Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሴት ልጅ መሕረሞች እነ ማን ናቸው? ለምንስ አስፈለገ?!

↪የሴት ልጅ መሕረሞች እነ
ማን ናቸው?
↪ለምንስ አስፈለገ?!
🚩ውዱ ነቢያችን
የሚከተለውን ብለዋል
("በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምን ሴት ከሷ ጋር መሕረም ሳይኖራት መጓዝ አይፈቀድላትም " )
💥ሴት ልጅ ለብቻዋ ( መሕረም ሳይኖራት) መጓዝ የምትችለው ለሂጅራ (በሀገሯ እምነቷን በአግባቡ መከተል ተከልክላ ስትሰደድ) ብቻ ነው።
ለሴት ልጅ (በየትኛውም እድሜ ላይ ብትኖር)
⛤መሕረም ያስፈለገበት አንዱ ምክንያት ሴት ልጅን ከተለያዩ ድንገተኛና የሚገመቱ ከሆኑ መንፈሳዊም ይሁን አካላዊ ጉዳቶችና ጥቃቶች ለመጠበቅ ሲሆን ይህን ኀላፊነት መወጣት የሚችሉ ሰዎች እነማን እንደሆኑና የሴት ልጅ መሕረም ማን እንደሆነ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እራሳቸው ገልጸዋል እነሱም የሚከተሉት ናቸው:-☞☞
🔮(አባትና አያት፣ ባል፣ወንድ ልጅና የልጅ ልጆቿ፣ ወንድሞች የወንድምና የእህት ልጆች፣ በአባትም ይሁን በእናት በኩል ያሉ አጎቶች (የወላጆቻችን ወንድሞች)፣ የወላጆቻችን አጎቶች፣ የጡት ወንድሞች፣ የአንዲት ሴት የሴት ልጇ ባል (አማች)፣ የእንጀራ አባት
( የእናት ባል) ሲሆኑ ከዚህ ውጭ ያሉ ወንዶች ቀረብ ያሉ ዘመዶች እንኳን ቢሆኑ
📌ለምሳሌ፥ (የአጎትና የአክስት ልጆች) መሕረም መሆን አይችሉም!
↪ይህን የሸሪዓ ህግ በመጣስ መሕረም ከማይሆኗቸው ወንዶች እየተጓዙ የተለያዩ ጥቃቶች የደረሱባቸው ብዞዎች ናቸው!
አይደለም ራቅ ያለ ዘመድና ባዕዱ ይቅርና ከላይ ከተጠቀሱ ቅርብ ዘመዶችና መሕረም ሊሆኑ ከሚችሉ ሰዎች ውስጥም አንዱ በመጥፎ ስነምግባር የሚታወቅና የሴትን ክብር አይጠብቅም የሚባል ሰው ከሆነ ከሱ ጋር መጓዝ አይፈቀድላትም!
💥ትክክለኛ መሕረም ይሆን ዘንድ ታማኝና ከሴት ልጅ አደጋን መከላከል የሚችል መሆን አለበት ፣እድሜውም ጠቃሚና ጎጂን ለይቶ ለማወቅና ጥቃትን ለመከላከል የደረሰ መሆን አለበት፣ እንደዚሁም
ጾታው ወንድ መሆን አለበት
↔ሴት ለሴት በየትኛውም መልኩ መሕረም ልትሆን አትችልም
🔸በዘመናችን በርካታ ሴቶች በሸሪዓው መሕረም ከማይሆናቸው ወንድ ጋ ለብቻቸው መኪና ላይ ሲጓዙ
ይታያል!ይህ ትልቅ ስህተትና ዲኑ የማይፈቅደው ተግባር ነው!ረጅም ጉዞ ባይሆንና ከተማ ውስጥ እንኳን ቢሆን አይቻልም!
ምክንያቱም ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል
(" አንድ ወንድ ከባዕድ ሴት ጋ ተነጥሎ ለብቻቸው አይቀመጡም ሶስተኛው ሸይጣን ቢሆን እንጂ! ")
መቼም ሸይጣን ባለበት ቦታ ላይ መጥፎ ነገር ማሰብ ወይም መከሰቱ የማይቀር ነው
🔸"ተነጥለው ለብቻቸው" የሚለው ነብያዊ ቃል ቤት ውስጥ አንድ ክፍል ላይ መሆንን ብቻ ሳይሆን መኪና ውስጥ ለብቻቸው መጓዝንም ጭምር እዚህ ውስጥ እንደሚካተት በዘመናችን ያሉ ዑለማዎች ገልጸዋል!
በዚህ መልኩ ለብቻቸው ከከተማ የወጡና ራቅ ብለው የሄዱ እንደሆነ ጥፋትና ቅጣቱ የተነባበረ ይሆናል አደጋውም ይከፋል!
ይህን ነቢያዊ መመሪያ የጣሱ በርካታ እህቶችም አምነዋቸው አብረዋቸው ይጎዙ በነበሩ ሾፌሮች ወደውም ይሁን ተገደው ተደፍረዋል!!
ህይወታቸው ላይም ብዙ ችግሮች ደርሷል የሰው ልጅ ደካማ ነው ስሜት በሩ ካልተዘጋጋ ሁሉንም ሊያጠቃ የሚችል ነገር ነው! ዛሬ ያልተከሰተው ነገ ሊከሰት ይችላል!
🔹ከተማ ውስጥም ቢሆን ከአጅነቢይ ሾፌር ጋ ለመሄድ ከተገደዱ ከነሱ ጋ ሌላ ሶስተኛ ታማኝ ሰው አብሯቸው ሊኖር ይገባል።
🔸እንደዚሁም በየትኛውም መልኩ ከአጅነቢይ ወንድ ጋ ( ማንም ይሁን ማን) በር ዘግተሽ አትቀመጪ!
አንድ ክፍል ውስጥም ከባዕድ ወንዶች ጋ ተቀላቅለሽ አታሳልፊ የራስሽንም ይሁን የወንድሞችሽን ኢማን ለአደጋ አታጋልጪ! ዘመኑ የፊትና ነው የብዙዎች ቀልብ ደርቃለች አኼራም ተረስቷል፣አላህን ከማስቀይም ተጠንቀቂ! ነገ መገናኘታችሁ አይቀርምና!
አላህ ከክፉና እሱንም ከሚያስቆጣ ነገር በሙሉ ይጠብቅሽ!ወሰላም
✍ አሕመድ ኣደም
25/3/1438 ዓ.ሂ