🕳እንዴት እህትማማችነት ይገኛል ?
⚬በእህቶች ላይ ያለ ከባድ በሽታና ሊታከም የሚገባው
በአብዛኛው በነገሮች ላይ ትኩረት ሰጥተን ከመወያየት ይልቅ ቀዳዳዎችን በማስፋት ነገርን ከሚገባው በላይ በማክበድ ነገሩ እንደተከሰተ በማሰብና ራሳችንን በማሳመንም ጭምር ፣የሌሎችንም አስተሳሰብ መስረቅና መቀየር፣
⚬የጉዳዩ ባለቤት ጋ በግለፅ ከመነጋገር ይልቅ ምንም በማያውቁት ጉዳይ ሳናውቀው ሌሎችንም የወንጀል ተባባሪ ማድረግ በሰው ላይ ማሳመፅና ስም ማስጠፋት
⚬የእህቶቻችንን ጥሩ እንቅስቃሴ በበጎ አለማየትና አለመቀበል ከበስተጀርባው የሆነ ነገር አስባ ነው ብሎ ማሰብ ብቻ ሳይሆን ማመን ፣በዚህም የተነሳ
የእህቶችን ቅስም መስበርና አንገቷን እንድትደፋ ማድረግ
👌ወላሂ ይህ በእርግጥም በጣም ትልቅ በሽታ ነው!
⛔የጥላቻ፣የምቀኝነት፣የፋሲቅነት የጥርጣሬ ብቻ መንገድ ነው
❗
↪ለልጆቻችንም ይህኑ ቅርስ ነው የምናወርሰው?
📌አላህን እንፍራ፣የራሳችን ወንጀል ሳይበቃ ሌሎችንም አንበክል፣ በዚህ መልኩ እንዴት እህትማማችነት ይመጣል ተብሎ ይታሰባል? በፍፁም አይመጣም! ይህን የተበላሸ አስተሳሰብ ይዘን
⛤መፍትሄው መጀመሪያ ለለውጥ ራስን ማዘጋጀት፣ በግልፅ የመነጋገር ጥፋተኛ ከሆንን ቢመረንም መቀበል፣ቂም አለመያዝ፣ጥፋተኛ ካልሆንም የአሸናፊነት ስሜት ሳይኖር ይህንን ልምድ ማዳበር ተማምረን ተራርመን ማለፍ፣ እህታችንን በሰፊና በንፁህ ልብ መቀበል ይህ ሁሉ ጠፍቶ ፍቅር፣መተሳሰብና መተዛዘን
እውነተኛው እህትማማችነት ይመጣ ነበር !!
አላህ ሰፊ አስተሳሰብና ይቅር ባይነትን ይስጠን
ወላሁአዕለም
📝ኡሙ አብዱረህማን ሩቀያ
March1/2017
©ተንቢሃት