Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

"ሃይማኖቴን ልቀይረው እችላለሁ። ብሄሬን ግን ልቀይረው አልችልም"

"ሃይማኖቴን ልቀይረው እችላለሁ። ብሄሬን ግን ልቀይረው አልችልም"
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
እንዲህ የሚሉ ብሄርን ከእምነት በላይ የሚያጎሉ መርዛማ ፈላስፎችን እያየን ነው ደግሞ። ለምን የናቴ ልጅ አትሆንም! ብሄርህ እንድለይህ እንጂ እንድወድህ ወይም እንድጠላህ የሚያደርገኝ አምስት ሳንቲም ያክል ዋጋ የለውም። መርጬና ወድጄ የያዝኩትን እምነት መርጬ ካልወጣሁበት ብሄር ፈፅሞ አላስቀድምም።
~ በቀብር የምጠየቀው ስለ እምነቴ እንጂ ስለ ብሄሬ አይደለም።
~ ዘላለማዊ ህይወቴን፣ የነገ ቤቴን የሚወስነው እምነቴ እንጂ ብሄሬ አይደለም።
~ ከጌታዬ ዘንድ ያለኝን ዋጋ የሚወስነው እምነቴ እንጂ ብሄሬ አይደለም።
~ አሰላስየ፣ አገናዝቤ የምከተለው እምነቴን እንጂ ብሄሬን አይደለም። በብሄሬ ጉዳይማ ሽራፊ ታክል የኔ ምርጫም፣ አስተዋፅኦም የለም። ያልመረጥኩትን ከመረጥኩት አላስቀድምም።
እናም እልሃለሁ! ለእምነቴ ፀር ከሆንክ እዚሁ ሃገሬ ውስጥ ከሚገኘው የሌላ ብሄር ሙስሊም ቀርቶ ከውቅያኖስ ማዶ ብሩኒ ወይም ኒውዚላንድ ከሚገኘው ከማያውቀኝ፣ ከማላውቀው ሙስሊም አላስቀድምህም። ኧረ አላወዳድርህም!! "በብሄርኮ አንድ ነን" አትበለኝ። ለምን የናቴ ልጅ አትሆንም?! ምኔም አይደለህም ስልህ?!

Post a Comment

0 Comments