Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቀብር ላይ እንዲሁም ሃዘንተኞችን ሲያፅናኑ ቁርኣንን መቅራትን በተመለከተ •••••••••••

ቀብር ላይ እንዲሁም ሃዘንተኞችን ሲያፅናኑ ቁርኣንን መቅራትን በተመለከተ
••••••••••••••••
#ፈታዋ_ተንቢሀት
መልእክተኛው ﷺ ብዙ የሚወዷቸውን ምርጥ ሰሀቦች በሞት ተነጥቀው አዝነዋል። ሆኖም ለማናቸውም ፋቲሀ ወይም ያሲን ሲቀሩ አልተሰሙም። ልጃቸው ያለፈበት ሁኔታም በእጅጉ ያዘኑበት ነበር። ቀብር ላይም ይሁን ሀዘን ላይ ለሟች ኢስቲግፋርና ዱአ ከማድረግ ውጭ ቁርአን ሲቀሩ የተሰማበት አጋጣሚ አልነበረም። እናም ለሟች ወገኖቻችን ዱአ በማድረግ የመልእክተኛውን ፈለግ ህያው እናድርግ።
ታላቁ ሊቅና ፈቂህ ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን አልፈውዛን
አላህ ይጠብቃቸውና ስለዚህ ጉዳይ የቀረበላቸውን ጥያቄና የሰጡትን ምላሽ እናካፍላችሁ።
ጥያቄ: በአገራችን ተሰራጭቶ እንደሚገኘው ሀዘንተኛን ሲያፅናኑ ሰዎች ተሰባስበው እጃቸውን ከፍ በማድረግ ፋቲሐን ይቀራሉና ይህ ነገር በሸሪዓ ይፈቀዳልን
↪ ምላሽ:–
🔹ይህ ነገር ለታዕዚያ ሰውን ማፅናናት ሳይሆን በዲን ላይ የተጨመረ አዲስ ፈጠራ ቢደዐ ነው።
🔹ታዕዚያ መድረስ ወይም ማፅናናት ማለት ሀዘን ለደረሰበት ሰው:–
👉አላህ ፅናትህን የተሻለ ያድርግልህ፣
👉ያጋጠመህንም ጉዳት አላህ ይጠግንልህ፣
👉ሟችህንም አላህ ይማርልህ ማለት ነው።
ቁርአንን መቅራት ወይም ፋቲሃን ወይም ከቁርአን የሆነን ክፍል (ለታእዚያ) መቅራትን በተመለከተ ምንም አይነት ማስረጃ አልመጣም።
በቀብር ስነ ስርኣት ወቅት እንዲሁም ቀብር ላይም ሆነ ቀብር ዘንድ ሆኖ ቁርአን መቅራትን በሚመለከት ምንም ማስረጃ ባለመምጣቱ ይህ ነገር በሙሉ በዲን ውስጥ የተጨመረ ፈጠራ ነው።
📓 قـراءة القـرآن في العـزاء .
• لـ فضيلة الشيخ العلامة الفقيه /
صالح بن فوزان بن عبد الله الفوزان
- حفظه الله ورعاه -
`````````````````````````
🔊 لسمــاع المقطــع الصوتــي :
http://www.alfawzan.af.org.sa/sites/default/files/01_3.mp3
◇◇◇

© ተንቢሀት