Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከደረሰው በላይ የከፋ አላማ ነበራቸው


ከደረሰው በላይ የከፋ አላማ ነበራቸው
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
አላህ መልሶት እንጂ በአሕባሽ ቁንጮዎች የተደገሰልን አደጋ ከደረሰው በላይ እጅግ ዘግናኝ ነበር። እስኪ ይህንን ትላንት እሁድ ጥቅምት 30/2012 በሸገር ሬዲዮ ከቀረበው የ "ሙፍቲ" ዑመር ቃለ ምልልስ የተወሰደ ንግግር መላልሳችሁ አስተውሉ!! ይሄው:–
"ለባለስልጣኖቹም፣ ለእነ አባይ ፀሃዬ – የዚያን ግዜ የደህንነት ኃላፊ ነበሩ –
‘ተው እባካችሁ! ይኼ ችግር (#ሰለፍያን ማለቱ ነው) መንግስት ላይ ይወጣል። እኛ ላይ ብቻ ሳይሆን እናንተም ላይ ይደርሳል’ እላቸው ነበር።
በኋላ እንግዲህ በእነመለስ ግዜ እነርሱ ላይ ሲደርስ መጥፋት አለበት ብሎ ያ ሁሉ ችግር ተፈጠረ። መጀመሪያውኑ ከውጥኑ ማጥፋት ይቻል ነበር።"

ተመልከቱ! መንግስት ሳያስብ በፊት አሕባሽ ያልሆኑ ሙስሊሞችን እንዲያጠፋላቸው ሲወተውቱ ነበር ማለት ነው። እነዚህ አቅሙ ቢኖራቸው እንደነ ዮሐንስ አጋድመው ያርዱ ነበር።

ቀጠለ:—
"መንግስት የዚያን ግዜ በጎናችን አልቆመም። መፈለግ አይፈልገውም። ሙስሊሙ ላይ ብቻ ይቀር መስሎታል እንጂ ወደ መንግስት ያልፋል አልመሰለውም። አሁን ሀገሩ በሙሉ ተዳርሷል። ለማጥፋት አልተቻለም። ወደአንድነት መጥተን ሰላም ቢሆን ይሻላል ሀገሩ ብለን ነው። ወደን አይደለም በአንድነት የምንታየው። ማጥፋት ካልተቻለ አብሮ በሚሆንበት ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል በሚል ነው።"

ምንኛ ልብ የሚያደማ ንግግር ነው?! አላ፞ሁል ሙስተዓን! ይሄ እንግዲህ የተሰማው ነው። በርግጠኝነት የተዳፈነው ከዚህ የከፋ ነው። በነዚህ ሰዎች የተሸወዳችሁ አሁንም አልረፈደም። ንቁ! ከነሱ ጋር መጨማለቃችሁን ትታችሁ በጊዜ ሚናችሁን ለዩ።
(یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ لَا تَتَّخِذُوا۟ بِطَانَةࣰ مِّن دُونِكُمۡ لَا یَأۡلُونَكُمۡ خَبَالࣰا وَدُّوا۟ مَا عَنِتُّمۡ قَدۡ بَدَتِ ٱلۡبَغۡضَاۤءُ مِنۡ أَفۡوَ ٰ⁠هِهِمۡ وَمَا تُخۡفِی صُدُورُهُمۡ أَكۡبَرُۚ قَدۡ بَیَّنَّا لَكُمُ ٱلۡـَٔایَـٰتِۖ إِن كُنتُمۡ تَعۡقِلُونَ)
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፡፡ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፡፡ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፡፡ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸው በእርግጥ ተገለጸች፡፡ ልቦቻቸውም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነው፡፡ ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን፡፡" [ኣሊ ዒምራን: 118]

Ibnu Munewor

Post a Comment

0 Comments