Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከአመታት በፊት ሙስሊሙን ሙስሊም ነኝ የሚል የቀብር አምላኪ "ሙሽሪክ" ለማድረግ ከአሕባሽ ጋር ብዙ ደባ ተሰራ — በፖለቲከኞቹ ።



ከአመታት በፊት ሙስሊሙን ሙስሊም ነኝ የሚል የቀብር አምላኪ "ሙሽሪክ" ለማድረግ ከአሕባሽ ጋር ብዙ ደባ ተሰራ — በፖለቲከኞቹ ።
ሰው ታሰረ ፣ ተደበደበ ፣ በሴቶች ላይ ግፍ ተሰራ !
ዛሬ ስትራቴጂው ተቀየረና የትናንት የሽርክ አንጃ አሕባሽ የተመረጠና የተወደደ የሙስሊም መሪ ተደርጎ ሊያዝ ቀረበ ። የትናንቱን የሽርክ ቡትቶ ሳይቀይር አሕባሽ ሙስሊሙን ይመራው ጀመረ— ከትናንቱ በረቀቀና በከፋ ተንኮል ።
የግልም ሆነ የመንግስት ሚዲያ የአሕባሹንና የአሽዐሪያውን አቋም በደግ ሲያራግብ ፣ የሱናው ሰውና የሰለፊያው መንገድ ላይ ጥላቻን የሚቀሰቅሱ ነገሮችን በማሰራጨት ስራውን እየሰራ ነው !
ወንድሜ ሰለፊ ወንድሜ ሆይ! ማንም ካንተ ጎን እንዳልሆነ እወቅ! የትኛውም የቢድዐ አንጃ ካንተ ጋር አይደለም! አትጠራጠር! ከሃዲው ደግሞ ከየትኛውም ሙስሊም በበለጠ አንተን ሰለፊዩን ይጠላል!
ለጴንጤው የክህደት ዘመቻ ትልቅ እንቅፋት የሆነው ያንተ የተውሒድ ዳዕዋ ነውና ጴንጤው እጅግ አድርጎ የሚጠላው አንተን ነው! የቀብር አምላኪውን ወደ ክህደቱ ለመጥለፍ አፍታ ያክል አልቆይም ብሎ ያስባልና የሱ ነገር አያሳስበውም ።
አንተ ግን ትልቁ እንቅፋት ነህና ሊያጠፋህ ቀን ተሌት ያስበሃል! ! ንቃ!!
ሌላውም የክህደት መስመር ሰባኪ እንዲህ አድርጎ ይጠላሃል!
ያሁኑን ነጃሳ መጅሊስ ከትናንቱ የተሻለ ብላችሁ በችኮላ ያወደሳችሁ ሁሉ እስኪ ዛሬን ቆም ብላችሁ አስተንትኑ ! ሰዎችን ቸኩላችሁ በችኮላ ከመፈረጅ የራሳችሁን ችኮላ አጢኑ !
ደግሞ ገና ነው! ይሄ ጅምሩ ነው ....

አላህ ሙስሊሙን ከአሕባሽና ከፖለቲከኞች ተንኮል ይጠብቅልን!

Muhammedsirage M Nur Gidey

Post a Comment

0 Comments