በዚህ
በኩል የተከተሉት ስልት ቁርኣንና ሐዲስን መሰረት ያደረገ ነው። እጅግ አርኪ ስልትም ነው። የቢድዓ አራማጆችን
የተሳሳቱ መረጃዎች በግልፅ ይጠቅሳሉ። ከዚያም ምላሽ ይሰጡባቸዋል። ሱንናውን መከተልና ከቢድዓና ከአዳዲስ ነገሮች
መታቀብ ግዴታ ለመሆኑ የቁርኣንና የሀዲስ መረጃዎችን ያቀርባሉ። በዚህ መስክ በርካታ መፅሀፍትን ፅፈዋል። ስለ አቂዳ
በፃፏቸው መፅሐፍት ለሺዓ፣ ለኽዋሪጆችና፣ ለጀሕሚያ፣ ለሙእተዚላ፣ ለአሸዐሪያና ለሌሎችም አንጃዎች እምነቶች አጥጋቢ
ምላሽ ሰጥተዋል። በዚህ መስክም በርካታ መፅሀፍትን ለንባብ አብቅተዋል። ከነኝህ መፅሀፍት ውስጥ “ረድ ዐለል
ጀሕሚያ” በሚል ርዕስ ኢማሙ አህመድ የፃፉት መፅሀፍ በአብይነት ተጠቃሽ ነው። ሌሎች ኢማሞችም በዚህ መስክ
መፅሀፍትን ፅፈዋል። ዑስማን ኢብኑ ሰዒድ አድዳርሚይ፣ ሸይኽል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህና ተማሪያቸው ኢብኑል ቀይዪም፣
መሀመድ አብዱል ወሐብና ሌሎችም እውቅ ዑለሞች በዚህ በኩል ተጠቃሽ ናቸው። እነኚህ ዑለሞች ለአንጃዎች ለቀብር
አምላኪያንና ለሱፍዮች ምላሽ ሰጥተዋል።
በቢድዓ አራማጆች ላይ የተፃፉ መፅሀፍት በርካታዎች ናቸው። ከዚህ በታች ጥቂቶቹን ዘክረናል፦
በቀደምት መፅሐፍት፦
1. አል-ኢዕቲሷም በኢማሙ ሻጢቢይ
2. ኢቅቲዷዕል ሲራጠል ሙስተቂም በኢማም ኢብኑ ተይሚያ
3. ኢንካሩል ሐዋዲስ ወልቢደዕ በኢብን ዋዲህ
4. አል-ሐዋዲስ ወልቢደዕ ጡርጡሺ
5. አል-ባኢስ ዐላኢንሳሪል ቢደዕ ወልሐዋዲስ በአቢሻመህስ
በዚህ ዘመን ከተፃፉ መፅሃፍት፦
6. አል-ኢብዳዕ ፊመዷሪል ኢብቲዳዕ- አብዱልዐዚዝ ኢብን ባዝ
7. አል-ሱነን ወል ሙብቲዳዐህ አል-ሙዐለቃህ ቢል አዝካሪ ወሰለዋት በሸይኽ መሐመድ ኢብኑ አህመድ ሸቂሪይ
8. አትተሕዚር ሚነል ቢደዕ በሸይኽ አብዱል ዐዚዝ ኢብን ባዝ።
የሙስሊም ዑለሞች ባለንበት ዘመን በጋዜጣዎች፤ በመፅሔቶች፤ በሬድዮኖች፤ በጁምዓ ንግግሮች፤ በሲምፖዚየሞችና በተለያዩ የሌክቸር ዝግጅቶች ቢድአን ከማውገዝና ለቢድዓ አራማጆች ምላሽ ከመስጠት አልተዘናጉም። ለአላህ ምስጋና ይድረሰው። ይህ እንቅስቃሴያቸው የሙስሊሞችን ንቃተ ህሊና በማዳበርና ቢድዓን በማጥፋት ቢድዓ አራማጆችንም በመምታቱ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።
[ከሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን ኪታቡ አል-ኢርሻድ የተወሰደ]