Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኧረ እባካችሁ አላህን ፍሩ! የጥፋት በር አትክፈቱ!



ኧረ እባካችሁ አላህን ፍሩ! የጥፋት በር አትክፈቱ! ብዙ ፈሳድ ነው የምታመጡት። አላማችሁ ቢዝነስ ከሆነ ሌላ ሐላል አማራጭ ፈልጉ። አላማችሁ ዲን ከሆነ ኢስላም በድንቁርና አይታገዝም። አዋቂ አማክሩ። ይህን ሳታደርጉ ስንዝር አትራመዱ። ግን ምነው ሃይ ባይ አጣችሁ?! ኧረ ተው ኢስላምን ጠላት ከሚያደርገው በላይ ከውስጥ እየቦረቦራችሁ ነው።
ለመሆኑ ወንዶችን ብቻ ነጥላችሁ ልታስሮጡ ነው? ወይስ ሴቶችን አደባባይ አውጥታችሁ ከወንድ ጋር እያጋፋችሁ ልታስሮጡ ነው? ለመሆኑ በቁምጣ ነው ወይስ በሱሪ የምታስሮጧቸው?! ይህን ያክል በእምነት መነገድ ምን የሚሉት ድፍረት ነው?!
በነገራችን ላይ የዚህ ዝግጅት አላማ አዲስ መልክ ያለው ዘመናዊ የኢኽዋን መውሊድ ነው።

Post a Comment

0 Comments