Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለኩፍር በዓላት መልካም መመኘትና መሳተፍ

ለኩፍር በዓላት መልካም መመኘትና መሳተፍ
የዘመናችን ፈቂህ ሸይኽ ሷሊህ አል-ዑሠይሚን (ረሂመሁላህ) አንድ ሰው በነዚህ በዓላት ላይ እንዲገኝ ግብዣ ቢቀርብለት ሊቀበል አይገባም ይላሉ። አያይዘውም አንድ ሰው በነሱ በዓል ላይ መመሳሰሉ ወይም ስጦታ መቀባበሉ አሊያም ምግብና ጣፋጮችን መስጠቱ የተከለከለ ነው ይላሉ።
.
እውቁ ዓሊም ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) ... ካፊሮችን በነዚህ ክብረ በዓላት መመሳሰል በእነርሱ የውሸት እምነትና ስራ ሰውየው መማረኩን ያሳያል። ይህ ደግሞ ካፊሮች ደካማውን እንዲያሸማቅቁ እና እንዲያጠሙ ተስፋ ይሰጣቸዋል ይላሉ።
.
ሸይኽ ዑሠይሚንም (ረሂመሁላህ) ... ምንም እንኳ ሰውየው ይህን የሚያደርገው ካለው ለስላሳ ባህሪ ወይም አይናፋርነት ወይም ጓደኝነት የመነጨ ቢሆንም ከወንጀለኝነት አይድንም ይላሉ። እንዳውም ነገርየው እስከ ኒፋቅ እንደሚሄድ እና ከሀድያን በሀይማኖታቸው ኩራት እንዲሰማቸው እንደሚያደርግ ይገልፃሉ።
.
በተጨማሪም በዓላቱ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ዘፈንና ጭፈራ፣ የሴቶች መገላለጥ፣ የወንድና ሴት መቀላቀል (እንዳውም ለብልግና መፈላለግ) ይኖራል:: እንዲሁም በዓላቱ አስካሪ መጠጥ ስለሚኖርባቸው በዚህ የሚሳተፉ ሙስሊሞች እነኝህን ፀያፍና ከባባድ ሐራም ተግባራት እንዲፈፅሙ ሰበብ ሆኗል።
.
ይህም ጥቂት ለማይባሉ ሙስሊሞች ከዲናቸው መራቅ፣ ወንጀል ውስጥ መዘፈቅ፣ በቢድዓ መሸወድ እና ከሀድያንን መከተል ብሎም ኩፍር ውስጥ መግባት ምክንያት ሁኗል።
.
ይህ ሊበቃ ይገባል!
.
ሼር እናርግ ሙስሊሞችን እንታደግ! እናስታውስ!

Post a Comment

0 Comments