ይድረስ ለባለ ወሰጢያው
بسم الله الرحمن الرحيم الحمد لله الذي جعلنا أمة وسطا وصلى الله وسلم على من بين لنا طريقا وسطا وعلى آله وصحبه ومن تبعهم بإحسان إلى يوم الدين أما بعد:
ከቅርብ ሳምንታት በፊት ወሰጢያ በሚል ርዕስ በያሲን ኑሩ የተለቀቀው ሙሀደራ አነጋጋሪ ሆኖ መቆየቱን ባሳለፍነው ሳምንት ሰማሁና ዛሬ የሙሀደራውን ሙሉ ቅጅ አደመጥኩ::
ለሙሀደራው የተሰጠው ርእስ ወሰጢያ (ሚዛናዊነት) ቢሆንም በውስጡ ሚዛንን ያጓደሉ ፍረጃዎች አሽሙርን የተላበሱ ትችቶችና ራስን ከማጥራራት አልፎ በተውሂድና ሱና ዳዒያን ማላገጥ የተሞላ ሆኖ ሳገኘው ተናጋሪው እንዲታረምና አድማጮችም እንዲጠነቀቁ ስል የበኩሌን እርምት እንደሚከተለው አቀረብኩ፦
በንግግሩ መክፈቻና መደምደሚያው ላይ ሰለፊይ ነን የሚሉ መዳኺላዎች በማለት ኢኽዋኖች ዘንድ የተለመደውን ስም ልጠፋ ሲደግም ይሰማል::
ኢኽዋኖች መዳኺላ ሲሉ የሚፈልጉት ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሃዲ አልመድኸሊን ለመተቸትና ስማቸውን ባልዋሉበት ለማንሳት መሆኑ አገር ያወቀው ጉዳይ ነው::
ሸይኽ ረቢዕ አል መድኸሊ የኢኽዋኖችን ወሰን ማለፍ አፅንኦት ሰጥተው ከመቃወምና ወደ ሚዛናዊነት ከመጣራት ውጭ መድኸሊያ የተሰኘ ጭፍራ ያልመሰረቱና ከቁርአንና ሀዲስ ውጭ መሪ ያደረገን ተከታይ ያላፈሩ መሆናቸው እየታወቀ ወሐቢያ በማለት ከሚዛለፉ ሰዎች ጋር መመሳሰል ከአንድ ዳዒ የሚጠበቅ አይደለም::
የሚዛናዊነት መገለጫ በተሰኘው ንዑስ አርእስት ስር አጉልቶ ለማሳየት የሞከረው ማግራራት፥ አለማጠባበቅ፥ ለቀቅ ማድረግ ወዘተ… ያላቸውን ነበር::
በቅጂው 1:08 ሰዓት ላይ “አንዲት ሴት ሂጃቧን ለብሳ ሲጋራ ስታጨስ ብትመለከታት ወንድ በላት:: ምክንያቱም ብታጨስም ሂጃቧን ግን አልለቀቀችምና” ሲል ከኢኽዋኑ ሰልማነል ዐውዳህ የሰማውን ያስተላልፍልናል::
በርግጥ ሂጃቧን አለማውለቋ መልካም ጎኗ ቢሆንም ሸሪዓችን ያዘዘዘን ግን ከሲጋራ ማጨስ ምትላቀቅበትን ጥበባዊ መንገድ ተጠቅመን መምከር እንጂ ፖዘቲቭ እይታን በማየት ብቻ ማለፍ አይደለም::
"من رئى منكم منكرا فليغيره بيده فإن لم يستطع بلسانه فإن لم يستطع فبقلبه وذلك أضعف الإيمان"
በሙሀደራው ቅጅ 1:09 ሰዓት ላይ ያስደመጠን ደግሞ በተለይ ባለንበት ዘመን ለኡማው ገራገሩን መምረጥ እንዳለብንና ሀራም ሀራም ማለትን ማብዛት እንደሌለብን ነበር::
እዛው ወረድ ብሎ ቢድዓ ሀራምና ሺርክ የዘመኑ ቋንቋ እንደሆኑ በማውራት የአንድ መድረሳ ተማሪ ተፈታኝን ተረት እየተረተ በሲርየስ ጉዳይ ታዳሚውን ሲያስቅ ይደመጣል::
በርግጥ ከሸሪዓችን መገለጫዎች አንዱ ማግራራት ሲሆን አጉል ማጠባበቅና ወሰን ማለፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው:: ይሁንና ማግራራት ማለት ግን ሀራም ሽርክና ቢድዓን ከቁርአንና ሀዲስ ውስጥ ፍቆ ለማጥፋት መታገል አይደለም::
ሽርክና ቢድዓ ከሁለቱ የእስልምና መግቢያ ምስክሮች ጋር የሚጣረሱ በመሆናቸው ሸሪዓችን አጥብቆ እንደኮነናቸው ከአንድ ዳዒ ይሰወራል ብዬ አልገምትም::ሀራም ሀያሉ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ክልክል ያደረጋቸውና እንዳንዳፈራቸው በጥብቅ ያስጠነቀቀን ተግባራት ማለት ሲሆን እነዚህን ሸሪዓዊ ህግጋት ለማላላት መሞከር ሚዛናዊነት ሳይሆን ጠርዘኝነት ነው::
ነገሩ ሽርክ ቢድዓና ሀራምን ማስጠንቀቅ ተገቢ አይደለም ማለት ተፈልጎበት ከሆነ ሀያሉ ጌታችሁን አትታዘዙ መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምንም ትታችሁ እኔን ስሙ ሊሆን ነው:: ተናጋሪውን ግን በዚ ስለማንጠረጥረው ይህን ትርጓሜ አንደፍርም የተፈለገበት ግን በዙልም መዳኺላዎች ያላቸው ሰለፊዮች ተውሂድን ሽርክ ሱናን ቢድዓ ሀላልን ሀራም የሚሉ ጥራዝ ነጠቆች ናቸው ከሆነ ደግሞ ፊቅሁል ዋቂዕ የለውም ማለት ነው أحلاهما مر እንጂ ሚዛናዊ በሚል ርእስ ስር ያለ አንዳች መረጃ ይህን ከባድ ውንጀላን ባልፈፀመነ ነበር::
በቅጂው 1:15 ሰዓት ገደማ የዓቂዳ ችግርን ማረም የአፈንጋጮች የጋራ ዜማ የሚል ስያሜ በመስጠት የዓቂዳ ዱዓቶችን ከኸዋሪጆች ጋር ለማመሳሰል ሲጣጣርም ተሰምቷል:: ቅድሚያ ለዓቂዳ… ኩን ዓለል ጃዳህ… የመሳሰሉ መፈክሮች ማስተማር እንዳልተፈለገባቸውና ጎላቸው ሌላ እንደሆነ ከመሀላ ባልተናነሰ መልኩ እርግጠኛ ሆኖ ሲናገርም ይሰማል::
እኔ የምለው በዚህ መልኩ ወደ ተውሂድና ሱና ሰባኪዎችን ማጠልሸት በየትኛው ሚዛን ነው ወሰጢያ ሊባል የሚችለው?
የሰዎችን ልብ ፈትሾ ኒያቸውን የማወቅ ችሎታ እንዳለው አስመስሎ ማሳየትስ የትኛው የዳዒ ባህሪይ ነው? ዓላማቸው ሌላ እንደሆነ የሚያውቅ ቢሆንኮ ያንን ውጉዝ ዓላማ ማስረጃን አስደግፎ መግለጥና ምላሽ መስጠት ነበረበት::
የተውሂድና ሱና ተጣሪዎች ግልፅ በሆነ መልኩ የነቢያትን መንገድ ፈለግ አድርገው ወደ ኢስላምና ወደ ኢስላም ብቻ ሰባኪዎች ናቸው ነቢያት እንደተቀጠፈባቸው እነሱም ይዋሽባቸዋል ነቢያት ሀቅና ሀሰትን ለይተው ስላሳዩ ከፋፋይ እንደተባሉ ሁሉ በሀቅ ተከታዮቻቸውም በታታኞች የአንድነት ተቃራኒዎች ሲባሉ መስማት የተለመደ ነው:: በርግጥ ከአንዳንድ ሱና ተከታዮች የእውቀት ማነስና የጥበብ ጉድለት ሊስተዋል ይችላል ያለ ሀቅ ራሳቸውን ወደ ሰለፊያ ካስጠጉ ጀመዓዎችም ግድፈቶችን ማስተዋል የተለመደ ነው:: ያም ሆነ ይህ "وزنوا بالقسطاس المستقيم" የሚለውን መለኮታዊ ትእዛዝ በቅድሚያ ራስ ላይ መተግበር ግድ ይላል::
አላህን መፍራትና እድል ሆኖ ያገኘናቸውን የዳዕዋ መድረኮችን አማና መጠበቅ ይኖርብናል:: ዝና ጠፊ ነው ምላስም ተያዥ ናት ነገ እያንዳንዳችን አላህ ፊት ለየብቻ ስንጠየቅ አጃቢዎቻችን መጥተው ሊያድኑን አይችሉም ለኔም ለተናጋሪውም ሆነ ለአድማጮች የአላህን ምህረት እለምናለው:: ያሲን ኑሩና ሌሎችም ዳዒያን አላህ የተውሂድና የሱና ሰባኪዎች እንዲያደርጋቸው የፀሀፊው (ሰልሰቢል ዙመካን) የዘወትር ምኞት ነው::
جعلني الله وإياكم ممن يستمعون القول ويتبعون أحسنه وصلي اللهم وسلم وبارك على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين وأخر
دعوانا أن الحمد لله رب العالمين