Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አጫጭር ቀሚሶችን መልበስ!

አጫጭር ቀሚሶችን መልበስ!
ሴቶች አጫጭር ቀሚሶችን መልበስን በተመለከተ ለታላቁ ፈቂህ አል-አል'ላማህ ሸይኽ ሙሀመድ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) ጥያቄ ቀረበላቸውና በጥበባዊው ምላሻቸው እንዲህ መከሩሽ።
1ሴቶች እቤታቸው ውስጥ አጫጭር ልብሶችን መልበስ ይፈቀድላቸዋልን ?
“ በቤቷ ከሆነና ከባሏ ውጭ ሌላ ወንድ የሌለ ካልሆነ በስተቀር አጭር ልብስ መልበስ አይገባትም። (ባሏ) ከሌላ ሰው ጋር ባለበት ሁኔታ አጭር ልብስ ወይም ጠባብ እንዲሁም ገላዋን የሚያሳይ ስስ የሆነ ልብስ መልበስ አይፈቀድላትም።
ነቢዩ ﷺ "የእሳት ሰዎች የሆኑ ሁለት አይነት ሰዎች ካሉ በኋላ ለብሰው ያልለበሱ ሴቶች …፣ ጀነትን አይገቧትም። ሽታዋንም አያገኟትም።” ብለዋልና።
በመሆኑም ሴት ልጅ አጭር ልብስ ወይም ጠባብ ወይም ከውስጡ ቆዳን የሚያሳይ ስስ ልብስ ከለበሰች በትክክልም ይህች ሴት "ለብሰው ያልለበሱት ሴቶች" ከተባሉት ትመደባለች። በላይዋ ላይ ልብስ ስላለ ለብሳለች ይባላል። ልብሱ ግን (ገላዋን ለመደበቅ) ምንም ስለማይጠቅማት አልለበሰችም።”
ምንጭ፡ መጅሙዕ ፈታዋ ኢብኑ ዑሰይሚን ☞⇘⇘(12/268)
2 ሴቶች ለሴቶችስ እንዴት ይልበሱ?
አሁንም ታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሙሀመድ ሷሊህ አልዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) ቀጣዩን ያስገነዝቡናል።
“ ሴት ልጅ ሴቶች ዘንድ መሸፈን የሚገባት የሰውነቷ ክፍል ከመዳፎቿ ማብቂያ እስከ ተረከዟ የሆነውን ክፍል ነው። የተደነገገውም ይኸው ነው። ነገር ግን በቤት ውስጥ ሴቶች ዘንድ ለስራና ለመሳሰሉት ጉዳዮች ከዚህ በላይ መግለጥ ካስፈለጋት ቀሚሷን እስከ ጉልበቷ ብትሰበስብ እንዲሁም ለእጆቿም እጅጌዋን እስከ ክርኗ ብትሰበስብ ላስፈላጊ ጉዳይ ብቻ እስከሆነ ድረስ ይፈቀድላታል። ይሁንና ይህንን አለባበስ (ሴቶች ዘንድ ብቻ ቢሆንም) የሁል ግዜ ባህሏ አድርጋ መልበሱ ግን አይሆንም።”
ምንጭ ⇘⇘
فتاوى الشيخ محمد بن صالح العثيمين لمجلة الدعوة " العدد 1765 / 55.



ተንቢሀት - ሙስሊም ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት Tenbihat - Rulings Pertaining to Muslim Women

Post a Comment

0 Comments