Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የአይን ፀጉር ላይ አርቲፊሻል መቀጠል እንዴት ይታያል?

የአይን ፀጉር ላይ አርቲፊሻል መቀጠል እንዴት ይታያል?
#ፈታዋ_ተንቢሀት
👉 በሸይኽ ሙሐመድ ሷሊሕ ኢብን አል-ኡሰይሚን
አንድ ማስታወሻ ለእህቶች... ፀጉራችን ላይ አርቴ ከመጠቀም የተቆጠብን ብዙ ነን አልሀምዱሊላህ!! ነገር ግን በተዘዋዋሪ መንገድ ሰርግም ሆነ ሌላ ፕሮግራም ሲኖር የአይን ፀጉር ላይ የሚቀጠለዉ አርቲፊሻል ፀጉር እንዴት ይታያል?? ብዙ እህቶች ሲጠቀሙት ይስተዋላልና ሁክሙን መጠየቅ ግደታችን ነዉ።
ታላቁ አሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን ረሂመሁላህ ይሄን አስመልክቶ ተጠይቀው የሰጡትን ምላሽ እናንብብ፦
ጥያቄ፦ አንዲት ሴት በአርቲፊሻል የአይን ፀጉር ለባሏ ብትዋብ ይፈቀዳልን?
መልስ፦ ሰዉሰራሽ የዓይን ፀጉር መቀጠል አይፈቀድም። ምክንያቱም ልክ ፀጉር ላይ እንደሚቀጠል ዊግ ነው!
ነብዩ ﷺ ቀጣያዋንም አስቀጣይዋንም እረግመዋል!
አርቴፊሻል የአይን ፀጉር ሲባል እኔ እንደገባኝ ከሆነ፤ ፀጉሩ በዝቶና ደምቆ እንዲታይና አይን ይበልጥ ውብ እንዲሆን ዘንድ የአይን ሽፋሽፍት ላይ የሚቀጠል ፀጉር ከሆነ፤ ልክ ነብዩ ﷺ የእራስ ፀጉር መቀጠልን እንደረገሙት አይነት ነው። ነገር ግን አርቴፊሻል የአይን ፀጉር ማለት ቅንድብን ማቅለም ከሆነ ይህ ችግር አይኖረውም።]
{ፈታዋ ኑሩን ዓለ-ደርብ ካሴት ቁጥር 330}
السؤال: أحسن الله إليكم وبارك فيكم فضيلة. الشيخ السائلة أم معاذ من الرياض تقول: ما حكم استعمال الرموش الصناعية للتجمل بها عند الزوج؟
الجواب: الرموش الصناعية لا تجوز؛ لأنها تشبه الوصل أي وصل شعر الرأس، وقد لعن النبي صلى الله عليه وسلم الواصلة والمستوصلة، وهذه الرموش إذا كانت مما أتصوره الآن أن يوضع خيوط سوداء كالشعر على الرموش حتى تبدو وكأنها كثيرة تتجمل بها العين فإذا كان هكذا فهي من الوصل الذي لعن النبي صلى الله عليه وسلم فاعلته في رأسها، أما إذا كانت الرموش بمعنى تلوين الشعر شعر الأجفان فإنه ليس بحرام. نعم.
المصدر: سلسلة فتاوى نور على الدرب > الشريط رقم [330]
https://zadgroup.net/bnothemen/upload/ftawamp3/Lw_330_12.mp3
© ተንቢሀት