ሱብሃን አላህ"የአዋቂዎች ምላሽ ምንኛ ያስደምማል"
የሆነ ሰው ወደ ሐሰነልበስሪ (ረሂመሁላህ) መጣና ሰማይ መዝነብ አቆመች አላቸው:-ሐሰነልበስሪም፦ ጌታችሁን መህረት ጠይቁ አሉት።
ሌላ ሰው መጣና ' በድህነት እንደተቸገረ ስሞታ አቀረበ '
ሐሰነልበስሪም ፦ ጌታችሁን ምህረት ጠይቁ አሉት።
ሐሰነልበስሪም ፦ ጌታችሁን ምህረት ጠይቁ አሉት።
ሶስተኛ ሰውም መጣና ሚስቴ መካን ናት አትወልድም ' አላቸው"ሐሰነልበስሪም፦ ጌታችሁን ምህረት ጠይቁ አሉት ።
ከዚህ ሁሉ በኃላ ሌላ ሰው ወደ እርሳቸው መጥቶ መሬት ደረቀች አዝርዕት ማውጣትን አቆመች አላቸው"ሐሰነልበስሪ ፦ ጌታችሁን ምህረት ጠይቁት አሉት።
የርሳቸው መልስ ነበር" በዚህ ጊዜ በዙሪያቸው ያሉት እንዲህ አሏቸው ፦ ይገርማል !! ስሞታ ሊያሰማ የመጣን ሁሉ እኮ ጌታችሁን ምህረት ጥይቁ አልካቸው ? 'አሉ ።
ሐሰነልበስሪም ፦ እንዲህ የሚለውን የአላህን ቃል አላነበባችሁምን ?
((فَقُلْتُ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنَّهُ كَانَ غَفَّارًا يُرْسِلِ السَّمَاء عَلَيْكُم مِّدْرَارًا وَيُمْدِدْكُمْ بِأَمْوَالٍ وَبَنِينَ وَيَجْعَل لَّكُمْ جَنَّاتٍ وَيَجْعَل لَّكُمْ أَنْهَارًا))
አልኳቸውም (ኑህ ህዝባቸውን ሲገስፁ) ፦ ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት ፡ እርሱም በጣም መሀሪ ነውና [11] በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል ። [12] በገንዘቦችና በልጆችም ይለግስላችኃል ። ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል ። ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል(ኑህ:-10-12)
አልኳቸውም (ኑህ ህዝባቸውን ሲገስፁ) ፦ ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት ፡ እርሱም በጣም መሀሪ ነውና [11] በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል ። [12] በገንዘቦችና በልጆችም ይለግስላችኃል ። ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል ። ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል(ኑህ:-10-12)