Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ወዴት ወዴት? "ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ" አሉ



ወዴት ወዴት?
"ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ" አሉ
ኧረ ወገን ለምን ያልበላንን እናካለን እንደው ስለ እውነት ሙስሊም ሆኖ "ዚክር" እና "ሶላዋት" የሚጠላ አለ ???
ነው ወይስ ለማስጠቆር ነው? እዚህ ጋር አንድ እንደ ቀልድ የሚነገር ነገር ትዝ አለኝ ወዲህ ነው ነገሩ
አንዱ ለሊት ተነስቶ እየሰገደ ይቆይና መጨረሻ ላይ ዱዓ ሲያደር "አላህ ሆይ ይኸው ሌላው ሲተኛ እኔ ተነስቼ ሰግጄ እየለመንኩህ ነው ዱዓዬን ተቀበለኝ" ይላል ይሄኔ ከጎኑ ለጥ ብሎ የነበረው ወዳጁ ይሄን ሲሰማ አላስችል አለውና ቀና ብሎ "አቦ ዝም ብለህ ዱዓህን አድርግ እኛን ለምን ታስጠቁረናለህ " አለው ይባላል
(ሰነዱ አልተጠቀሰም ዘጋቢውም አይታወቀም ደሊል አይደለም እሺ)
የወንድሞቻችን ማቀሳሰር ስላልደላኝ ነው ይህን ያነሳሁት…
ሐቂቃ ነብዩን መዘከርና ሶላዋት ማብዛት ማንም ስህተት ነው ያለ የለም… ሆሆ ስንትና ስንት አጅር የሚታፈስበትን ማን ወንድ ነው "ጥፋት" ነው የሚለው … የሚል ካለም ሂድ ጥፋ ነው የምንለው ጨምላቃ… በሐቢቢ ቀልድ የለም
ይልቅ ሶላዋቱም ዚክሩም ሐቢቢ ባስተማሩት ሶሓባዎቹ ባደረጉት መልኩ ይሁን ነው የተባለው አራት ነጥብ…
"ረቢዕ ሲገባ ሸይጣን ይበሳጫል " ተባለ ሐቅ እንዴት አባቱ አይበሳጭ ነብዩ የጀሌዎቹን ቁጥር ቀንሰውበት አይደል ድብን ይበል የታባቱ!
ግን እቺ ሾርኒ መውሊድ ማክበር አይቻልም ያለውንም ወረፍ ለማድረግ የምትሞክሯትም ነገር ይደብራል ቢድዓውን እንጂ የነብዩን መወለድ የጠላ የለም ይሄ ሁሉ ሙስሊም ዑማ በእርሳቸው ሰበብ አይደል እንዴ ይህን መተኪያ የሌለውን የኢስላም ፀጋ የተጎናፀፈው ፣ ከሺርክ ጨለማ ወጥቶ በተውሒድ ብርሃን የፈካው ፣ ፍጡርን ከማምለክ ቀንበር ተላቆ የፍጡራን ሁሉ አምላክ አላህ ለማምለክ የበቃው?
ባይሆን አላህም እኮ በተከበረ ቃሉ ታላቅ ፀጋ እንደዋለልን ሲገልፅ መወለዳቸው ሳይሆን ነብይ ሆነው መላካቸውን ነው የገለፀው ይኸው ካላመንከኝ
﴿لَقَد مَنَّ اللَّهُ عَلَى المُؤمِنينَ إِذ بَعَثَ فيهِم رَسولًا مِن أَنفُسِهِم يَتلو عَلَيهِم آياتِهِ وَيُزَكّيهِم وَيُعَلِّمُهُمُ الكِتابَ وَالحِكمَةَ وَإِن كانوا مِن قَبلُ لَفي ضَلالٍ مُبينٍ﴾
"አላህ በምዕመናን ላይ ከጎሳቸው የሆነን በእነርሱ ላይ አንቀጾቹን የሚያነብ ፣ የሚያጠራቸው ፣ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የሆነን መልዕክተኛ በውስጣቸው #በላከ ጊዜ ፣ በእርግጥም #ለገሰላቸው ፤ እነርሱም ከዚያ በፊት በግልፅ ስህተት ውስጥ ነበሩ።"
[Âl-'Imrân: 164]
ይኸው ነው ቃሉ በደንብ አስተንትን ወዳጄ!
ይቺ ሰንጎ መገን ግጥም ጉድ አፈላች እኮ ቤት ካልመታው ብሎ ከሸሪዓ ጋር የሚማታ ግጥም መጻፉ አሳዝኖኛል እንደው ሌላ በ "ቴ" የሚያልቅ ቃል ጠፍቶ ነው በአላህ? ?
ምናለ "ይቅርብኝ እረፍቴ
ጫ* ቤቴ"
ምናልባት " ጀነቴ " ለማለት የፈለጉት ቋንቋዊው ትርጓሜውን "ጀነት" አትክልት ስፍራ ለማለት ይሆን ??? ብዬ አሰብኩ 🤔
﴿وَدَخَلَ جَنَّتَهُ وَهُوَ ظالِمٌ لِنَفسِهِ ﴾
"እርሱም ነፍሱን በዳይ ሆኖ ወደ አትክልቱ ገባ፤"
[Al-Kahf: 35]
እንደ ግሌ እንደው ኡዝር ልፈልግ ብዬ "አለማወቅ" ከሚለው ሌላ ማግኘት አልቻልነኩም
በጣም ይሰቀጥጣል!
ቀይ መስመር ለማለፍ አንሞክራ እናረጋጋው!
ሀይ!
እዛጋ ይሰማል አይደል? ?? አላህ ሐቢቢን እንዲህ በሉ ብሏቸዋል ፦
﴿قُل إِنَّما أَنا بَشَرٌ مِثلُكُم يوحى إِلَيَّ أَنَّما إِلهُكُم إِلهٌ واحِدٌ فَمَن كانَ يَرجو لِقاءَ رَبِّهِ فَليَعمَل عَمَلًا صالِحًا وَلا يُشرِك بِعِبادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا﴾
"እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ፣ ወደኔ የሚወርድልኝ ቢጤያችሁ #ሰው ብቻ ነኝ ፤ ጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው ፤ መልካም ሥራን ይሥራ ፣ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ በላቸው። "
[Al-Kahf: 110]
ወንድሜ በጀነት ውስጥ ትልቁና ምንም ተስተካካይ የሌለው ፀጋ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ሐታ የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ነፍስ በእጁ የሆነችው ጌታችንን አላህ መመልከት ነው!
﴿وُجوهٌ يَومَئِذٍ ناضِرَةٌ۝إِلى رَبِّها ناظِرَةٌ﴾
"ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው * ወደ ጌታቸው (አላህ) ተመልካቾች ናቸው"
[Al-Qiyâmah: 22-23]
ያረብ እኔንም እናንተንም ይህን ታላቅ ፀጋ ይወፍቀን!
ምነው ባልጠፋ ዱዓ ይህን ተመኛችሁ? አኺ የአላህ ራሕመት ሰፊ ነው ፤ እንደቆማችሁበት ሸቀጥ ሱቅ ጠባብ አይደለም! አላህን ሰፋ አድርገህ ለምን ጀነት ከጀነትም ፊርደውሱን እንዲወፍቅህ ጠይቅ! የሐቢቢን ጉርብትና ለምነው!
አላህ ዱዓቹን አይቀበላችሁ ሌላ ምን ይባላል!
አላህ እኔንም እናንተንም የነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ትዕዛዝ ፈፅመን በራሕመቱ ጀነት አስገብቶን ጉርብትናቸውን ይወፍቀን!
ሼር በማድረግ ለወንድሞቻችንና የእነርሱ ዓይነት ምልከታ ላላቸው ሙስሊሞች እናድርስ!
አኹኩም ሐይደር ኸድር
ጥቅምት 26 2012

Post a Comment

0 Comments