Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዕድለኞች ነን አላህን እናመስግን !!

ዕድለኞች ነን አላህን እናመስግን !!
ጠለሃ ኢብን ዑበይደላህ ረድየላሁአንሁ እንደዘገብው:-
« ሁለት ሰዎች ወደ ረሱል ሰለላሁአለይሂወሰለም ይመጡና በተመሳሳይ ሰዓት ኢስላምን ይቀበላሉ ።
አንደኛው ኢባዳ ላይ በጣም የተበራታ ሲሆን ደሞ ሌላኛው ደሞ ጅሃድን አብዝቶ ይሳተፍ ነበር ፤ እናም አንድ ቀን ጅሃድ ላይ ይገደልና ሸሂድ ይሆናል ፤ አንደኛው እርሱ ሌላኛው ከሞተ ከአንድ ዓመት በኋላ ያርፋል ።
ጠላሃ እንዲህ ይላል " አንድ ቀን በህልሜ ከነዚህ ሁለት ሰዎች ጋር በር ጀነት በር ላይ ቆሜ ነበር ፤ አንድ ነገር ከበሩ ይወጣና ከመጀመሪያው ሟች ቀጥሎ የሞተውን ሰው ግባ ይለዋል ፤ ከዚያም ድጋሚ ይመጣና መጀመሪያ የሞተውን ግባ ይለዋል ፤ ከዚያም ወደኔ ዞር ብሎ 'አንተ ሂድ ተመለስ ያንተ ጊዜ ገና ነው' ይለኛል" ::
ጠለሃ ከዕንቅልፉ እንደተነሳ ስላየው ህልም ለሰዎች ይነግራቸውና ሰዎቹም ይገረማሉ ፤ እናም ይህ ወሬ ረሱል ሰለላሁአለይሂወስኀለም ጋር ይደርሳል ፤ እሳቸውም ሰዎቹን "ምንድር ነው ያስደነቃቹ?" ብለው ይጠይቃሉ ሰዎቹም "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ከነዚህ ሁለቱ ሰዎች አንደኛው ጅሃድን አብዝቶ ይሳተፍ ነበር ሸሂድ ሆኗልም ነገር ግን ቅድሚያ ጀነትን እንዲገባ የተደረገው ቀጥሎ የሞተው ነው" አሏቸው
ረሱል ሰለላሁአለይሂወሰለምም ፤ " ቀድሞ ጀነትን የገባው ሰው ከመጀመሪያው አንድን ዓመት በሂወት አልቆየምን?"
ሰዎቹም አዎን ሲሉ መለሱ ረሱልም ሰለላሁአለይሂወሰለም: " ‪#‎ረመዳንን‬ አላገኘምን ፤
‪#‎አልፆመምን‬ ፤ ይሄንና ይሄን ያክል ሰላት
አልሰገደምን ?"
ሰዎቹም "አዎን" አሉ
ረሱልም ሰለላሁአለይሂወሰለም:- " ታዲያ በሱና በዛ ሰውዬ መካከል የሰማይና የምድር ያክል በላይ ልዩነት አለ" አሏቸው:: »
_____________
ኢብን ማጃህ (2/345, 346) ፤ ሸኽ አልባኒ በሲልሲላ አ'ሰሂሃ ሰሂህ ብለውታል ዘግበውታል


Sultan Khedir