Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የኔ ጀግና!


የኔ ጀግና!
~~~~~~
ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ ኢስላምን ያጠለሹ፣ ሙስሊሞችን በአጉል ኮተቶች ጠፍረው ያሰሩ የሱፍያ ኮተቶችን የበጣጠሰ አንበሳ ነው። በጀሊሉ፣ በወሃቡ ፈቃድ የተሃድሶ ንቅናቄው የቀብር አምልኮትን ግንድ ከምድረ ሰዑዲያ ገንድሶታል። በመላው የሙስሊሙ አለም ያለውን የበሰበሰ የሱፍያ ሸክም አነቃንቆታል። ኧረ ክፉኛ ወዝውዞታል።
በዚህ የተነሳ ሱፍዮች ዘንድ እንደሱ የተጠላ ፍጡር የለም። የተፃፈ ኹጥባ ለማንበብ ሚንበር ላይ ወጥቶ የሚንገዳገደው ሁላ እየተነሳ "ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ ጃሂል ነው" ሲል የምንሰማው ያለ ምክንያት አይደለም። ይገባናል፣ የሚያስጮሃችሁ ህመማችሁ ነው። "አሶራኹ ዐላ ቀድሪል አለም" እንዲል ዐረብ። "ጩኸት በህመም ልክ ነው!"
ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ እንዳንተ ሶደቃ ሲያባር እድሜውን አልፈጀም። ጋርዶ ጫት የሚቀረጥፍ ቦዘኔ አልነበረም። ሁሉን እንዳመጣጡ ያስተናገደ፣ ለቆመበት አላማ ቆርጦ የተነሳ፣ ከዚያም እስከ ደም ጠብታ የታገለ ቆራጥ ነበር፣ የጀግና ጀግና! የፅናት፣ የትጋት፣ የብቃት ተምሳሌት!!
ዛሬ ግን ይሄ ነው የሚባል የዒልም ቅሪት የሌለው፣ ኢስላምን የግል ጥቅም መሸመቻ ያደረገ፣ ከሆዱ አሻግሮ መመልከት የማይችል ቦዘኔ ሁላ እየተነሳ "እሱኮ ጃሂል ነበር" ይላል። እርሱ ጃሂል ከነበረ አንተ ጅህልና እራሱ ነህ!!

"ወሃብዮች ዑለማእ አያከብሩም" የሚሉ አስመሳዮች ሁላ በሸይኹ ላይ ምላሳቸውን ሲያሾሉ ማየት በስፋት የተለመደ ነው። ግማሹ "ተክፊር ነው" ይላል። ግማሹ "የሁዲ ነው" ይላል። ግማሹ "የእንግሊዝ ቅጥረኛ ነበር" ይላል። ሌላም ሌላም ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ውንጀላዎች አሉ። እናንተ ናችሁ ስለ ዑለማእ ክብር የምታወሱት? በጀግኖቻችን ክብር ላይ እየተረማመዱ ከዚያ የነሱን የጥፋት ሰባኪዎች እንድናከብርላቸው ይፈልጋሉ።
በሃገራችን በመውሊድ ሰበብ ስማቸው ገኖ ከሚታወቁ ቦታዎች ጋር ተቆራኝቶ ዝናቸው ከናኘ መሻይኾች ውስጥ #ከፊሎቹ የእውነት እንደሚባለው በዒልም የላቁ እንደነበሩ የሚያሳይ ማስረጃ ብትጠይቁ አስቂኝ ነገር ትሰማላችሁ። "እስኪ ኪታባቸውን አሳዩን?" ብትሉ "የመውሊድ መንዙማ ፅፈዋል" "ማዲሕ ነበሩ። መድሕ አዘጋጅተዋል" ብለው የግጥም መድብል ይነግሯልኋል። ዒልም ማለት ግጥም መፃፍ ነው አንዳንድ የዞረባቸው ዘንድ!! በዚህ የግንዛቤ አቅምህ ነው ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብን በጅህልና የምትወርፈው?! አዎ መውሊድ ያገነናቸው ብዙ ስመ ገናናዎች አሉ። ከመውሊድ ጭፈራ ባለፈ ከነ ጭራሹ በቦታው ምንም አይነት የዒልም እንቅስቃሴ የሌለባቸው ብዙ ናቸው።


Ibnu Munewor 

Post a Comment

0 Comments