★ልጄ ሆይ!! ዱንያ(ምድራዊ ህይወት) እንደ ጥልቅ ባህር ነች በሷም ብዙዎች ሰምጠዋል ስለዚህ በሷ ላይ ለመንሳፈፍ ከፈለክ ጀልባህን የአላህ ፍራቻ መቅዘፊያህን ኢማን መንገድህን ደግሞ በአላህ ላይ መመካት አድርግ፡፡
★ልጄ ሆይ!! ከፈሪሃ አላህ ሰዎች ጋር ሁሌም ተጎዳኝ
እነርሱ በሚሰሩት ስራ ተካፋይ ትሆናለህና በተጨማሪም
የአላህ ልዩ ፀጋ በነርሱ ላይ ሲወርድ አንተም ከድርሻው
ታገኛለህና ከመጥፎ ሰዎች ጋር አትጎዳኝ ከነርሱ የሚገኝ
መልካም ነገር የለምና ይልቅስ የአላህ ቅጣት በወረደ
ችባቸው ጊዜ አንተም ከቅጣቱ ተካፋይ ከመሆን በቀር፡፡
★ልጄ ሆይ!! ዘወትር አቀማመጥህ ከኡለማዎች ጋር ይሁን እነዚህ ብልሆች የሚናገሩትን ከልብህ አድምጥ፣ ከአላህ
መልካም ምንዳ በተስፋ ስትጠብቅ ቅጣቱንም በመፍራት ይሁን፣ዘወትር ጌታህን ከሀጢያትህ ይምርህ ዘንድ ጠይቅ፡፡
★ልጄ ሆይ!!ከሀሰት ጨርሶ ራቅ ሀሰት ጠላትን እንጂ ወዳጅን፣ ጥላቻን እንጂ ፍቅርን አያፀናም በቀብር ስነ ስርዓት ላይ ዘወትር ተገኝ የነገን ሞት ያስታውስሃልና ከድግስና ከጭፈራ ቦታ ራቅ ድግስ ከንቱ አለማዊ ደስታን እንድትናፍቅ ያደርግሃል አላህ ዘንድ ስትቀርብ ይዘኸው የምትሄደውን ስራ
ያዘናጋሀል ያለመጠን አትመገብ፡፡
★ልጄ ሆይ!!እጅጉን ጣፋጭ አትሁን ሰዎች ይበሉሃል ፣ እጅግም አትሁን አንቅረው ይተፉሃል ሌት እንደ ዶሮ ንቃት
ይኑርህ፣ ለተውበት ዛሬ ነገ አትበል ሞት አዘናግቶ
ይወስድሃልና ከጅላጅሎች አትጎዳኝ አይረቤ ንግግሩንም
አትከታተል፡፡ ከብልህ ሰዎች ጋር ፀብ አትፍጠር ካንተ
ከሸሹ ከዕውቀታቸው ተጠቃሚ አትሆንምና፡፡
★ልጄ ሆይ!!አላህን ከሚፈራ ካልሆነ ሰው ጋር አትመገብ ምንጊዜም ኡለማዎችን አማክር ከዕዳ ሽሽ ዕዳ የቀን ውርደት የማታ ፀፀት ናት ከአላህ ራህመት ተስፋ አትቁረጥ ተስፋህ ያለ
ቅጥ ደንድኖ ለሃጢያት እንዳያበቃህም ተጠንቀቅ አላህን
ፍራ ፍርሃት ግን ከእርሱ እዝነትና ተስፋን አስቆራጭ አይሁን፡፡
ከምክሩ ተጠቃሚ ያድርገን።