Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢስላማዊ እውቀት ከሚሰጥባቸው ቦታዎች ከመራቅ እንጠንቀቅ❗️

ኢስላማዊ እውቀት ከሚሰጥባቸው ቦታዎች ከመራቅ እንጠንቀቅ❗️
ከአቢ ደርዳዕ መልካም ስራውን አላህ ይውደድለት:– (አስተማሪ ሁን፣ ወይም ተማሪ ሁን፣ አለያም አዳማጭ ሁን፣ አራተኛ እንዳትሆን ትጠፋለህ።)
አዋቂ አስተማሪ ሁን፣ አለያም ተማሪ ተግባሪ ሁን፣ ካልሆነም ሰምቶ ተግባሪ ሁን፣ አራተኛ ሰው ግን አትሁን አደጋ አለው❗️

ኡመር ኢብኑል ኸጣብ (መልካም ስራቸውን  አላህ ይውደድላቸውና) እንዲህ ይላሉ:–

"አንድ ሰው ካለበት ስፋራ የተራራ ያህል ወንጀል ኖሮበት ይወጣል፣ እውቀት ሲሰማ ግን ይፈራል ወደ አላህ ተፀፅቶ ይመለሳል! ከዚያም ወደቦታው ምንም ወንጀል የሌለበት ሆኖ ይመለሳል! የኡለማዎችን መቀማመጫ ቦታ አትለዩ"
ምንጭ:– መዳሪጅ አስሳሊኪን 1/122
አደራችሁን የዑላማዎችን መቀማመጫና ኢልም ከሚሰጥባቸው ቦታዎች አንራቅ! ኢስላማዊ እውቀት ከሚሰማባቸው ቦታዎች የተራራቀ ሰው እወቁ አደጋ ላይ ነው‼️

✍🏻ኢብን ሽፋ 03/04/1439 ዓ.  ሂ

Post a Comment

0 Comments