Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሴቶች ከወንዶች ጋር እንደ ልብ መቀላቀል ስለመከልከላቸው


ሴቶች ከወንዶች ጋር እንደ ልብ መቀላቀል ስለመከልከላቸው
ከአቢ ኡሰይድ አል አንሷሪይ ረዲየላሁ ዐንሁ እንደተወራልን

የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) ከእለታት አንድ ቀን ከመስጂድ በመውጣት ላይ ሳሉ ወንዶች ከሴቶች ጋር በመንገድ ላይ ተቀላቅለው ተመለከቱ ይህንን ክስተት በማስመልከትም:-
📃‹‹ከወንዶች ወደ ኋላ ሁኑ፤ የመንገዱንም መሀከል ይዛችሁ ልትጓዙ አይገባም፤ የመንገዱን ጥግ ያዙ ›› አሉ፡፡ 
ይህንን ሀዲስ ያወራልን ሰሀቢይ ክስተቱን እንዲህ ሲል ገለፀ:
📜 ‹‹ከዚያ በኋላ ሴቶች በጣም ወደ ዳር ከመውጣታቸው የተነሳ ልብሳቸው በአጥር ይያዝ ነበር፡፡›› በማለት ይናገራል፡፡

📇[አቡዳውድ ሱነናቸው ላይ ሲዘግቡት አልባኒ ሀሰን የሚል ደረጃ ሰጥተውታል]

ከሐዲሱ የምንማራቸው ነጥቦች
•••••••••••••••••••••••••••••••••
1• ሴቶች መስጂድ በመሄድ የግዴታን ሰላት ከወንዶች ጋር መስገዳቸው የተፈቀደ መሆኑን
2• ሴቶች ከወንዶች ጋር ከሚያነካካቸውና ከሚያጋፋቸው እንቅስቃሴዎች መራቅ እንዳለባቸው
3• እንኳንስ ለዱንያዊ ጉዳያቸው ሲንቀሳቀሱ ይቅርና ለኢባዳ እንኳን በሚወጡበት ግዜ በተቻላቸው አቅም ከወንዶች ጋር ልቅ በሆነ ሁኔታ ከመቀላቀል መቆጠብ እንዳለባቸው
4• ለፈተና የሚዳርግ ወይም ብዙሃኑን ጎጂ የሆነ ነገር ሲታይ እውቀቱና አቅሙ ያለው ሰው በዝምታ ማለፍ እንደሌለበት
5• አንድን ስህተት በምንቃወምበት ግዜ በጥሩ ስርአት መሆን እንዳለበትና መፍትሄውንም መስረዳት ተገቢ እንደሆነ
6• ሰሃቢያት አላህ ከሁሉም ላይ ስራዎቻቸውን ይውደድላቸውና ፤ ግዴታቸውን ለመወጣት፣ ትእዛዝ ለማክበር ምን ያህል ትጉህ እንደነበሩ
7• አንድን የአላህ ትእዛዝ ለመተግበር ስንንቀሳቀስ ሌላውን ትእዛዝ ወይም ደንብ መጣስ እንደሌለብን
8• ሰሃቢያት የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከወንዶች እንዳይጋፉ ሲለዩአቸው :
ምን ችግር አለው፣ ኒያችንን አላህ ያውቃል፣ የመጣነው ለኢባዳ ነው፣
የመሳሰሉትን ራስን መሸንገያ ቃላቶች እንዳላንፀባረቁና ጭራሽ ልብሳቸው በአጥር እስኪያዝ ድረስ ከፈተና ለመራቅ ይጠነቀቁ እንደነበር ተምረንበታል።
አላህ ሀቅን ያሳውቀን ባወቅነውም የምንሰራበት ያድርገን።

Post a Comment

0 Comments