💥 ከ ሠ ለ ፎ ች ማ ኅ ደ ር💥
ተውሂድ የፅናት፣ የጥንካሬ፣ የንቃት፣ የጉብዝናና የስኬት ቀዳሚውና ዋነኛው ሞተር መሆኑን የሚያሳይ ራስን የሚያስታዝብ የሠለፎች ወግ
※ ዘጋቢ:- ኢብኑ ቁዳማ አልመቅደሲይ
※ ተራኪ:- አብዱልዋሂድ ቢን ዘይድ
※ ባለታሪክ:- በተውሂድ የነገሰ ደግ ባሪያ
※ ምንጭ:- ኪታቡ-ተዋቢን ገፅ 179
※ ታሪክ:- የተውሂድ ላይ ፅናት
አብዱልዋሂድ ቢን ዘይድ ከሀሰን አልበስሪይ ተማሪዎች አንዱ ናቸው። በሒጅሪያ 177 ከዚህ ዓለም ተለይተዋል። በህይወት ዘመናቸው ያጋጠማቸውን ታሪክ እንዲህ ያጫውቱናል ረሂመሁሙላህ☞
«ባንድ ወቅት በመርከብ ተሳፍረን እየተጓዝን ሳለ ነፋሱ ወደ ደሴት ገፍቶ ወሰደንና ከመርከቧ ወረድን። እዚያች ደሴት ላይ አንድ ሰው ጣዖት እያመለከ አየነውና ወደሱ ሄደን "አንተ ሰው ምንድነው የምታመልከው?" ብለን ጠየቅነው። እሱም ጣዖቱን አሳየን።
እኛም "ይኸኮ የሚመለክ አምላክ አይደለም።" ስንለው "እናንተስ ምንድነው የምታመልኩት?" ኣለን።
"አላህን ነው የምናመልከው።" ስንለው
"አላህ ምንድነው?" ሲል ጠየቀን።
"አላህ ማለት ያ ዙፋኑ በሰማይ ሆኖ ስልጣኑ ደግሞ በምድርም ያለውና ውሳኔው በህይወት ባሉትም በሞቱትም ላይ የሆነው ነው።" ኣልነው።
ቀጠለና "እንዴት ኣወቃችሁት?" ኣለን።
"ይኸ ታላቅ የሆነ ንጉስና ሃያል ፈጣሪ የተከበረ መልእክተኛውን ወደኛ ላከልንና ይህን ጉዳይ ነገረን።" ስንለው
"ታዲያ መልእክተኛው ከምን ደረሰ?" ኣለን።
"መልእክቱን ኣደረሰን ከዚያም አላህ ህይወቱን ወደራሱ ወሰደው።" ኣልነው።
"ታዲያ የሆነ ምልክት እናንተ ዘንድ አልተወምን?" ሲለን
"እንዴታ… ትቷል እንጂ።" ኣልነው።
"ምንድነው የተወው? " ኣለን
እኛም "ከሃያሉ ንጉስ የተሰጠውን መፅሃፍ ትቶልናል።" ኣልነው።
"የንጉሱን መፅሃፍ አሳዩኝ። መቸም የንጉሶች መፅሃፍ የግድ ቆንጆ መሆን አለበት።" ኣለንና ቁርኣንን አምጥተን ሰጠነው።
ከዚያም "ይኸንን መፅሃፍ ኣላውቀውም።" ኣለን። እኛም ከቁርኣኑ ምዕራፎች አነበብንለት። ንባቡን በቀጠልን ቁጥርም እሱ ያለቅሳል። እኛም ምዕራፉን እስክንጨርስ እናነብለታለን እሱም ያለቅስ ነበር።
ከዚያም "የዚህ ንግግር ባለቤት ላይ ማመፅ ትዕዛዙን መጣስ አይገባም።" ኣለን። ወዲያውም እስልምናን ተቀበለ። እኛም የኢስላምን ህጎችና ደንቦች እንዲሁም ቁርኣንን አስተማርነውና በመርከባችን አሳፍረነው ይዘነው ሄድን።
ታዲያ በመጓዝ ላይ ሳለን መሸብንና ሲጨልም በየመኝታችን ተኛን። ይህን ግዜ "ይኸ ያመላከታችሁኝ አምላክ ሌሊቱ ሲጨልም ያንቀላፋል እንዴ?" ኣለን።
"አንተ የአላህ ባርያ ሆይ! እሱማ ህያው የሆነ ሁሌም ያልለ ሃያል ነውና አያንቀላፋም።" ኣልነው።
" ታዲያ ጌታችሁ የማይተኛ፣ የማያንቀላፋ ሆኖ ሳለ እናንተ የምትተኙ ከሆነ የማትረቡ ባሮች ናችሁ ማለት ነው።" ኣለንና እኛን ትቶን አላህን ማምለኩን ተያያዘው።
ሃገራችን እንደደረስንም ለጓደኞቼ "ይኸ ሰው ወደ እስልምና በቅርብ የገባና ለሃገሩም እንግዳ ነው።" ብዬኣቸው ገንዘብ ሰብስበንለት ነበርና ወስደን ስንሰጠው "ምንድነው እሱ?" ኣለን።
"ለሚያስፈልጉህ ጉዳዮች ማስፈፀሚያ ታውለዋለህ" ኣልነው።
"ላ ኢላሀ ኢለላህ" ከአላህ በስተቀር በሀቅ ሊመለክ የሚገባው አምላክ የለም! በባህር ደሴቶች ላይ ሳለሁ እሱን ትቼ ጣዖትን ሳመልክ እንዲሁ ያልተወኝ ጌታዬ አሁን እሱን አውቄ ሳለሁ ይተወኛልና ነው እርዳታ የምታደርጉልኝ?! " ኣለንና ለሚያስፈልገው ጉዳይ ሁሉ ለራሱ ወጪውን ለመቻል ተንቀሳቅሶ መስራት ጀመረ። በዚሁ መልኩ እስኪሞት ድረስ ከታላላቅ ሷሊሆች አንዱ ሆኖ ይኖር ነበር። [ረሂመሁላህ]
ከግዜያት በኋላ "ያ ሰው እኮ በጣም ታምሞ በሞት አፋፍ ላይ ነው" በሚል ተነገረኝና ልጠይቀው ሄድኩኝ "የሚያስፈልግህ ነገር አለ ወይ" ብዬም ጠየቅኩት። "የሚያስፈልገኝንማ ያ ወደዚያች ደሴቴ እንድትመጡ ያደረጋችሁ ፈፀመልኝ።" ኣለኝ።
እሱ ዘንድ ቆየሁና እንቅልፌ መጥቶብኝ አይኖቼ ሲያሸልቡ እዚያው ተኛሁ። በዚሁ አጋጣሚ ስለሱ ህልም አየሁኝ። ከዚያም ጭንቅ ብሎኝ ስነቃ ከዚህች ዓለም ተለይቷል።
ከዚያም አጠብኩት፣ ከፈንም አለበስኩትና ቀበርኩት። እለቱ መሽቶ ሲጨልም ተኛሁ። በህልሜም ከአንዲት ውብ ልጃገረድ ጋር ሆኖ ተቀምጦ ባለበት
{وَالْمَلائِكَةُ يَدْخُلُونَ عَلَيْهِمْ مِنْ كُلِّ بَابٍ سَلامٌ عَلَيْكُمْ بِمَا صَبَرْتُمْ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ}[الرعد: 23 – 24] .
“ በመታገሳችሁ በናንተ ላይ ሠላም ይስፈን እያሉ በሁሉም በሮች መላእክት (ሊያበስሯቸው) ወደነሱ ይገባሉ። ከበስተኋላም የተዘጋጀላችሁ ሀገር ምንኛ ያማረ ነው።” የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ ሲያነብ በህልሜ አየሁት።» ሲሉ አብዱልዋሂድ ቢን ዘይድ መልካም ገጠመኛቸውን አካፈሉን። ረሂመሁሙላሁ አጅመዒን።
[ كتاب التوابين: 179]
ከዚህ ታሪክ እንደምንረዳው አንድ ሰው የተውሂድ መልዕክት በትክክል ገብቶት፣ የሚፈፅመውን የአምልኮ ተግባር ሁሉ ለብቸኛው ፈጣሪ ጌታችን ብቻ ካደረገና ከጣዖት አምልኮ ከራቀ በዚህች አለም ሆነ በወዲያኛው ዓለም የተሳካ ህይወትን እንደሚጎናፀፍ ነው።
ተውሂድን የያዘ ግንዛቤው የተስተካከለ ነው። ተውሂድን ያነገበ ስለ ዱንያው አይጨናነቅም። በሰውም ላይ ሸክም አይሆንም። ኑሮውን ለማሸነፍ ጥሮ ግሮና ይህን ያመቻቸለትን ጌታውን አመስግኖ በደስታ ይኖራል።
የተውሂድ ትምህርት ውስብስብና ከባድ አይደለም። ለዚህም ነው ያ ዘላን ገጠሬ በእንግዶች የተነገረውን ነገር ወዲያውና በቀላሉ የተረዳው። እያደረግክ ያለኸው አምልኮት ነው። የምታመልከው ደግሞ ፍጡርን ነው። ፍጡር ደግሞ ሊመለክ አይገባውምና ይኸን ትተህ አምልኮ የሚገባውን አምላክ ተገዛ ሲሉት። ሳያወላውል ነው ስህተቱን የተረዳውና ይኸንን በምን አወቃችሁ ሲል ተገርሞ የጠየቃቸው።
ተውሂድ በልቡ የሰረፀ ሰው እዩኝ እዩኝ አይልም። ራሱንም ከፍ አድርጎ ሰዎች በዙሪያው እንዲሰበሰቡ፣ ስጦታና ሰደቃ እንዲያበረክቱለት፣ የሚናገረውን እንዲቀባበሉለት የሚጥር ሳይሆን ባገኘው አጋጣሚ ጌታው ከሱ የሚፈልገውን በመፈፀም በአምልኮ ላይ ፀንቶ ይጓዛል። አላህ ግን የዚህ አይነቱ ባሪያው በሰዎች ዘንድ ቦታ እንዲኖረውና በመልካም አማኝነቱ እንዲዘከር ያደርገዋል። በውናቸው ሆነ በህልማቸው መልካሙን እንዲያዩለት ያደርጋልም።
≅≅≅≅≅≅≅≅≅
✍Abufewzan
ረመዳን 08/1439
May 24/2018

0 Comments