Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አታላይ! "አንቱን መዘከሬ ከሆነ ስህተቴ፣ እኔ አንቱን ዘክሬ ይቅርብኝ ጀነቴ!!"


አታላይ!
~
"አንቱን መዘከሬ ከሆነ ስህተቴ፣
እኔ አንቱን ዘክሬ ይቅርብኝ ጀነቴ!!"
~
"ጀነትን አልፈልግም" ማለት የራሳችሁ ምርጫ ነው። ነብዩ ﷺ "ሁሉም ህዝቦቼ ጀነትን ይገባሉ፣ እምቢ ያለ ሲቀር" ብለዋል። እምቢታ ማለት ትእዛዝን አለመቀበል ነው።

"አንቱን መዘከሬ ከሆነ ስህተቴ" የሚለው ግን ቀንዳም ውሸት ነው። በዚህ ቅጥፈት መሰረት:–
~ መውሊድ የማይጨፍር ሰው ነብዩን በሶለዋት አያወሳም ማለት ነው። አይን ያወጣ ቅጥፈት!
~ እሳቸውን ማውሳት ማለት በመውሊድ መጨፈር ከሆነ አመቱን ሙሉ ረስታችሁዋቸው የምታወሷቸው በመውሊድ ቀን ብቻ ነው ማለት ነው።
~ ድግስ ካልተደገሰ፣ ጭፈራ ካልተጨፈረ ነብዩን ﷺ ማውሳት አይቻልም ማለት ነው።
~ በርካታ የመውሊድ ደጋፊዎች ቢድዐ መሆኑን ያምናሉ። የአሕባሾች ቲቪም ሰሞኑን ይህንኑ አረጋግጧል። መውሊድ ከጊዜ በኋላ የመጣ መጤ ፈሊጥ በመሆኑ ላይ ከተስማማችሁ፣ እሳቸውን ማውሳት ማለት መውሊድ መጨፈር ከሆነ ይሄ መውሊድ ከመጀመሩ በፊት ያለፉት ሶሐቦች፣ ታቢዒዮች፣ አትባዑ ታቢዒን፣ አኢማዎች ሁሉ ነብዩን ﷺ አውስተው አያውቁም ማለት ነው። ከዚህ በላይ ቅጥፈት አለ?!
~ እነዚህ ሰዎች ዘንድ ነብዩን ﷺ ማውሳት ማለት አመት ጠብቆ መዝለል፣ መደለቅ፣ መደነስ ነው። ሎጂካችሁ ጭፈራቸውና ዝላያቸው እየሱስን ከመውደድ የተነሳ እንደሆነ ከሚሞግቱት ጴንጤዎች ጋር ያመሳስላችኋል። እንዲያውም ቅጥፈት ከመሆኑም ጋር የነሱ ሎጂክ ከናንተ ሎጂክ ይሻላል። የሚያስጨፍራችሁ "ኢሽቅ" (ፍቅር) ከሆነ በአመት አንድ ጊዜ ከሚጨፍረው ይልቅ በየሳምንቱ የሚጨፍረው የበለጠ ያፈቅራል ማለት ነው። ይልቅ እሳቸውን በመውደድ እያመሃኘ ከፊሉ እንጀራውን ሲያበስል፣ ከፊሉ የጭፈራ ሱሱን ሲያስተነፍስ፣ ሌላው ለብልግና አጋጣሚውን ሲጠቀም፣ ሌላው ደግሞ እንዲሁ ምኑም ሳይገባው
"ሲሉ ሰማሁ ብየ፣
እላለሁ ነብየ"
የሚል የደመቀ አጫፋሪ ነው። እናንተ ከየትኞቹ ናችሁ?

Post a Comment

0 Comments