Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሃሰነል በስሪይ ረሂመሁላህ:-« እንስቃለን ግን ማን ያውቃል ?

ሃሰነል በስሪይ ረሂመሁላህ:-« እንስቃለን ግን ማን ያውቃል ? አላህ ወደ ከፊል ስራዎቻችን ተመልክቶ.. " ምንም አይነት ስራቹን አልቀበላቹም " ሊለን ይችል ይሆናል !የአደም ልጅ ሆይ ወዮልህ ! አላህን መጣላት ትችላለክን ? አላህን ያልታዘዘ ሁሉ እየተጣላው ነው ፤ በአላህ ይሁንብኝ ሰባ የሚሆኑ የበድር (ጦርነት) ተሳታፊዎችን (በህይወት) አግኝቻለው ፤ አብዛኛው ልብሳቸው ሪዝ (የበግ ፀጉር የሚሰራ ልብስ) ነው ፤ ብታዩዋቸው 'እብዶች' ትሏቸው ነበር ፤ እነርሱም ደሞ ከናንተ መካከል ጥሩ የሚባለውን ሰው ቢያዩ.. " ይህ ሰው የምፅዓት (ቂያም) ቀን ምንም ድርሻ የለውም " ይሉ ነበር ፤ ከናንተ መካከል ደሞ የከፋውን ቢያዩ.. " ይህ ሰው በምፅዓት (ቂያም) ቀን አያምንም " ይሉ ነበር ።
ከሰዎች አይቻለው ይቺ ዓለም እግሩ ስር ካለ ቆሻሻ በላይ ርካሽ የሆነችው ፤ ከሰዎች አይቻለው ማታ ላይ ወደ ቤቱ ሲመለስ ለርሱ ከተቀመጠለት ጥቂት ምግብ ውጪ ቤቱ ውስጥ የማያገኝ ሆኖም እንዲህ የሚል.. " ይሄን ሁሉ ምግብ ሆዴ ውስጥ ብቻዬን አላስገባም (አልበላም) ፤ ለአላህ ብዬ መስጠት አለብኝ " ይልና ፤ የእህሉን የተወሰነ በምፅዋት የሚሰጥ ፤ ምንም እንኳን ለራሱ በጣም ፈልጎት (ርቦት) ቢሆን እንኳን.. »

[አቡ ኑዓይም አል ሂላያ አል አውሊያ]