Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አሳዛኝ እውነታ! በአሁኑ ሰዓት ህዝባችንን ይበልጥ የሚያስደነግጠው ወንጀል የቱ ነው?

አሳዛኝ እውነታ!
በአሁኑ ሰዓት ህዝባችንን ይበልጥ የሚያስደነግጠው ወንጀል የቱ ነው? ለምሳሌ አንድ የመስጂድ ኢማም
ሀ/ ሺርክ ሲሰራ ቢታይ፣
ለ/ ሰው ሲገድል ቢታይ፣
ሐ/ የጎረቤቱን ሚስት ሲያባልግ ቢታይ
የትኛው ነው ይበልጥ የሚያሸማቅቀው? እነዚህ ጥፋቶች ሁሉም ከከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ጉድንም ጉድ ይበልጠዋልና አንዱ ካንዱ ይበላለጣሉ፡፡ የተጠቀሱት ሁለቱ ጥፋቶች ከሺርክ ጋር የሚስተካከሉ አይደሉም፡፡ ሶሐባው ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡-
سَأَلْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : أَيُّ الذَّنْبِ أَعْظَمُ عِنْدَ اللَّهِ ؟ قَالَ : أَنْ تَجْعَلَ لِلَّهِ نِدًّا وَهُوَ خَلَقَكَ ". قُلْتُ : إِنَّ ذَلِكَ لَعَظِيمٌ، قُلْتُ : ثُمَّ أَيُّ ؟ قَالَ : " وَأَنْ تَقْتُلَ وَلَدَكَ ؛ تَخَافُ أَنْ يَطْعَمَ مَعَكَ ". قُلْتُ : ثُمَّ أَيُّ ؟ قَالَ : " أَنْ تُزَانِيَ حَلِيلَةَ جَارِكَ ".
“ነብዩን ﷺ ‘ከወንጀል ሁሉ አላህ ዘንድ ከባዱ የትኛው ነው?’ ስል ጠየቅኳቸው። እሳቸውም {የፈጠረህ እሱ ሆኖ ሳለ ለአላህ ብጤን ማድረግህ ነው} አሉኝ። ‘ይሄ በርግጥም ከባድ ነው!’ አልኩኝ። ‘ከዚያ ቀጥሎስ የትኛው ነው?’ ስላቸው፡ {ካንተ ጋር መብላቱን ሰግተህ ልጅህን መግደልህ ነው} አሉኝ። ‘ከዚያ ቀጥሎስ የትኛው ነው?’ አልኩኝ። {ከጎረቤትህ ሚስት ጋር ዝሙት መፈፀምህ ነው} አሉኝ።” [ቡኻሪ፡ 4477፣ ሙስሊም፡ 267]

ይህንን እንያዝና የህዝባችንን ግንዛቤ እንታዘብ፡፡ ከሚከፋው ወንጀል ይልቅ የሚያስደነግጠው በንፅፅር ቀላሉ ነው፡፡ ለተውሒድ ከተገነባው የአላህ ቤት ከሚፈፀመው ሺርክ ይልቅ የሚሰቀጥጠን በስውር የሚፈፀሙት ብልግናዎች ናቸው፡፡ በርግጥ ሁሉም ያስደነግጣሉ፡፡ ግን ለከፋው ያለን እይታ ለምን ያነሰ ሆነ? ይበልጥ የሚያስደነግጠው ደግሞ ይሄ የተንሻፈፈ እይታ የተራው ህዝብ ችግር ብቻ አለመሆኑ ነው፡፡ ዱዓቶች፣ አስተማሪዎች ሳይቀሩ ይበልጥ የሚወተውቱት ስለየቱ እንደሆነ ተመልከቱ፡፡ ይበልጥ የሚያሳፍረው ደግሞ ከነ ጭራሹ የችግሩንም መኖር የሚክዱ አታላይ ሰባኪዎች መኖራቸው ነው፡፡
وإن كنت لا تدري فتلك مصيبة وإن كنت تدري فالمصيبة أعظم


Ibnu Munewor

Post a Comment

0 Comments