Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነሺዳ ይወዳሉ?!

("ነሺዳ ይወዳሉ?!")
🕯{ቁርኣንን ከመስማት ይልቅ ግጥሞችን የመስማት ፍላጎትና ጉጉት ያለው ሰው
የአላህና የንግግሩ (የቁርኣን) ውዴታ ልቡ ውስጥ ያለመኖር ትልቅ ምልክት ነው!}
አል-ኢማሞ ኢብኑ ቀይሚል ጀውዚያ
[አል-ጀዋቡልካፊ ገፅ ٢٣٦]

🔘ሸይኹ ይህንን ንግግር የተናገሩት ከስድስት መቶ ዓመት በፊት ነው:-
ዛሬ ሙስሊሙ ወጣት ያለበትን ሁኔታ ቢመለከቱ ምን ሊሉ ነበር!?
📒ቁርኣን ሲሰሙ ምንም የማይመስላቸው በነሺዳ ግን የሚያነቡና ኢማናቸው የጨመረ የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው!
📍ሸይጣን አመሳስሎባቸው እንጂ በዜማና በዘፈን ኢማን አይጨምርም!
ይልቁንስ ቀልብ ይደርቃል ከቁርኣንም ይሸሻል
☞የዲን ዕውቀት የሌላቸው
ባለባበሳቸውም ይሁን በሌሎች ነገሮች የነቢዩን
صلى الله عليه وسلم
📌ሱንና የማይከተሉ ባቀራረባቸውም ከከሃዲያንና ከፋሲቅ ዘፋኞች ጋር የሚመሳሰሉና ልክ እንደነሱም ወንድና ሴት ተቀላቅሎ በተቀመጡባቸው መድረኮች ላይ እየቀረቡ በኢስላም ስም ኢስላምን የሚያደፈርሱ
በደዕዋ ስም ወደ ሌላ ነገር የሚጣሩ ወገኖች አላህን ሊፈሩ ይገባል ዲኑን መኻደም ፈልገው ከሆነም ቁርኣንና ሐዲሥን መሰረት ባደረገ መልኩ ሊሆን ይገባዋል!
⭐️ዲኑን የማንም መጫወቻ አናድርገው
🔸ስሜታችንንም አንከተል ስሜት በዱኒያ ለጥመት በአኼራ ለእሳት ይዳርጋልና!
اللهم ارزقنا حلاوة كتابك وتلاوته آناء الليل وأطراف النهار
⭐️አላህ ሆይ፦ የቁርኣንን ጥፍጥና ስጠን❗️
🔸ቀን ከሌሊት በአግባቡ ከሚያነቡት ባሪያዎችህም አድርገን❗️
👌 ልብ ይበሉ: ደጋግ ቀደምቶች (ቁርኣንና ዘፈን የአንድ ግለሰብ ልብ ውስጥ አይሰበሰቡም) ይሉ ነበር
🔸የዘመኑን ነሺዳዎች ከዘፈን መለየት በጣም እየከበደ ነው!
ነሺዳን ዘወትር በማድመጥ የተፈተናችሁ ወንድምና እህቶቼ ሆይ፦ ነሺዳ በማድመጥ ለጊዜው ስሜታዊ ከመሆን ውጪ ያገኛችሁት ጥቅም አለ?!
⭐️ቶብቱ ወደ ቁርኣን ተመለሱ
🔸ቁርኣንን በማድመጥ ብቻ ቀልብ ይረጥባል!
🔸ወንጀል ይራገፋል ኢማን ይጨምራል
🔸የአላህ ውዴታም ይሸመታል
🍃አላህ ቀልብ ይስጠን " ኣሚን !!
✍️ አሕመድ ኣደም
ሙሐረም 5/1438

Post a Comment

0 Comments