Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ትዝብተ FB! ክፍል ሁለት



ትዝብተ FB!
ክፍል ሁለት

✘ ሐያእ (አፍረት) መጥፋት!

ነብዩ ﷺ በተለያዩ ሐዲሶቻቸው የሐያእን አስፈላጊነትን አስተምረዋል።

«ሐያእ አንዱ የኢማን ቅርንጫፍ ነው።»

በሌላ ሐዲሳቸው ደግሞ፦

«ሐያእ የሚያመጣው መልካምን ነገር ብቻ ነው» ሲሉ ተናግረዋል።

የኢማናችን መድከም ከሚያሳብቁ ምልክቶች አንዱ የሐያእ ከሰዎች ላይ መገፈፍ እና መጥፋት ነው። ይህም ከተጋረጡብን አደጋዎች ትልቁን ቦታ ከሚይዙት አንዱ ነው።

በተለይ ከሙስሊም እህቶቻችን ላይ የጠፋ ብርቅዬ መገለጫ ሆኗል። ሱብሐነ ረቢ! በጣም የሚያሳዝን እኮ ነው!

ድሮ ድሮ ሙስሊም ሴት የምትታወቀው በአፍረቷ ነበር አሁን እንኳን በዲኗ ላይ ብዙ ግንዛቤ የሌላት እህት ይቅርና ራሷን ወደ ዲን እውቀት ያስጠጋችው እሱም ብቻ አይደለም የመልዕክተኛውን ﷺ መንገድ ተከትያለሁ የምትለዋ እህት ላይ ራሱ መታየት ካቆመ ሰንበትበት ብሏል ።

ይህን ስል መልካሞች የሉም ማለት አይደለም ግን ራስሽን ታውቅያለሽ ቆም በይና ያለሽበትን ሁኔታ አስተውይ። FBም ላይ ይሁን በእውነተኛው ዓለም ያለሽበትን ሁኔታ ታዘቢ ስለራስሽ አንቺ የበለጠ ታውቅያለሽ።

የሴቶች ሁኔታ ሲበላሽ የዚህ ኡማ ጉዳይ እየተበላሸ መሆኑን ልናውቅ ግድ ይለናል።

እህቶቻችን FB ላይ በየደቂቃው እየገቡ የሚለቁት ፅሁፍ በጣም የሚያሳቅቅ ነው። በተደጋጋሚ FB ላይ መግባቱ ራሱ አንድ ችግር ሆኖ ሳለ የሚለቁትና እሱንም ተከትሎ የሚሰጣጡት ኮሜንት እጅጉን ያሳዝናል። ይባስ ብሎም ስለ ሐያእ መነሳቱም ቅር የሚያሰኛቸው አልጠፉም። ወድ እህቴ! ዲን አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ የሚሄዱበት እንደ ምግብ ብፌ የፈለጉትን የሚመርጡበት አይደለም።

ፎቶዋን በፌቢ የምትለቅን እህት እንደምንወቅሰው ፌቢ ላይ ተጥዳ የምትውለውንንና አላስፈላጊ ወሬ የምታወራውን ተገቢ ያልሆነ ኮሜንት የምትሰጠውንም እህት እንወቅሳለን።

ወንዶችም ጋር ቢሆን ያለው ነገር ተመሳሳይ ነው። እኛም ዘንድ ሐያእ ሊኖር ግድ ነው።

ወንዶች ሆይ! ለእህቶቻችን ሐያእ ማጣት እዚህ መድረስ ተጠያቂው ማንም ሳይሆን እኛው መሆናችንን ፈፅሞ እንዳንረሳ! እንዴት የሚለውን በአላህ ፍቃድ በቀጣይ ርዕሶች ላይ ለማንሳት እሞክራለሁ ከተጠያቂነት የትም ማምለጥ የለም! ።

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል…

መልካም ሆኖ ካገኙት እባክዎ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ያድርጉት!