Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ይድረስ ለመውሊድ አክባሪዎችና በዲናችን ላይ ጥሩ ቢድዓ መፍጠር ይቻላል ለሚሉት


بسم الله الرحمن الرحيم وبه أستعين
"ይድረስ ለመውሊድ አክባሪዎችና በዲናችን ላይ ጥሩ ቢድዓ መፍጠር ይቻላል ለሚሉት"
ሰሞኑን መውሊድን በተመለከተ ለቀረበው ጥያቄ ቀጥተኛ መልስን መመለስ ትተው ጥያቄን በጥያቄ ለመለሱ ሰዎች የተሰጠ አጭር ምላሽና ምክር

🔸 መውሊድ ማክበር የነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትክክለኛ የውዴታ መገለጫ ቢሆን ከነፍሳቸው በላይ ነቢዩን ይወዱ የነበሩ ሰሓቦቻቸው ባከበሩት ነበር፣ግን ከነሱ መሀል አንድም መውሊድ ያከበረ ሰሓቢይ የለም!

አላህ አክብሩ አለማለቱ፣ ሰሓቦችም ይሁን ታቢኢዎች ከዛም በኋላ እስከ አራተኛው ክፍለዘመን የነበሩ ሙስሊሞች
አለማክበራቸውና አክብሩም ብለው አለማዘዛቸው አዲስ መጤ ተግባር መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ፣መውሊድን ከጀመሩ ሰዎች በፊት የነበሩ ሙስሊሞች ነቢዩን ሰለሁ ዐለይሂ ወሰለም በሚገባ አይወዱም ነበር ፣ወይም ደግሞ ከኋላ የመጡት ከፊተኞቹ ይልቅ (ሰሓባዎችንም ጨምሮ) ስለዲኑ ይበልጥ ያውቃሉ ማለትም ይሆናል!
ይህ ደግሞ ነቢዩ ( ጥሩ ሰዎች ማለት እኔ ባለሁበት ክፍለ-ዘመን ያሉ ሰዎች ናቸው! ከዛም ከነሱ ቀጥሎ ያለው ክ/ዘመን ላይ ያሉ፣ ከዛም ከነሱ ቀጥሎ ያለው ክ/ዘመን ላይ ያሉ ናቸው!
ከዛ በኋላ መስክሩ ሳይባሉ የሚመሰክሩ መስክሩ ሲባሉ ደግሞ እምቢ የሚሉ መኃላቸው ንግግራቸውን የሚቀድም ሰዎች ይመጣሉ)
ከሚለው ንግግራቸው ጋር ይጋጫል

🔹ቀደምት ዑለማዎችም ("መልካም ነገር ሁሉ ያለው ደጋግ ቀደምቶችን በመከለተል ነው፣መጥፎ የተባለ ሁሉ ያለው ደግሞ ከኋላ የመጡ ሰዎችን በመከተል ነው" ) ብለዋል

⛤ነቢያችን ሊሞቱ 80ቀናት አካባቢ ሲቀራቸውም አላህ ["ዛሬ ዲኑን ሙሉ አደረግኩላችሁ"]
ብሎን ሳለና፣ መልካምና ወደ አላህ የሚያቃርብን ነገር ሁሉ ያዘዙን ነቢይ መውሊድን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሳያዙ፣ ሰሓቦቻቸውም ይሁን የነሱ ተከታዮች እንዲሁም
አራቱ የዲን መሪዎች
(አቡ ሐኒፋ፣ኢማም ማሊክ፣ ኢማም ሻፊዒይና ኢማም አሕመድ ) ያልሰሩትን ነገር
እየሰራን ወደ አላህ ለመቃረብ መሞከር ትልቅ የሆነ ስህተትና ሞኝነትም ነው!
ስለዲኑ ከነቢዩና ከሰሓቦች በላይ አውቃለሁ ማለትም ነው!👌

በዲን ላይ አዲስን ነገር ከመፍጠርና ከመለጠፍ ነቢያችን አስጠንቀቀውንና
(" ቢድዓ በሙሉ ጥመት ነው") ብለውን ሳለ :-"ጥሩና መጥፎ የሚባል ቢድዓ አለ" ማለት የነቢዩ ንግግር ከሰሓባዎቻቸው የበለጠ እኛ እንረዳለን ማለት ይሆናል!

ቢድዓ ሐሰናና ቢድዓ ሰዪኣ፣ ጥሩና መጥፎ የሚባል ቢድዓ :- አለ የሚለውን ንግግር ውድቅነት ይረዱ ዘንድም እነሆ ደጋግ ቀደምቶቻችን ያሉትን ይነልከቱ፥

🌟" ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው ሰዎች ጥሩ ነው ቢሉም "
☞ ሰሓቢዩ ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር
🌟" ተከተሉ! አዲስ ነገር አትፍጠሩ የሚያስፈልጋችሁ ነገር በሙሉ ተሟልቶላችኋል " ☞ ሰሓቢዩ ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ
🌟 " አደራህን ካንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን መንገድና ፋና ተከተል! አዳዲስ ነገሮችንም ተጠንቀቅ! እነሆ እነሱ ፈጠራ ናቸውንና"
☞ኢማም አቡ ሐኒፋ

🌟 " በዲን ላይ አዲስን ነገር የፈጠረና ጥሩ ነገር ነውም ብሎ ያመነ ሰው ነቢዩ መልዕክታቸውን በአግባቡ አላደረሱም! አጉድለዋል! እንዳለ ይቆጠራል! ምክንያቱም አላህ ["ዛሬ ዲናቹን ሙሉ አደረግኩላችሁ"] ብሏልና"
☞ኢማሙ ማሊክ
(ረዱየላሁ ዐንሁም ወረሒመሁም ጀሚዐን!)

💥በመሆንም መውሊድንም ይሁን ሌሎችን ነቢዩና ሰሓቦች ያልሰሯቸውን ነገሮች በመስራት ወደ አላህ ለመቃረብ ከመሞከር መጠንቀቅና መራቅ ይገባናል! አይ ብለን ያደረግንም እንደሆነ ትርፉ ድካም ብቻ ነው የሚሆነው
👌ምክንያቱም ነቢዩ["በዲናችን ላይ አዲስን ነገር የፈጠረ ስራው ተመላሽ ነው! ተቀባይነት የለውም"] ብለዋል

🔸ከታቢዒዪችም መሀል አንዱ የሚከተከውን ብሏል
("ማንኛውም የነቢዩ ሰሓቦች ያልሰሩት ዒባዳ እናንተ አትስሩት!")

📌ይህ ሆኖ ሳለ አንዳንድ ሰዎች ዑመር ተራዊህ ሰላት እንዲሰገድ አድርጎ ከዛም
(" እቺ ያማረች ቢድዓ ናት ") ብሏል ይላሉ
ዑመር በዚህ ንግግራቸው ማለት የፈለጉት በነቢዩ ዘመን ለተወሰኑ ሌሊቶች ሰግደው ከዛም በኡመታቸው ላይ ግዴታ እንዳይደረግ ብለው በመስጋት ካቆሙት በኋላ የተጀመረ መልካም ነገር ለማለት ፈልገው እንጂ ፣እሳቸው መሰረት የሌለውን ነገር ፈጥረው አልሰሩም

🔹ሌሎች ደግሞ("ነቢዩ ሰኞ እለት ይጾሙ የነበረው መውሊዳቸውን ለማክበር ብለው ነው ይላሉ!")

⛤ከደጋግ ቀደምቶች መሀል አንድ እንኳ ዓሊም ነቢዩ ይጾሙ የነበረው መውሊዳቸውን ለማክበር ብለው ነው ያለ የለም! ይጾሙም የነበረው በየሳምንቱ እንጂ በዓመት አንዴ ረቢዕ አል አወል 12ኛውን ቀን እየጠበቁ አልነበርም!

💥ሲጀምርም ነቢዩ የተወለዱበትን ቀን በትክክል መች እንደሆነ ነቢዩ ራሳቸውም ሆነ ከሰሓቦቻቸው መሀል አንዱ እንኳ አልተናገረም!
ከዛ በኋላ የመጡ ዑለማዎች የተወሰኑት ነቢይ የተወለዱት በረቢዕ አል አወል 9 ላይ ነው ሲሉ ሌሎች 12 ላይ ነው ብለዋል አብዛኞቹ የታሪክ ዑለማዎች የመረጡት 9 ላይ ነው የሚለውን ነው!
ግን በሁሉም ዑለማዎች ስምምነት ነቢያችን የሞቱት በረቢዕ አል አወል (12) ላይ ነው!
እንግዲህ እሳቸው በሞቱበት ቀን ላይ ነው ወዳጅ ነኝ የሚሉ ሰዎች መውሊድ ብለው እየተደሰቱ የሚውሉት!? ምናልባትም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሞቱበት ቀን ላይ ("እንዘን") ማለታቸውም አይቀርም!

💥አንዳንዶች ደግሞ በነቢዩም ዘመን ይሁን በሰሃቦቻቸው ዘመን ቁርኣን አናባቢ አልነበርውም እና መውሊድ ቢድዓ ነው ከተባለ ይህም ቢድዓ መባል አለበት እያሉ ይከራከራሉ!መልሱን እነሆ፥

ቁርኣን ላይ ሐረካት -ፈትሓ ዷምማ ከስራ መቀመጡና መውሊድን ማክበር ምንም ግንኙነት የለውም!

ቁርኣን በነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘመን አንድ ላይ ተሰብስቦ ባይሆንም ተጽፏል! በአቡበከር ዘመን ደግሞ ተሰብስቧል! ዑመር ቁርኣን ይጽፉ የነበሩ ሰዎችን አሳምረው እንዲጽፉ ያዙ ነበር {"ሲንን"}ፊደል ግልፅ አድርገህ አልፃፍክም በማለትም የቀጡትና እርምጃ የወሰዱበት ሰውም አለ!
("በስመላን አሳምሮ የፃፈ ሰው አላህ ወንጀሉን ይምራዋል!") ያሉም አሉ ከሰሃባ ወይም ከታቢኢዮች መሀል!
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱ አናባቢዎች ጽሁፍን ማሳመር ውስጥ የሚገቡ ናቸው

በዑሥማን ኢብኑ ዐፋን ዘመን ደግሞ በሙሉ ሰሓባዎች ስምምነት ቁርኣን ወጥ በሆነ መልኩና ልዩ በሆነ የአፃፃፍ ደንብ ተከትቦ ለኢስላማዊ ሀገራት ተሰራጭቷል

በጊዜው የነበሩ ሰዎች ዓረብኛ ንባባቸው ጥሩ ስለነበረም ያኔ ፈትሓ፣ ዷምማ ወዘተ አልተደረገም ነበር ከጊዜ በኋላ ግን የኢስላም ግዛት እየሰፋና የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ሰዎች ወደ ኢስላም ሲገቡ፣ ዓረብኛም ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር ሲቀላቀልና ቁርኣንን እየሰባበሩ የሚቀሩ ሰዎች ሲበዙ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በጊዜው የነበሩ የዲን ሊቃውንት ቁርኣንን በቀላሉ ለማንበብ የሚረዱና ከስህተትም የሚጠብቁ አናባቢዎችን ለማስቀመጥ ተገደዋል!ምክኒያቱ የተገኘው ያኔ ነው ማለት ነው

በሰሓባዎች ዘመን የግድ አልነበረም
የነቢዩ ውዴታ ግን ሁሌም ዋጅብና የግድ ነው ከመሆኑም ጋር ሰሓባዎች መውሊድን የውዴታ መገከጫ ነው ብለው አላደረጉትም!
👉ይሄንንም -ፈትሓ ዷምማ ወዘተ- ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጉት ታቢኢዮች ናቸው ፣በዓልይ ረዲየላሁ አንሁ ትዕዛዝ የነሕው ትምህርት ህጎችን ያረቀቀው (አቡል-አስወድ አዱአሊይ)አንደሆነም ታሪክ ላይ ተዘግቧል!

ዋናውና ትልቁ ነገር ይህ ተግባር መሰረት ያለውንና ቀድሞውኑ የተጻፈውን ቁርኣን የመጠበቅና አቀራሩን የማቅለል ስራ ነው

መውሊድ ላይ እየተባለ እንዳለው በራሱ ራሱን የቻለ ዒባዳ ነው ተብሎ አይደለም!
ታዲያ ይህ ሆኖ ሳለ መውሊድንና ይህን አንድ ማድረግ ተገቢ ነውን!?

🚩አላህ ሆይ ሁላችንንም ቀናውን መንገድ ምራን !በዲን ላይ አዲስ ነገር ከመፍጠርም ጠብቀን

ኡስታዝ አሕመድ ኣደም
አልኸሚስ 23/3/1438 ዓ'ሂ

Post a Comment

0 Comments