╔══════ ❁✿❁ ══════╗
ዑለማዎቻችንን እንተዋወቅ‼️
╚══════ ❁✿❁ ══════╝
╔══════ ❁✿❁ ══════╗
አቡ ሐኒፋ፡ (80-150 ዓ.ሂ)
╚══════ ❁✿❁ ══════╝
***********************
===============
✍️ሙሉ ስማቸው አቡ ሐኒፋ ኑዕማን ኢብን ሣቢት ኢብን ዙውጣ ኢብን መርዙባን (أبو حنيفة نعمان بن ثابت بن زوطا بن مرزبان) ይባላሉ።
በ80 ዓ.ሂ በአሁኗ ኢራቅ ውስጥ በምትገኘው በኩፋ ከተማ ተወለዱ።
ይህ ዘመን ኃያሉ የዑመያድ አስተዳዳሪ ዓብዱል መሊክ ኢብን መርዋን በስልጣን ላይ ያለበት ዘመን ነበር።
አባታቸው ሣቢት ኢብን ዙውጣ በአሁኗ አፍጋኒስታን ከምትገኘው የካቡል ከተማ አልባሳትና ቁሳቁሶችን በማምጣት የሚሰሩ ነጋደ ነበሩ።
የዘር ግንዳቸው ከፐርሽያ እንደሚመዘዝ ይነገራል።
አቡ ሐኒፋ በልጅነታቸው ከአባታቸው ጋር በመሆን በሐር ልብስ በመነገድ አሳልፈዋል።
አባታቸው ሣቢት ኢብን ዙውጣ አቡ ሐኒፋን ሲወልዱ የአርባ አመት ጎልማሳ ነበሩ።
✍️በወጣትነት ጊዚያቸውም ወደ ዓረቢያ ሂጃዝ ክልል በመሄድ በመካና በመዲና በሚገኙ ታላላቅ ዓሊሞች ላይ ተምረዋል።
✔️ፊቂህን ከኢማሙ ሐማድ፣
✔️ሐዲሥን ከኢማሙ ሸዓቢ ተምረዋል።
ከኢማሙ ሐማድ ሁለት ሺህ ያክል ሐዲሦችን ይዘዋል።
✔️ከኢማም ጃዕፈር ኢብን ሙሐመድ ሷዲቅ፣
✔️ከአዲ ኢብን ሣቢት፣
✔️ከመንሱር ኢብን ዑመርና ከሌሎችም ታላላቅ ዓሊሞች ላይ ተምረዋል።
✍️አቡ ሐኒፋ የተወለዱት ነብያችን ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከሞቱ ከ67 አመታት በኋላ ነበር።
በህይወታቸው እያሉ የነብዩን ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሶሐቦች በህይወት ሳሉ አግኝተዋል።
ከነርሱም ሐዲሥ አስተላልፈዋል።
በህይወት ያገኟቸውን የሶሐቦች ብዛት በተመለከተ የተለያዩ ዓሊሞች የተለያዩ ሃሳቦችን ሰንዝረዋል።
ሐፊዝ ኢብኑ ሐጀር ስምንት ብቻ ናቸው ሲሉ፣ የ"አል-ኸይራት አል-ሒሳን" ኪታብ ደራሲ ደግሞ 60 ሶሐቦች ናቸው ብለዋል።
ሐፊዝ አልሚዚ ደግሞ ሰባ ሁለት ናቸው ሲሉ ኢማም ሳሒብ ሃያ ስድስት ናቸው ብለዋል።
👉ከነዚህም ውስጥ የነብዩ አገልጋይና ተንከባካቢ የነበረው
✔️አነስ ኢብኑ ማሊክ፣
✔️ጃቢር ኢብን ዓብደላህ፣
✔️ሰህል ኢብኑ ሰዒድ፣
✔️አቡ ጡፈይል አሚር ኢብኑ ዋሲላህና ሌሎችም ሶሐቦች ይገኙበታል።
አቡ ጡፈይል አሚር ኢብኑ ዋሲላህ የሞተው አቡ ሐኒፋ የሃያ አመት ታዳጊ ሳሉ ነበር።
👉ከተማሪዎቻቸው መካከል፦
--------------------------
✔️ታዋቂው ኢማም አቡ ዩሱፍ፣
✔️ዓብደላህ ኢብኑ ሙባረክ፣
✔️ሐማድ ኢብን አቡ ሐኒፋ፣
✔️ዩኑስ ኢብኑ ኢስሐቅ፣
✔️አቡበክር ኢብኑ አያህ፣
✔️ዑበይዱልሏህ ኢብኑ ሙሳ፣
✔️ሙጚራ ኢብኑ ኢቅሳምና ሌሎችም ይገኙበታል።
.
👉ከስራወቻቸው መካከል፦
--------------------------
በሁለቱ ተማሪወቻቸው በአቡ ዩሱፍና በሙሐመድ አልሸይባኒ የተዘገበው ሰባ ሺህ ሐዲሦችን የያዘው
✔️"ኪታቡል አሰር" አንዱና ዋነኛው ነው።
✔️"ፊቂሁል አክበር": ሙስነድ ኢማሙል አዕዞም፣
✔️"ዓሊም ወል ሙተዓሊም"፣
✔️"ኪታቡል ረድ ዓለል ቀደሪያህ"ና ሌሎችም ይገኙበታል።
.
✍️አቡ ሐኒፋ ከአራቱ ታላላቅ የፊቂህ አኢማዎች ውስጥ አንዱ ናቸው።
የሐነፍያ የፊቂህ ትምህርት በርሳቸው መዝሃብ ስም የተቋቋመ ነው።
አቡ ሐኒፋ በብዙዎች ዘንድ ኢማሙል አዕዞም (ታላቁ ኢማም) {The Great Imam)፣
ሲራጁል አኢማ (የአኢማዎች መብራት) (The Lamp of Imams) በመባል ይታወቃሉ።
"አቡ ሐኒፋ" የኩንያ ስማቸው ነው።
ተማሪያቸው አቡ ዩሱፍ በሃሩን ራሺድ የኺላፋ ዘመን ጊዜ ቃዲ ሆኖ ተሹሟል።
.
✍️አቡ ሐኒፋ ከመሞታቸው አራት አመታት በፊት፡
አል-መንሱር የተባለ የአባሲዶች ገዥ አቡ ሐኒፋን በአስተዳደሩ ስር የቃዲዎች ቃዲ አድርጎ መሾም ፈለገ።
እርሳቸው ራሳቸውን ከማስተናነስ አንጻር ለአል-መንሱር እንዲህ አሉት፦
"እኔ ለዚህ ቦታ አልመጥንም!!"
አል-መንሱርም አቡ ሐኒፋን "ዋሽተሃል!" ብሎ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አደረገ።
እርሳቸውም እንዲህ አሉት፦
"ዋሽተሃል ካልክ፡ የኔ ንግግር እጥፍ እውነት ነበር።
ምክንያቱም እንደት አንተ ውሸታምን ቃዲ አድርገህ ትሾማለህ?"
ለዚህ ቦታ አልመጥንም ማለቴ አይጋጭም አሉ።
ከዚያም ይበልጥ ወደ እስር ቤት እንዲወረወሩ ተደረጉ።
በእስር ቤት ውስጥም ብዙ እንግልትና ስቃይ ደረሰባቸው።
ብዙም ሳይቆዩ ከአራት አመታት በኋላ ባልታወቀ ምክንያት እዚያው እስር ቤት ውስጥ በ150 ዓ.ሂ በሰባ አመታቸው ህይወታቸው አለፈ።
በቀብር ስነ ስርአታቸው እለትም ከሃምሳ ሺህ በላይ የሚያክል ህዝብ ተገኝቷል።
ታላቅ ታብዒይ ናቸው።
አላህ ይማራቸው።
ጀነተል ፊርደውስን ይወፍቃቸው።
"በፊቂህ ትምህርታቸው ውስጥ ከቁርአንና ከሐዲሥ ውጭ ተቃርኖ የተገኘ ሃሳብ ካለ፣
በዚያ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የርሳቸውን እይታ ትተን ቁርአንና ሐዲሥ ያለውን እንድንከተል አዘዋል።"
||
************************
"ክፍል: ሁለት [2]" ይቀጥላል።
//
ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ
_________
==>(Murad Tadesse)
ሶፈር 23, 1440 ዓ.ሂ
ጥቅምት 22, 2011 E.C
November 1, 2018 G.C
_________________________
"ማሳመርን እንጂ ሌላን አልሻም‼️"
0 Comments