ታላቁ አሊም ሱፍያን አሰውሪ የቢዲአን አስከፊነት እንዲህ ሲሉ ነበር የገለፁት "ቢድአ ኢብሊስ ዘንድ ከሀጢያት /ማእሲያ /ይልቅ የበለጠ ተወዳጅ ነው ምክነያቱም ሀጥያተኛ የሆነ ሰው ወንጀል ላይ እንዳለ ሰለሚረዳ ተውበት ሊያደርግ ይከጅላል ከሙብተዲኡ በተቃራኒ እሱ ግን (ሙብተዲኡ) ወደ አላህ የሚቃረብ እየመሰለው በወንጀሉ ላይ ይቀጥላል"
"የቢድዓ ባለቤትን ሥም አንስቶ መናገር እደሃሜት አይቆጠርም" አህመድ ኢብኑ ሀምበል
"በቢድአ ሠዎችላይ /ረድ/ መልሥ በመሥጠትላይ የተጠመደ ሠው እርሡ በእውነት /ሙጃሂድ/ ታጋይ ነው" ኢብኑ ተይምያ
"ከእነዝያ አህሉል አህዋ /የቢድአ ሠዎች ትንሽም ሆነ ብዙ እውቀትን አትዘግቡ ተጠንቀቁ ሱናንና የሠለፎችን አሰር/ፋና/ ተከታይ ከሆኑት ብቻ እውቀትን ዘግቡ" ኢብኑ ሀምበል
በአጠቃላይ የመላ ሙሥሊሞችን አንድነት እና ህብረት ለመጠበቅ ብሎም ሠሀቦች እና ታብእዮች የነበሩበትን ሀያልነትና ታላቅነት ለማሥመለሥ የኢሥላም ጉድፍ እና አረም ቢደአዎች እና የቢደአ አራማጆችን ከኢሥላም እና ከሙሥሊሙ ላይ መመንገል የግድ ነው!!!
4,የሠለፎች አሷሊህ /የቀምት ደጋግ አበዎችን /መንገድ በቅን መከተል አላህ እንዲህ አለ "በእርሱ በአመናችሁበት ቢጤ ቢያምኑ በእርግጥ ተመሩ ከዚህ እናንተ ከአመናችሁበት መንገት ቢዞሩም በጭቅጭ ውስጥ ብቻ ናቸው"
አብደላህ ኢብኑ መስኡድ ረዲየላሁ አንሁ . እንዲህብለዋል "መልካም አርያ የፈለገ ሰው ያለፉት ሠዎች አርአያ ያደርግ" አዎን የዢህ አመት /ዘመን ምርጦች እና ፀዱ ልቦና ያላቸው የሆኑትን እነርሱን የነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ሠሀቦች ረዲየላሁ አንሁም ናቸው
ኢማሙ አህመድ እንዲህ ይላሉ "እኛ ዘንድድ የሱና መሰረቶች ማለት ሠሀቦችን ረዲየላሁ አንሁም አርአያ ማድረግና እነሱ የነበሩበትን መንገድ ጠበቅ አድርጎ መያዝ እንዲሁም በዲኑ ላይ አዲስ መጤ የሆነውን ቢድአን መተው ነው"
"አንተ የአላህ ባርያ ሆይ ፍትህን /እውትን/ ትፈልግ እንደሆን በቁርአንና በሀዲስ መልዕክቶች ላይ ፅና ከዚያም ሠሀቦችን እና ታቢዮችን እንዲሁም የተፍሲር ኡለማውች ረዲየላሁ አንሁም ያሉትንም ተመልከት እንዲሁም ከሰለፎች የጠቀሱትን ም ጭምር ከዚያ ውጪ ግን በእውቀት ላይ ሆነ ተናገር ወይም በትግስት ዝም በል"( ኢማሙ ዘሀብይ)
☞☞ እነዚህ ወሣኝ የሆኑ አራት ነገሮችን ያላካተተ አንድነት ምንም ያክል የሠው ብዛት ቢኖረው በኢስላም መሠረት አንድነት ወይም ትክክለኛው አንድነት ነው ሊባል አይችልም በአንፃሩ ደግሞ እነዚህ ነገሮች ባማከለ መልኩ የተሠራ አንድነት በዛ ላይ ያሉ ሠዎች ብዛታቸው አናሣ ቢሆንም ትክክለኛው አንድነት ከመሆን ከልካይ የለውም
ያ! አላህ ሀቅን በሀቅነቱ አሣየን የምንከተለውም አድርገን ባጢልንም በባጢልነቱ አሣየን የምንርቀውም አድርገን!!

Post a Comment

0 Comments