Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሴቶች በቁርኣን ድመፃቸውን ለአጅነብይ ወንድ ማሰማት❓❓❓

بسم الله الرحمن الرحيم 

👉ሴቶች በቁርኣን ድመፃቸውን ለአጅነብይ ወንድ ማሰማት❓❓❓

ታላቁ ሸይኽ አልባኒ እንዲህ ይላሉ:
《ሴቶችን በርቀት መገናኛ ዘዴዎች ቁርኣን የሚያስምር ወንድ _አጅነብይ ከሆነ… ሴቶቹ እየቀሩ ድምፃቸውን ቢያሰሙት የዚህ ብይን ልክ አካላቸውን ሳያይ ድምፃቸውን ከመጋረጃ ጀርባ እንደሰማ ነው። ፊትናው (አደጋው) በሁለቱም መንገድ ይከሰታል።ምክንያቱም በመገናኛም ይሁን በአካል ከሂጃብ በስተጀርባ ድምፇ ያው የሴቷ ድምፅ እራሱ ነው።በእርግጥ የሴት ድምፅ በራሱ ሀፍረት (ዐውረት) አይደለም።ነገር ግን ይህን ለማለት ድምፁ ተፈጥሯዊነቱ እንደለ መሆኑ መስፈርት ነው።ነገር ግን እርሷ ቁርኣን የምትቀራው በጉና (በማረ ድምፅ) ፣ በኢቅላብ (እያገላበጠች) ፣ በኢዝሃር (ግልፅ እያወጣች) ፣ በመድ (ድምፇን በተለያየ ደረጃ እየሳበች) ነው። እንደዚሁም የነብዩ (ﷺ) ንግግርም ይመጣል። 
" لَيْسَ مِنَّا مَنْ لَمْ يَتَغَنَّ بِالْقُرْآنِ ".
 وَزَادَ غَيْرُهُ : يَجْهَرُ بِهِ.(صحيح البخاري)
{ በቁርዓን ድምፁን ከፍ አድርጎ ያላሰማረ ከእኛ አይደለም }ተብሏል።  

ስለዚህ እርሷ ቁርኣንን በቅላፄ ወይም በሚመስጥ ድምፅ መቅራቷ አይቀሬ ነው። እናም ይህን ለጅነብይ ወንድ ማድረግ አይሆንም። ቂርኣቷ በማሰራጫ ጣቢያም ይሁን በቴሌፎን ልዩነት የለውም።》

👌 ፊትናው በሚከተሉት ሁኔታሆች ደግሞ የባሰ የከፋ ስለመሆኑ ጤናማ ልብ ያለው ሁሉ አያውቅምን ⁉️

#1: አስቀሪው ወንድ በሴቶች ድምፅ የሚረካ ልበ በሽተኛ ወይም ደካማ ከሆነስ  ⁉️

#2:  ያላገባ ወጣት ያላገቡ ወጣት ሴቶችን ድምፅ የሚሰማ ከሆነስ ⁉️

#3: ሴቶችን የሚላከፍና የሚያድን  ኡስታዝ መሳይ አደገኛ ቦዘኔ ከሆነስ ⁉️
 
#4: ከሴቶቹ መካከል ድምፅ የሚያቅለሰልሱ፣ ሽቶ የሚቀቡ ከአስተማሪው ጋር የሚቀልዱ ከሆነስ ⁉️

#5: ከአስተማሪው ውጭ ሌሎች ወንዶችም እየሰሟት ከሆነስ ⁉️

#6: ድምፇን ቀድታ (ሪከርድ) ከላከችለትስ ⁉️ 

#7: ይህ ሁሉ የሚሆነው ሌሎች ከኢስላማዊ ድንጋጌዎች ጋር የማይጋጩ በርካታ አማራጮችን በመጠቀም    
መቅራት እተቻለ ከሆነስ ⁉️

እነዚህና ሌሎችም ሁኔታዎች አጅነብይ ወንድ ሴትን ቁርኣን ሲያስተምር ልብ ሊባሉ የሚገባቸው ነጥቦች ለመሆናቸው የዲኑን መቃሲዶች፣ የኡለማዎችን ጥልቅ ምክሮችና ተጨባጩን በንፁህ ልብ ያጤነ ሁሉ ይደርስበታል።

ዲንና ክብርሽን ጠብቂ ❗️❗️

✍ አቡ ሀመዊ

Post a Comment

0 Comments