Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ድሮ፣ ድሮ፣ በጣም ድሮ።

ድሮ፣ ድሮ፣ በጣም ድሮ።የሰው ልጅ ተውሂድ ላይ ጠንካራ በነበረ ጊዜ፣ ጂኖች የሰውን ልጅ ይፈሩት ነበር። የሰው ልጅ ይህን ጂኖች ላይ የነበረውን የበላይነት ሽርክ ሲቀላቅልበት በጂኖች ተነጠቀው።አላህን በብቸኝነት ያመለከ፣ አላህን የፈራ ሁሉ ይፈራዋል። አላህን ያመፀ፣ በአላህም ላይ ያጋራ፣ ሁሉንም ይፈራል።የጂኑ፣ የእብዱ፣ የጥቁር እና የመሳሰሉት ከለር ዶሮ እና በግ፣ ለነ ሰይፉ ጨንገሬ፣ አዳል ሞቴ፣ ሻሺ እና የመሳሰሉት ጂኖች፣ በሰው ሰይጣኖች አማካኝነት ሲገብር ይኖራል።የሰው ልጅ ሆይ! ክብርህን በተውሂድ አስጠብቅ። አለበለዚያ የነ ታምራት፣ የነ በይዲ እና የሌሎች ጠንቋዬች መጫወቻ ትሆናለህ/ትሆኛለሽ። ከአላህ ውጭ ያለን ረዳት አድርጎ የያዘ 2 አገር ከሰረ። አላህ ይጠብቀን።አላህ ሆይ! ያንተን ተውሂድ አጥብቀው ከሚይዙት፣ በእርሱም ላይ ኖረው፣ በዚሁ መንገድ ላይ ከሚሞቱት አድርገን። የአላህ ሰላት እና ሰላም በአላህ መላክተኞች ላይ ሁሉ ይስፈን።