Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የጁሙዓ ሰላት በኡዝር/በኮሮና ወቅት

🏷️የጁሙዓ ሰላት በኡዝር/በኮሮና ወቅት

🔅ጁሙዓ ሰላት እንዳይሰግድ የሚያደርግ ኡዝር/ምክንያት ያለው ሰው ባለበት ሆኖ የተለመደውን ዙህር ሰላት 4 ረክዓ ይሰግዳል። ጁሙዓ ቀን ላይ ዙህር ከተሰገደ እንደሁኔታው ካገኙት ጀመዓ ጋርም ይሁን በተናጠል/ለብቻ መስገድ ይቻላል።

🔅አብዛኞቹ ዑለማዎች ዘንድ ጁሙዓ ሰላት ቤት ውስጥ በጀማዓም ይሁን በተናጠል አይሰገድም።
ምክንያቱም ጁሙዓ ሰላት የተደነገገው አዛን ወደሚሰማበት መስጂድ/ቦታ በመሄድ ተሰብስቦ በጋራ ለመስገድ ነው።

🔅በመሆኑም ጁሙዓ መስገድ ያልቻለ ሰው በምትኩ የተለመደውን ዙህር ሰላት ነው የሚሰግደው።

ለሰዎች ደህንነት ተብሎ መሰባሰብ በተከለከለበት ሁኔታ ላይ በይፋም ይሁን በድብቅ ተሰባስቦ መስገድ የማይገባ ተግባር ነው።
ነቢዩ ﷺ ጉዞ ላይ ሲሆኑ ኡዝር ስላላቸው ጁሙዓን ትተው ዙህር ይሰግዱ እንደነበረው እኛም ለጁሙዓና ለጀማዓ መሰባሰብን የሚከለክለን ነገር ሲኖር ያለምንም ውስጣዊ ቅሬታ ጁሙዓውን ትተን ዙህር መስገድ እንችላለን።ይህ በእንዲህ እንዳለ በተከበረው ጁሙዓ ቀን ላይ የሚከናወኑ ድርጊቶች (ዒባዳዎች)  ለምሳሌ ትጥበት፣ ሱረቱል-ከህፍ መቅራትና ሰለዋትና ዱዓ ማብዛት ወዘተ ጁሙዓ ለማይሰግድም ሰው ቢሆን ይደረጋሉ።

ጁሙዓና ጀማዓ እንዳንሰግድ ያደረገንን  
በላ/አደጋ አላህ እንድያነሳልንና እንዲጠብቀንም ዱዓ እናብዛ፣ተውበት እናድርግ፣ አቅመ-ደካሞችን እንርዳ
اللهم أرنا رحمتك كما أريتنا قدرتك
ولا تهلكنا بما فعل السفهاء منا
آمين.
ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
9/8/1441ዓ. ሂ@ዛዱል መዓድ
 🔸🔹🔸🔹🔸🔹

Post a Comment

0 Comments