Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የተከበሩት ሸይኽ ሙሐምድ ቢን ዑሰይሚን "የጋራ ጾም ብይኑ ምንድን ነው?

የተከበሩት ሸይኽ ሙሐምድ ቢን ዑሰይሚን 
"የጋራ ጾም ብይኑ ምንድን ነው? ለምሳሌ የተወስኑ ሰዎች ተሰባስበው አንድ ቀን ለምሳሌ፥ ሰኞን ወይም ሐሙስን ለመጾም ይስማማሉ፤ ይህም በመለካም እና አላህን በመፍራት ላይ መተባበር ነውም ይላሉ፤ ሰው ለበቻው ደካማ በወንድሞቹ ጠንካራ ነው፤ የዚህ ብይን ምንድን ነው? " የሚል ጥያቄ ተጠይቀው። 

"ይህ ሱና እንዳልሆነ ነው የሚታየኝ፤ ይልቁንስ በዚህ ላይ ከተስማሙ ከቢድዓህ (ከፈጣራ) ነው ይሚቆጠረው፤ዛረኢ እኛ የጋራ ተክቢር (አላሁ አክበር) ማለትን፣ ወይም የጋራ ዚክር ማድረግ የምናወግዝ ከሆነ፥ ይህም እንደዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ጾም ዒባዳህ (አምልኮት) ነው፤ የጋራ መሆን የለበትም፤ ነገር ግን ሳይስማሙ ቢገጥም ችግር የለውም፥ ለምሳሌ ሰኞ ቀን እንዳጋጣሚ ብንጾም እና እርስ በእርሳችን፥ የጾምን እገሌ ጋር ነው የምናፈጥረው ብንባባል ችግር አይኖረውም፥ ምክንያቱም ገጠመኝ ነው እንጂ የሆነ የዒባዳን (የአምልኮትን) ተግባር ለመፈጸም ተስማምተን አይደልም። ዒባዳን (አምልኮትን) በጋራ አልያም በግል መፈጸም ድንጋጌ ነው፤ ስለሆነም ነው ሰላትን በጀማዓህ (በጋራ) መስገድ አላህ ባይደነግግልን ቢድዓህ (ፈጠራ) ይሆን ነበር፤ ነገር ግን አላህ ደነገገልን። በጋራ ጾምም እንደዛው ነው፤ ቀድሞ በጋራ ለመጾም መስማማት (ቀጠሮ) መያዝ ከፈጠራ ዓይነት ነው። የረመዳን ጾም ሲመጣ በጋራ አይድል የምንጾመው? አዎ! ይህም የሆነበት ድንጋጌ እንዲሁ ስለሆነ ነው፥ ድንጋጌው ሁሉም ሰው በዚህ ወር ውስጥ መጾም ያለባቸው በመሆኑ ነው። ከዚህ ተግባር ሰዎች ቢታቀቡ እላለሁ፤ ማንኛውም ሰው በአላህ ነው ማታገዝ ያለበት፤ ራሱንም ነው ይማቻል ያለብት፤ ማንኛውም ሰው አምልኮትን በድጋፍ (በጋራ ካልተሰራ በስተቀር ) የማይሰራ ከሆነ፥ ወኔው ደካማ ነው፤።" በማለት መልስ ሰጠተዋል።

@tenbihat

Post a Comment

0 Comments