ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ አሏህ ይሁን ሰላትና ሰላምም የነቢያት መደምደሚያና ለዓለም እዝነት ተደርገው በተላኩት ነቢያችን ሙሐመድ ላይ ይስፈን
🔸ጀነት ሲባል ውስጡ ደስታ የማይሰማውና የማይጓጓ ሙስሊም የለም:: ካለም ኢማኑን መፈተሽ ይጠበቅበታል ምክንያቱም ሰው ሆኖ ሀገሩን የማይናፍቅ የለም::
🔑የሙእሚኖች ሃገር ጀነት ናት
❗ ወደ ዱኒያ የመጣነው ስራ ሰርተን ለመመለስ ነው::
የመጣለትን ዋና ዓላማ የዘነጋና የሚኖርበትን ሃገር ምንነት የማያውቅ ሰው በጊዜው በሚያገኛቸው ወቅታዊ መደሰቻዎች ሊብቃቃና ሊረካ ይችላል::
💥 ሙእሚን ግን ቁርጠኛ ነው ወኔውም ትልቅ ነው ዓላማውንም አይዘነጋም::
በሁለቱም ዓለም እንደፈለጉ ሆኖ መኖር እንደማይቻል ያውቃል::
📌አሏህ
በተከበረው ንግግሩ "ባሪያዬ ላይ ሁለት ስቃዬን አልሰበስብም፣ ሁለት ሰላምም አልሰጠውም፣አዱኒያ ላይ ከፈራኝና
ህጌን ካከበረ ከሞት በኋላ ባለው ህይዎቱ ሰላምን እሰጠዋለሁ፣ ዱኒያ ላይ ህጌን ከጣሰና ካልፈራኝ ከሞት በኋላ
ስጋትና መከራ እንዲፈራረቅበት አደርገዋለሁ“ ማለቱን ሁሌም ያስታውሳል::
👉እነሆ ዱኒያ ላይ አሏህን ፈርቶ ወንጀለ የተወ፣ ስሜቱን ያሸነፈ አኼራ ላይ እንዳሻው ይኖራል።
👉ዱኒያ
ላይ እንደፈለጉ እየሆኑና አሏህንም እያስቀየሙ ኖረው፣ ከሞት በኋላ ጀነትና ጸጋዎቿን መመኘት ትልቅ ሞኝነትና
በዱኒያ ላይ ብዙ ነፍሳቸው የምትፈልጋቸውን ነገሮች ለአሏህ ብለው ትተው የኖሩ ሰዎችንና ያሻቸውን ስያድበሰብሱ
የኖሩትንም አሏህ አንድ ዓይነት ደረጃና ማዕረግ ይሰጣቸዋል ብሎ ማሰብ በመሆኑ አሏህ ሰዎችን ይበድላል ማለትም ጭምር
ነው::
🕹ጀነት አሏህ ለመልካም ሰሪ ባሪያዎቹ የሚሸልማት መቼም የማትጠፋ ውድ ንብረት ናት:: ይህን ታላቅ ሽልማት ለማግኘት አስፈላጊውን ነገር ማሟለት የግድ ነው::
📌 እያንዳንዱ ሰው አሏህ ዘንድ ጀነትን ሊያስሸልመኝ የሚችል ስራ ምን አለኝ? እያለ እራሱን ሊፈትሽ ይገባዋል::
💥ጀነት የሚገባው በአሏህ ራህመት ቢሆንም ከገቡ በኋላ ደረጃዎች የሚመደቡት ይሰሩት በነበረው መልካምስራ መሰረት ነው::
🔹ጀነት
አፈሯ ለም የሆነች ባዶ መሬት ናት ባሪያው ከተውሂድ ጋር ዱኒያ ላይ መልካምን ስራ በሰራና ከወንጀል በታቀበ
ቁጥር የጀነት ባዶ መሬቱ ላይ መላይኮች ይዘሩለታል፣ ይተክሉለታል የአኼራን የተሟላ ደስታና እረፍት የፈለገ
በሙሉ ዱኒያ ላይ ላለማረፍ መወሰን ይጠበቅበታል !ካልሆነ ግን ሁሉን ወዶ የለም!
✍ አሕመድ ኣደም
ረቢ ኢግፊር ሊ ወሊዋሊደየ ያከሪም