Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውበት ማን ያድርግ ⁉️

بسم الله الرحمن الرحيم

👉ተውበት ማን ያድርግ ⁉️

በሰሞኑ አስፈሪ ክስተት ብዙሃን ተደነግጠዋል፣ወደአሏህ እንመለስ ጥሪዎችም በርክተዋል አልሀምዱሊላህ። ነገር ግን እነማን ናቸው ከወንጀላቸው ሊቆጠቡ የሚገባቸው የሚለው ሊሰመርበት ይገባዋል።በጥቅሉ ሁላችንም ተውበት (ወደ አሏህ መመለስ) ያስፈልገናል።
በተለይ ደግሞ:በጣም በአንገብጋቢነት >>>

1)  ከሃዲያን:> አሏህ ወለደ፣ተወለደ፣ ተሰቀለ፣ሞተ፣ተነሳ ወዘተ እያላችሁ ፈጣሪያችሁን ከመሳደብ ተመለሱና በሱረት አልኢኽላስ እመኑ (ስለሙ)።
ያልሰለመ ከጀሃነም እሳት አይድንም ‼️

2) ሙሽሪኮች:>  ከምትገዟቸው አማልክት (ሙታን፣ መቃብሮች ፣ ግኡዝ አካላት፣ሰይጣናት፣ሰው ሰራሽ ህጉች፣ ጠንቋዎችና አጥማሚ መሪዎች) ተላቀቁ። የፈጠራችሁን አሏህን ብቻ አምልኩ ከዘለኣለም እሳት ትድናላችሁ ‼️

3) ሙብተዲዖች :> ሙሉዕና ንፁህ በሆነው የአሏህ ዲን ላይ የፈጣጠራችሁትን መጤ አምልኮ ሁሉ እርግፍ አድርጋችሁ ጥርት ወዳለው የሰሃቦችና የምርጥ ቀደምት መንገድ ተጠቅልላችሁ ግቡ። እነዚያ ምርጦች የበቃቸው ኢስላም ይብቃችሁ። ከመውሊድ፣ ከመንዙማ፣ከጫት ኢባዳ፣ ከጀማዐት አተብሊግ ደዕዋ፣ከኢኽዋን ፖለቲካ፣ከሃዳዲያና ኸዋሪጅ ፊትና እና ከሱፊያ ጡሩቆች ተላቀቁ !! በዋነኝነት
ሙስሊሙን የበታተነው  ቢደዓ ነው ‼️

4) አበላሽ ኡስታዞች 
የምታስተምሩትን እና የሚከተላችሁን ህዝብ የምታታልሉ ፣ያለ እውቀት የምትፈተፍቱ፣  የምትሸነግሉ፣የምታወዛግቡ፣ ያወቃችሁትን እውነት የምትደብቁ ፣ከቢደዓ ሰዎች ጋር ተለሳልሳችሁ ወኔ ቢስ እንዲሆን የምታደርጉ ፣መውሊድ አይለየንም እያላችሁ የዘቀጣችሁ፣ሁላችንም ሱፍይ ነን እያላችሁ የቀጠፋችሁ፣ ነብያትና ሰሃቦችን የተሳደባችሁ፣ ለስልጣን ጥማቹ ኢስላምና ሙስሊሙን መረማመጃ ያደረጋችሁ፣የተውሂድን ደዕዋ በአጠቃላይ ሰለፊያን እንቅፋት ሆናችሁ የተዋጋችሁ ሁሉ ከስሜታችሁ ተላቃችሁ በቁርኣን እና ሱና እንደ ምርጥ ቀደምቶች ቀጥ በሉ‼️ አለበለዚያ ግን ከአኼራው በፊት በዱንያ ውርደት ወየውላችሁ ‼️

5) ወንጀለኞች ሁሉ:>
የአሏህን ትዕዛዝ ችላ ብሎ ክልከላዎቹን ሲያተራምስ የነበረ ሁሉ ሊፀፀትና ሊመለስ ይገባል።በግልፅ ከሚታወቁት
ከዝሙት፣ከወለድ፣ከሀሜት፣ከስርቆት፣ከአስካሪ ነገሮች፣ከዘፈንና ነሺዳ ወዘተ ተላቆ ወደ ትዳር (እስከ አራት)፣ሀላል ስራ ፣መልካም ንግግር፣ቁርኣን ወዘተ ተመልሶ ህይወቱን ሊያድስና ከውድቀት ወደ ስኬት ሊቅጣጭ ጊዜው አሁን ነው ‼️
አሏህ አዘናግቶ ከያዘ አያያዙ የበረታ ነው ! 
አሏህም እንዲህ ብሏል:
{فَلَوْلَآ إِذْ جَآءَهُم بَأْسُنَا تَضَرَّعُواْ وَلَٰكِن قَسَتْ قُلُوبُهُمْ وَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيْطَٰنُ مَا كَانُواْ يَعْمَلُونَ}

አቡ ሀመዊያ

Post a Comment

0 Comments