Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቢድዐ ፈተናን ያባብሳል እንጂ አያቃልልም። ቢድዐ ዓለም አቀፍ ሆነ ሃገር አቀፍ የተወገዘ ነው

ቢድዐ ፈተናን ያባብሳል እንጂ አያቃልልም። ቢድዐ ዓለም አቀፍ ሆነ ሃገር አቀፍ የተወገዘ ነው። ከቢድዐ ቆንጆ ይልቅ በርግጠኝነት የዝንጀሮ ቆንጆ ውበት አለው። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "የኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ እርሱ ውድቅ ነው" ብለዋል። 
አሁን ለኮሮና ተብሎ በአለማቀፍ ደረጃ የሚደረገው የፆም ቅስቀሳ የነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አስተምህሮት የሌለበት መሰረተ ቢስ ስራ ነው። "ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው፣ ሰዎች መልካም አድርገው ቢያስቡትም" ይላሉ ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ። በዚህ ዘመን የሚራገቡ ነገሮችን በዲን ስም ስለተወሩ ብቻ ልንሸወድባቸው አይገባም። ታላላቅ የሱና ዑለማዎች በጉዳዩ ላይ ምን እንደሚሉ ልናጣራ ይገባል።

Post a Comment

0 Comments