#መጃሊስ_ሸህሩ_ረመዷን
መጅሊስ 1 ፦ #የረመዷን_ወር_ትሩፋቱን_በተመለከተ
የረመዷን ወር ብዙ ትሩፋቶች እንዳሉት በቁርአን እና በሀዲስ መጥቷል። ከነዚህም ውስጥ ከቁርአን ፦
{ شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ }
[ (እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ] (በቀራ ፥ 185)
°
ከሀዲስ ውስጥ
የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦
[ የረመዷን ወር በመጣ ጊዜ የጀነት በራፎች ይከፈታሉ ፤ የእሳት በራፎች ይዘጋሉ ፤ ሸይጧኖችም ይታሰራሉ ] (ቡኻሪ ፥ 1799 / ሙስሊም ፥ 1079)
ምክንያቱም መልካም ስራዎች ስለሚበራከቱ እና ሰሪዎቹንም ለማነሳሳት ሲባል የጀነት በሮች ይከፈታሉ ፤ እንደዚሁ ከኢማን ሰዎች ወንጀሎች ስለሚቀንሱ የጀሃነም በሮች ይዘጋሉ።
°
ኢማሙ አሕመድ (2/292 ፤ ) በዘገቡት ሐዲስ ላይ ነብዩ - ﷺ - ለረመዷን ወር አምስት ትሩፋቶችን ጠቅሰዋል።
1.የፆመኛ ሰው የአፉ መቀየር ሽታ አላህ ዘንድ ከሚስክ ሽቶ የበለጠ ተወዳጅ ነው።
2.መላኢካዎች ለፆመኞች ፆማቸውን እስኪያፈጥሩ ድረስ የአላህን መሃርታ ይጠይቁላቸዋል።
3.አላህ በየቀኑ ጀነትን ያጌጣታል ፤ ከዛም ሷሊህ የሆኑ ባሪያዎቼ እኮ ችግር እና ጣጣን ሊያወርዱ ይቀርባሉ ወደአንቺም ይቀርባሉ በማለት አላህ ይናገራል።
4.ከሸይጣኖች ውስጥ ሀይለኛ የሚባሉት በሰንሰለቶች እና በመቆለፊያዎች ይታሰራሉ።
5.በዚህ ወር መጨረሻ ላይ አላህ -ሱብሀነሑወተዓላ- ለነብዩ - ﷺ - ህዝቦች ይህንን ወር በፆም እና ሶላትን ቀጥ አድርገው በመስገድ ካሳለፉት ወንጀላቸውን ይምርላቸዋል።
°
አላህ -ሱብሀነሑወተዓላ- በዚህ ወር ምክንያት በባሪያዎቹ ላይ በ3አይነት መልኩ ውለታን ውሏል።
1.ወንጀላቸው እንዲማርላቸው እና ደረጃቸው ከፍ እንዲልላቸው ሲባል በዚህ ወር መልካም ስራን ደንግጎላቸዋል።
2.በአላህ እገዛ መልካምን ስራ እንዲሰሩ አግርቶላቸዋል። የአላህ እገዛ እና መገጠም ባይኖር ኖሮ መልካምን ስራ ባልሰሩ ነበር።
3.መልካም ስራዎች ላይ ብዙ ምንዳዎች እንዲገኙ አድርጓል። አንድ መልካም ስራ ከአስር እስከ 700 እጥፍ እንደ ሰውዬው ኢኽላስ ደግሞ ከዚህም በላይ እጥፍ ድርብ እንዲሆን አድርጓል።
______________________________________
ምንጭ ፦ መጃሊሱ ሸህሩ ረመዷን ሊብኒ ኡሰይሚን ከገጽ 7-11
✍️ኢብን ያህያ አህመድ @ Ibn yahya Ahmed
ሚያዚያ 19/2010
ለሌሎች ሙሀደራዎች፣ደርሶች፤ አጠር አጠር ያሉ የነቢዩ ሀዲሶችን እና የሰለፎችን ንግግር ለማግኘት ይህን የቴሌግራም ቻናል ጆይን ያድርጉ፦
https://telegram.me/ibnyahya7

0 Comments