Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢብኑ ባዝ እና ሰይድ ቁጥብ…


ኢብኑ ባዝ እና ሰይድ ቁጥብ…
“አርረሕማን ዐለል ዐርሺ ኢስተዋ” የሚለውን አስመልክቶ ሰይድ ቁጥብ እንዲህ ይላል፡- “በዐርሹ ላይ ኢስቲዋእ ማድረግ ማለት ይህንን ፍጡር የሚቆጣጠር እንደሆነ ለመግለፅ ነው ማለት እንችላለን፡፡” [ዚላሉል ቁርኣን፡ 4/232፣ 6/340]
ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
“ይሄ ሁሉ ብልሹ የሆነ ንግግር ነው፡፡ ይህ ማለት ኢስቲዋእን በቁጥጥር መተርጎም ነው፡፡ ኢስቲዋእን እንደሚገባ አላፀደቀም፡፡ ያቀረበው ሀሳብ የታወቀውን ኢስቲዋእ ማስተባበል ነው፡፡ እሱም ከዐርሹ በላይ መሆን ነው፡፡ ይህ የሱ ትንታኔ ሰውየው በተፍሲር ደካማ ምስኪን እንደሆነ የሚያሳይ ከንቱ ንግግር ነው፡፡”
ይህንን ኪታብ (የሰይድ ቁጥብን ዚላል) ሰዎች እንዲያነቡት ሁሌ የሚመክር እንዳለ አንዱ ሲያወሳላቸው ኢብኑ ባዝ እንዲህ አሉ፡-
“ይሄ ንግግሩ ባጢል ነው፡፡ በጭራሽ! ስህተት ነው፡፡ ይሄ ንግግሩ ውድቅ ነው፡፡ ኢን ሻአላህ እንፅፍበታለን፡፡”
ሶሐቦችን የሚሳደብበትን ንግግሩን ከሰሙ በኋላ ኪታቡን ቦጫጭቆ መጣል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ሊንክ ይግቡና ይስሙ፡፡