እነሆ እናንተ ቁጥራችሁ አናሳ ነው የውጭና የውስጥ ጠላታችሁም ብዙ ናቸው
"ከበስተኋላችሁ የትዕግስት ዘመን አለ በዛ ጊዜ ዲኑን አሳምሮ ለያዘና እዛ ላይም ለጸና ሰው ከናንተ-ከሰሓባዎች- ውስጥ የ50 ሸሂድ ምንዳ አለው!"
ነገ ሐቁ ይወጣል፣አቧራው ሲወገድ እየጋለቡበት የነበረው ፈረስ ይሁን አህያም ይታወቃል
🕹ታገሱ ባይተወርነትና ብቸኝነት አይሰማችሁ ወገን ዘመድ መክዳቱና ማግለሉም አይክበዳችሁ
የነቃፊ መብዛትና የተከታይ ማነስም ምንም አይጎዳውም
🕹ታገሱ አላዋቂዎችና በአላህና በአኼራ ትክክለኛውን ኢማን ያላመኑ ሰዎች ተግባር ወዳልሆነ አቅጣጫ እንድታመሩ አያድርጋችሁ፣
በውስጥና በውጭ ጠላቶች ስማችሁ መጥፋቱም ብዙ አይክበዳችሁ፣ የረዳቶች ማነስም አይበግራችሁ
فطوبى للغرباء
ዱኒያና በርሷ ላይ ያሉ ብልጭልጮችና አላዋቂዎች አኼራቸውን የሚያበላሹለት ነገር ሁሉ ጠፊ ነው
ብለዋልና ነቢያችን!
☞ሐቁን ለማጠልሸት ባለቤቱቹንም ለማሰናከል መጣራቸው ግን አይቀርም
ስለዚህም በርቱ በዓላማችሁ ላይ ጽኑ
✍ኡስታዝ አሕመድ ኣደም
ቅዳሜ 5/6/1438
