Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ ሐፊዞሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-

ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ ሐፊዞሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
“በሚያሳዝን ሁኔታ በጥፋትና በስህተት ባለቤቶች ላይ መልስ በመሰጠቱ ምክንያት የሚቆጩ ሰዎች አሉ፡፡ እነሱን (አጥፊዎቹን) ለመወዳጀት፣ ከነሱ ለመከላከል ይመረቅናሉ፡፡ ጥፋቶችና ስህተቶች ላይ መልስ የሚሰጡትን ግን ያርቃሉ፣ ይጠላሉም፡፡ ከባድ በሆነ መልኩም አሳልፈው ይሰጧቸዋል፡፡ ታዲያ ለሰዎች ይሄ ድርጊታቸው ልስላሴና ጥበብ እንደሆነ ያስመስላሉ፡፡ ይሄ እጅግ ከባድ ከሆኑ ፈተናዎችና መከራዎች ውስጥ ነው፡፡ የጥፋት ሃይሎች በጥፋታቸው እንዲጸኑ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ፊትናቸውን እንዲረጩ ያደረጋቸው ይሄ ነው፡፡ እነዚህ ክፍሎች የዚህ አደገኛ አቋማቸውን የኋላ ውጤት ምነው በተረዱ፡፡ ለነሱ ቅናቻንና ግንዛቤን እንዲሁም የሙሐመድ ﷺ ጥሪን በመርዳትም ላይ ሃላፊነታቸውን እንዲረዱ አላህን እንለምንላቸዋለን፡፡ በዚህም ላይ የወቃሾች ወቀሳ የማያስፈራቸው እንዲያደርጋቸውም እንዲሁ፡፡”
[በያኑ ማ ፊ ነሲሓቲ ኢብራሂም አርሩሐይሊ ሚነል ኸለል ወልኢኽላል፡ 26]

Ibnu Munewor