Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለሱብሒ ሰላት በወቅቱ ለመነሳት የሚረዱ ነገሮች

🍃ለሱብሒ ሰላት በወቅቱ ለመነሳት
የሚረዱ ነገሮች🍃
ሱብሒ ሰላትን በአግባቡና በወቅቱ መስገድ የትክክለኛ አማኝነት ምልክት ነው
ሱብሒ ሰላት ላይ መዘናጋት ደግሞ የሙናፊቅ ባህሪይ ነው!
🔸የህይወት ሚስጥር የገባቸው ከፈርዱ ፈጅር ሰላት በፊት ተነስተው ፣ ሱና የሆነውን ለይል ሰላት የገራላቸውን ያክል ይሰግዳሉ!
ለይልን እንኳ ተነስተን መስገድ ባንችል ፈርዱን በአግባቡና በወቅቱ እንስገድ
💥ጥቂት የማይባሉ ሰጋጆች ፈጅርን በሰዓቱና በስርዓቱ አይሰግዱም!
ፈጅር ሰላትን በወቅቱ ተነስቶ ለመስገድ ከሚረዱ ነገሮች ጥቂቶችን እነሆ
1⃣ በነፍሲያ ላለመሸነፍ መወሰን
2⃣ ከዒሻ በኋላ በጊዜ መተኛትና በማይረባ ነገር ጊዜ ማቃጠልን መተው
3⃣ቀን ላይ ከልክ በላይ አድካሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን መቀነስና እራት በመጠኑ መመገብ
4⃣ በቂ ድምጽ ያለውንና ደጋግሞ የሚጮኽ አላርም (የሚቀሰቅስ ሰዓት)መሙላት በተለይ አርፍደው ከተኙ
5⃣ ከላይ የተጠቀሱት ዘዴዎች ካልጠቀሙ
ከቤተ-ሰብ ወይም ከጓደኛ መሀል አንዱ ሰላት ሲደርስ ደጋግሞ እንዲደውል ወይም ጎረቤት የሆነ ሰው በር አንኳክቶ እንዲቀሰቅሰን ማድረግ
6⃣ በተለያዩ ምክኒያቶች ያረፈደ ሰው ለሱብሒ የቀረው ጊዜ በጣም አጭር ከሆነና ከተኛ መነሳት የማይችል ከሆነ መታገስና ሳይሰግዱ አለመተኛት!
🔸አላህ መልካሙን ሁሉ ያግራልን ከስንፍናም ይጠብቀን

✍ኡስታዝ አሕመድ ኣደም
6/6/1438 ዓ.ሂ
https://t.me/ahmedadem