Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሒዝቢያህ(ሒዝቢይነት)

☑️ሒዝቢያህ(ሒዝቢይነት)
📢 السُّــــــؤَالُ:
و تعريف الحزبية؟ وما هو حكمها؟
سُئل الشَّـيخ العلّامــة عُبَيْد بنُ عَبدُ الله الجَابِرِي -حـَفِظَهُ الله-:
↪️ሸይኽ ዑበይድ ኢብኑ ዐብደላህ አልጃቢሪይ አላህ ይጠብቃቸውና《ሒዝቢያህ ማለት ምን ማለት ነው? ኢስላማዊ ብይኑስ(ሁክሙስ) ምንድነው? ተብለው ተጠይቀው ሲመልሱ
http://miraath.net/quesdownload.php?id=1448
📣 الجَــــوَابُ:
↪️በእርግጥ ይህ ወሳኝና እጅግ ጠቃሚ ጥያቄ ነው። በመሆኑም ይህንን ጥያቄ ከሁለት አቅጣጫ ነው መመለስ የሚገባው
👈 الأول: في معنى الحزبية وأقول أحسنت إذ سألت هذا السؤال فإن كثيراً من الناس يمقت الحزبية ولا يعلم معناها وقد يقع فيها وهو لا يدري فالحزبية هي الانحياز إلى شخص أو أشخاص أو جماعة غير جماعة أهل السنة والجماعة وهي السلفية
1ኛ:አብዛሀኛው ህዝበ_ሙስሊም ሒዝቢያን የሚጠላ ሲሆን ይሁንና ሒዝቢያን በአግባቡ ባለመረዳት ሒዝቢይነት ውስጥ ሲወድቅ ይታያል።
አብዛሀኛው ሙስሊም ሒዝቢያህ ማለት በግለሰቦች ወይም በስብስቦች(በጀማዓዎች) ዙሪያ የሚሽከረከሩ ከትክክለኛው የኢስላም የእምነት ጎዳና ጋር ፍፁም የተነጣጠሉና ከአህለሱና ወልጀማዓህ አሰለፊያህ ውጭ የሆኑ መሆናቸውን አያውቁም።
 ⬅️وقد ينحازوا إلى عدة جماعات فتجده ينحاز على سبيل المثال إلى جماعة التبليغ وجماعة الإخوان وجماعة الجهاد وغيرها من الجماعات الدعوية الحديثة التي كُلها ضالة مُضلة أقول ذلك ولا أجد فيه غضاضة لأني أدين الله به فتجده يوالي فيمن انحاز إليه جماعة أو فردا او أفراداً يوالي ويعادي فيهم.
↪️በሚገባ ማወቅ ያለብን ቁምነገር ዛሬ ላይ ያለው አብዛሀኛው ቁጥር ሙስሊም ራሱን ሰዎች ወደመሰረቷቸው ጀምዓዎች እንደ ተብሊግ ጀማዓ፣ ኢኽዋነልሙስሊንና ጂሀድ አራማጅ በሚል ወደ ተደራጁ ጀምዓዎች የሚደገፍና ለዚህው ጀማዓ የሚወግን ሲሆን እነዚህ ጀምዓዎች ከትክክለኛው ከኢስላም አስተምህሮት ከሱና(ከሰለፊያህ) ያፈነገጡ ሂዝቢዮች መሆናቸውን የማያውቅ  መሆኑ ነው።
ማንኛውም ሙስሊም ከትክክለኛው የኢስላም አስተምህሮት ከአህለሱና ወልጀማዓህ አሰለፊያህ ውጭ የሆነን ጀምዓ የሚከተል ከሆነ ሂዝቢይ(ለግለሰቦችና ለስብስቦች(ለጀማዓዎች) የሚወግን) እንጂ ለሀቅ የሚወግን አይባልም።》ብለዋል።
⬅️ وإلى هذا أشار شيخ الإسلام بابن تيمية - رحمه الله - بقوله (ومن نصب للناس رجلا يوالي ويعادي فيه فهو من الذين فرقوا دينهم وكانوا شيعا)
↪️ለዚህም ነው ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ አላህ ይዘንላቸውና ማንኛውም ሰው ትክክለኛውን የኢስላምን አስተምህሮት ከመከትል ይልቅ እነ እከሌ ያሉበት እነ እከሌ የሚመሩት እነ እከሌ እነ እከሌ…ካለ እሱ ከእነዛ አላህ ቁርአን ውስጥ ዲናቸውን የከፋፈሉ ካላቸው መጥፎ ሰዎች ነው ሚመደበው።》 ብለዋል
⬅️ بهذا التقرير المُفصل إن شاء الله تعالى أظنك أدركت معنى الحزبية فهي مأخوذة من التحزب.
 ↪️ስለዚህ ከትክክለኛው ከኢስላም አስተምህሮት ውጪ ያለን አስተሳሰብንም ሆነ ግለሰብን አለያም ጀምዓን የሚከተል ከሆነ ሒዝቢይነት(ህዝባዊነት) አራማጅ እንጂ ሱኑይ ሊሆን አይችልም።
⬅️ وأما الشق الثاني: وهو سؤالك عن حكمها:
هي بدعة وضلال , فمن تحزب إلى غير الجماعة السلفية وهم أهل الحديث وأهل الأثر والطائفة المنصورة والفرقة الناجية وأهل السنة والجماعة , فهذا واقع في الحزبية المقيتة وهو من الذين فرقوا 
دينهم وكانوا شيعا نعم“.
2ኛ:ሌላው ማውቅ ያለብን ቁምነገር ደግሞ የሒዝቢያህ ብይኑ(ሑክሙ) ማንኛውም ከትክክለኛው የኢስላም አስተምህሮት ጎዳና ከአህለሱና ወልጀማዓህ፣ ከሰለፊያህ ከጣኢፈቱልመንሱራ፣ከአህሉልሐዲሶች ጎዳና እንዲሁም ከፊርቀቱናጂያ የእምነት ጎዳና ከሱና ውጪ ያለን የእምነት ጎዳና ከተከተለ ሒዝቢያህ(ሀሒዝቢይነት) ላይ ወድቋል።
የሒዝቢያህ የእምነት ጎዳና ደግሞ ከትክክለኛው የኢስላም  እምነት ከሱና ጎዳና ያፈነገጠ ፍፁም ስህተት የሆነ የጥመት ጎዳና ነው ።
📚🔊رابـط الصوتيــة :
✍️አቡ ኢብራሂም
ህዳር 03/03/2012 ዓ ል
ረቢዕል አወል 16/03/1441 ዓ ሂ

Post a Comment

0 Comments