Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

“ነገር ግን ዛሬ ላይ አዲስ የዳዕዋ ስልት ያስፈልገናል!” [የሸኽ ኢብኑ ባዝ ምላሽ]

“ነገር ግን ዛሬ ላይ አዲስ የዳዕዋ ስልት ያስፈልገናል!” [የሸኽ ኢብኑ ባዝ ምላሽ]
════════════════════════════════
የተከበሩት ታላቅ ሸይኽ ዐብዱል 'ዐዚዝ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ተብለው ተጠየቁ. .
የትኛውም ዘመን ከግዜው ጋር የሚሄድ አካሄድ አለው። ሰለፎች (ቀደምት አበው ትውልዶች) ትምህርቶችን (ዱሩሶእችን) እና ኹጥባዎችን ተጠቅመዋል። እኛ ግን የበለጠ ውጤታማ ዘዴዎች አሉን። (ለምሳሌ. .) መልከ መልካም ወጣት የኃጢዓተኞችን እና የጠጪዎችን ገጸ-ባሕሪ እየመሰለ ተውኔት (ድራማ) ለማስተማር ቢተውንስ?. . በመሆኑም የተከበሩ ሸይኽ መሰል ድርጊቶችን እንደሚያበረታቱልን ተስፋ እናደርጋለን?
👤 ሸይኹ እንዲህ ሲሉ መለሱ. .
አላሁ አክበር! አላሁ አክበር! አላሁ አክበር! አላሁ አክበር!
ምን አይነት አስደንጋጭ ውሸት ነው! ምን አይነት አጸያፊ ንግግር ነው!
↪ የመልእክተኛው (አላህ ደረጃቸውን ከፍ ያድርገው ሰላምም ያውርድባቸውና)፥ የአስሓቦች፥ የሰለፎች መንገድ ለዚህ ዘመን ፋይዳ የለውምን? ከድራማ እና ከውሸት ውጭ አይጠቀሙምን? ከእኩይ በአላህ እንጠበቃለን። ጠያቂ ሆይ! በርግጥም ውሸትና ቅጥፈት ተናግረሃል። ሰላምን ከአላህ እንጠይቃለን።
💥 መልእክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምና) ባልደረቦቻቸው ተውኔትን አልተወኑም። «እኔ አቡ ጀህል ነኝ!» ወይንም «እኔ አቡ በክር ነኝ. .» ፤ «እኔ ሙሐመድ ነኝ. .» ለምን ይዋሻል?
🔗 የሚሉት. . «አላህ እንዲህ አለ. .» ፤ «መልእክተኛው እንዲህ አሉ. .» ፤ «አላህን ፍሩ! . . ይህ ተው! . . ይህ የተፈቀደ ነው. . ይህ ያልተፈቀደ ነው. .» ነበር የሚሉት። ይህ ነው ህዝቡን የሚጠቅመው።
🔵 ፂሙን የተላጨ ሰው መጥቶ «እኔ አቡ በክር ነኝ!» ፤ «እኔ ዑመር ነኝ» ይላል። ማን ነው ይህ ሰው? ምንድን ነው ይህ እኩይ ንግግር? በአላህ እጠበቃለሁ!
♻ ተውኔት ሐራም ነው! እሱ ውሸትና ቅጥፈት ነው! አላህን ሰላም እንጠይቀዋለን! በአላህ እጠበቃለሁ! አላህን ሰላም እንጠይቀዋለን!
ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል. .
۝ (( وإنهم ليقولون منكرا من القول وزورا )) ۝
۩ {{ እነርሱ ከንግግርም የተጠላንና ውሸትን ይናገራሉ። }} ۩
[አልሙጃደላህ ፡2]
════════════════════════════════
📚 [Sahab.net.]

Abu Aisha